ETHIO12.COM

ኢትዮጵያን ሊበላ የተነሳው “አውሬ” ሴራ ተጋለጠ፤ “30ሺህ ሳምሪ ሱዳን ታጥቆ ቀዳዳ እየፈለገ ነው

አሁን አሁን ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ዋና ማዘዣ ጣቢያ ያለው፣ በእቅድ የሚመራ፣ በጥናት የሚሰራ፣ ለትግበራው በተዋረድ መስመርና ሰንሰለት የተበጀለት ዘመቻ እንደሆነ እየታየ ነው። ለዚህ ሪፖርት መነሻ ያነጋገርናቸው “እንዲህ በዋና ማዘዣ የተደራጀና መዋቅር ያለው ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም አያውቁትም። አሁን አሁን መንፈሳዊ እየሆነብኝ ነው። አውሬው ነው” ብለዋል።

እሳቸው እንዳሉት በተለየ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያን እያንቀረቀቡ ያሉትና ትልቅ ጎላ በርሜል ውስጥ ከተው ሊቀቅሏት የሚሰሩት ሃይሎች በታብሎይድ ደረጃ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ዓለም ” አንቱ” ያላቸው፣ ነገር ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ስነምግባራቸውን የሰቀሉ ሚዲያዎች ናቸው።

በሸገር ሺልፍ የህግ ማብራሪያ የሚሰጡት አቶ አብዱ አሊ ” እነዚህ ” ሲሉ ትላልቅ የሚባሉትን ሚዲያዎች እየጠሩ ” የስነምግባር ካባቸውን የሚደርቡት በአገራቸው ጉዳይ ነው” ሲሉ ዝርዝር ጥፋታቸውን ከስረገው ማንነታቸው ጋር በወል እያጣቀሱ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ሰሞኑንን ለፓርላማ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም እፊታቸው የተቀመጡት የነዚሁ ሚዲያዎች ተቀጣሪና ወኪሎች እንዲሰሙ በሚል “የምናውቀውን እውነት እየዋሻችሁ የማናውቀውን ልንገራችሁ ብትሉን እንዴት እንመናችሁ” ሲሉ መናገራቸው እንደ መሪ የቁጣቸውን ገደብ የሚያሳይ ነው።

የዚሁ ኢትዮጵያን የማጥፋቱ አስፈሳሚ ከሆኑት አንዱ ስንጣሪ የሆነው ፋይናንሻል ታይም የተባለው ሚዲያ አሳፋሪ፣ አስገራሚ፣ አስደንጋጭና ቲያትርም የሚመስል መተጣጠፍ አሳይቷል።

ፋይናሻል ታይም የትህነግን ሃላፊዎች ጠቅሶ አሁን ቀሪው ዘመቻ ጠላትን ከምዕራብ ትግራይ ( ወልቃይት ማለቱ ነው) በማስወጣት ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ ኮሪዶር ማግኘት፣ ይህ ሲሆን ሱዳን ሰለጥነው በዝግጅት ላይ ያሉ ሰላሳ ሺህ ወታደሮችም ጦርነቱን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ እንዳሉ አስነብቧል።

ከአፍታ በሁዋላ ” ሰላሳ ሺህ ወታደሮች” የሚለው ” ሰላሳ ሺህ ያልታጠቁ ንጹሃን” በሚል መቀየሩ ታየ። መረጃውን አስመልክቶ ከላይ የጠቀስናቸው ” ይህ የሚያሳየው ዘገባውን ዋናው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሰራው የማዘዣ ቢሮ ካየው በሁዋላ ሚስጢር መውጣቱን አይቶ አስቸኳይ መመሪያ በመስጠቱ የተወሰደ ማስተካከያ ነው። የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ተመልሰው ሊያርዱ ወደ ነበሩበት ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ስትወተውት የሰማ አልነበረም። አሁን ራሳቸው አጋለጡ። የአምላክ ስራ ነው” ብለዋል። አክለውም “በማያካድራ ጉዳይ ሃቁን ይፋ አድርጎ ሳይገፋበት ሆን ብሎ የተኛውና፣ በመጨረሻ ጭፍጨፋውን የትህነግ አለቆች ስለማዘዛቸው ማረጋገጫ የለም ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሞሽን እርቃኑንን ቀርቷል። ይህን ሲመከለት ሊያፍር ይገባዋል” ሲል ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

“ባልታጠቁ ታማኞች” እና በ“ወታደሮች” መካከል ጥልቅ ልዩነት አለ። በእውነቱ የዚህ ዘገባ ጥራት እና ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል ” ስትል የአቶ ኮኮብን መረጃ ደግማ ያሰራጨቸው ብራውኒ ብሩቶን የአትላንቲክ ካውንስል አጥኚ ናት። እንስቷ ለውጡ እንደፈነዳ ኤርትራና ኢትዮጵያ የጋራ ጠላት አላቸው ስትል መረጃ ላይ ተመስርታ የጻፈችና ሃሳብ ያቀረበች ናት።

በማይካድራ በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆችን አርደውና ጨፍጭፈው ወደ ሱዳን ያመሩት ሳምሪዎች፣ ሚሊሻዎችና የትህነግ ልዩ ሃይል አባላት ሱዳን ስደተኛ ጣቢያ ሆነው ፎቶ ሌሱ ሲሉ ፊታቸውን ቀለብ በሚቀበሉበት ሳህን የሚሸፍኑት ስለሚታወቁ መሆኑንን መንግስት ማስታወቁ አይዘነጋም።

ትህነግን ኢትዮጵያ ላይ መሪ ያደረጉት ኸርማንኮን ከሶስት በጁን 21 የትህነግ አመራሮች ወደ ሱዳን እንዲገቡ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሪዶር ይክፈት ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል። ይህ ንግግራቸው ” ልቀቋቸውን እዛ ሄደው ከ30 ሺህ የወገን ጦራቸው ጋር ተደራጅተው ይውጓቹህ ማለት ነው። ይህ ኢትዮጵያን የማጥፋቱ ሴራ መዋቅራዊ፣ የተጠናና በዋና እዝ ቢሮ የሚመራ መሆኑንን ያሳያል” ሲሉ አስተያየት ሰጪው ይናገራሉ።

እኚሁ ሰው አሁን ኢትዮጵያ ላይ በተከፈተው ደረጃ አንድም አገር ላይ እንዲህ ዓይነት መረባረብ አይተው እንደማያውቁ አመልክተው፣ ሚዲያው ምንም ጉዳይ ይሁን ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ከሆነ የሙያ ጉዳይ እንደማያስጨንቅ ገልጸዋል።

የማይካድራ ዕልቂት
የማይካድራ ጭፍጨፋ

“ሴኩሪቲ ካውንስል በትግራይ ጉዳይ ስንት ጌዜ ተሰበሰበ?” የሚሉት አስተያየት ሰጪ፣ በትናንትናው ዕለት የፈረንሳዩ ወኪል “ የአባይ ጉዳይ የሴኩሪቲ ካውንስል አጀንዳ እንዲሆን አንፈልግም” ማለታቸው ከሳቸው በተቃራኒ የሚፈልጉ መኖራቸውን አመላካች መሆኑንን ገልጸዋል። ይህ ደግሞ ጉዳዩ “የትግራይን ህዝብ መውደድ ወይም ለትግራይ ህዝብ ፍቅር ተብሎ ሳይሆን ትህነግና እነሱ ብቻ የሚያውቁት፣ እኛም፣ ኦነግም፣ አብንም ሌሎቹም አስፈጻሚባንዳዎች የማይውቁት ጉዳይ እንዳለ የሚያመላክት ነው” ብለዋል።

” አስቤው አስቤው አልገባ ለኝ” የሚሉት አስተያየት ሰጪ ” በዚህ ደረጃ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የትህነግ ስራ አስኪያጅ እስኪመስሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ መጠመዳቸው፣ቲዊት የሚያደርጉ ነጮች ብዛት፣ የነጭ ፖለቲከኞች አድማው ልክ ማጣቱ፣ የሚዲያዎች ሃፍረትና ልጓም አልባ መሆን…” መድረሻ ያለው ኢትዮጵያ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነው” ይላሉ። ሲያጠቃልሉ ” እንደ አዝማሪ እናንተም የ3000 ዓመት ታሪክ አላት እያላችሁ ትዘፍናላችሁ” ሲሉ አዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ለመጅመሪያ ጊዜ ጋዜጠኞችን ሰብስበው የተናገሩትን ያስታውሳሉ። የዛኔ ማንም እንዳልገባውና ንግግሩ ለእሳቸው ብቻ የሚገባ እንደነበር ጠቁመው ” ኢትዮጵያ እንዴት የ100 ዓመት ታሪክ ብቻ እንዳላት ማረጋገጫ ሳይሰጡና ሳያገኙ ሄዱ፣ አሁን በግል የገባኝ ጉዳዩ መንፈሳዊ መሆኑ ነው”

መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን ስሟን መጥራት የማይወዱ፣ ታሪኳ የአዝማሪ የሆነ፣ ከ100 ዓመት በላይ እድሜ የሌላት ጨቅላ አገር እያሉ ሲናገሩ የኢትዮጵያ ህዝብ አይገባውም ነበር የሚለው አሳብ ዛሬ ላይ እንደ አዲስ እየተነሳ ነው። በርካታ የትህነግ አጋርና አስፈሳሚ ” ቡችላ” የሚባሉት ድርጅቶችና ግለሰቦችም ተንኮሉን ሳያውቁ ትህነግ የተሰጠውን የቤት ስራ እንደሚያስፈጽሙ ዝምታን መርጠው የነበሩ እየገለጹ ነው።

ፋይናንሻል ታይም ሳምሪ የሚባሉትን ጨምሮ የማይካድራን ህዝብ ጨፍጭፈው ወደ ሱዳን የገቡ ሃይሎች በዩናይትድ ኔሽን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሆነው ወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ ተቀብለው ለዳግም ፍጅት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የኮሪዶሩን መከፈት እንደሚጠብቁ ውስጥ ውስጡን ሲባል የነበረውን ጉዳይ ይፋ አውጥቶታል። በዚህ ካምፕ ጋዜጠኞች የመብት ተከራካሪዎች ገብተው የማጣራት ስራ እንዳይሰሩ መከልከላቸው ይታወቃል። ጋዜጠኞችና መንግስትም ሆነ የአማራ ክልል በሱዳን በኩል ቀዳዳ ላለመስጠት መዘጋጀታቸውን እየገለጹ ነው። የኢትዮጵያ አየር ሃይልም ስፍራው ሜዳ በመሆኑ ጥቃት ለማድረስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰምቷል።

አቶ ጌታቸው ረዳም በቲውተራቸው አማራ ሚሊሻ እያደራጀ መሆኑንን በመጥቀስ እንደሚደመሰሱ አስጠንቀቀዋል። ” ወደ ወገን፣ ወደ ደጀን ገባ” የተባለው ሰራዊት በበኩሉ ” ቁስሌ ሽሯል” እያለ ነው። በትግራይ እንደ ባዕድ ወራሪ ሚጥሚጣና በርበሬ ሳይቀር ከገጀራ ጋር የወረደበት የኢትዮጵያ መከላከያ “መንደር ውስጥ በመደበቅ ሳይሆን የወታደር መለዮ ለብሶ በፍትሃዊ ውጊያ የሚሆነውን እናያለን” እያለ ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን በጨዋነት ሁሉንም ወገኖች ለማስማማት የተሳ ሃይል አልታየም።

በሌላ ዜና በትግራይ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በትህነግ ታጣቂዎች መገደላቸው፣ ግድያውም አካባቢን የለየና በፍረጃ መሆኑ እየተገለጸ ቢሆንም ስጋት ከመግለጽ በዘለለ ዓለም ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳለው እየታየ ነው። የኤርትራ ስደተኞች በስደት ካምፓቸው የመጠበቅ መብት ቢኖራቸውም ትህነግ እንደጨፈጨፋቸው ቢቢሲ በውስጥ ገጹ ከመጻፉ በስተቀር ሌሎች መንግስታት፣ የመብት ተሟጋቾች፣ ሚዲያዎች ” አልሰማንም” በልዋል። በተለይም ትግራይ ሆነው አይናቸው ስር ሰው ሲገደል የሚያዩ ሚዲያዎችና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ዝምታ መምረጣቸው ጉዳይ የተቀናጀው አሰራር አካል እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

በአሜሪካ የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች በስደት ጣቢያ ውስጥ ያሉ እየተገደሉ፣ እየታፈኑና አድራሻቸው እየጠፋ መሆኑንን ገልጸው ለተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ ዘርፍ ጠይቀው ” የቪዲዮና የፎቶ ማስረጃ አምጡ” መባላቸውን ከጠያቂዎች መካከል አንዱ ለኢትዮ12 አመልክቷል።


Exit mobile version