ዓለም ባንክ ተከተለ – ግብጽ ሚስጥሩን ይፋ አደረገች

ዛሬ የዓለም ባንክ ያወጣው አጠር ያለ መግለጫ ወይም ዜና፣ ግብጽን በመፈንቅለ መንግስት እንዲመሩ የተፈቀደላቸው አልሲሲ ካርቱም ገብተው ያሰሙት ንግግርና ከሚዲያ ዘመቻው በሁዋላ ኢትዮጵያ ላይ ክንዱን ለማንሳት እየሰራ ያለው የጸጥታው ምክር ቤት ማብራሪያዎች ” ዘመቻው የተቀነባበረና የተቀመጠ ዓላማ ያለው ነው” የሚለውን አስተያየት እያጎላው ነው። ለዚህ ሁሉ የዳረገው ትልቁ ችግር የሃያ ሰባት ዓመቱ አዝመራ የፈጠረው መለያየት ነው።

የዓለም ዓቀፉ ተቋማት፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችና “ገለልተኛ” የሚባሉት ሚዲያዎች “ግፍ” ሲሉ የመብት ጥሰት በምን እንደሚመዝኑት ግራ በሚያጋባ መልኩ የትህነግ መሪዎች፣ ያሰለጠነው ሰራዊት፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ በተቀነባበረ መልኩ ፈጽመውታል በሚል የሚቀርቡት ነብስ አስጨናቂ በደሎች ችላ ብለው፣ የግጭቱ ሁሉ መነሻ የሆነውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ጭፍጨፋ ዘንግተው ኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትት የተቀናጀ ዘመቻ የተቀነባበረና መድረሻ ያለው መሆኑንን የሚጠቁሙ ወገኖች ጉዳዩ ወደ ማጠቃለያ እያመራ መሆኑንን እየገለጹ ነው። ከግምት በላይ ዓላማው በገሃድ ባይገባቸውም።

ለዚህም በዋናነት የሚያስቀምጡት የጸጥታው ምክር ቤት የውስጥ ጉዳይ ላይ ገብቶ ውስኔ ሊያሳልፍ መሞከሩንና አሜሪካ በግልጽ የአማራ ብሄር አባላት ላይ ሲፈጸም የነበረውን አሳዛኝ ግፍ እንዳላየ በመሆን ያሳለፈችው ውሳኔ ነው። በዚሁ መነሻ የአሜሪካንን ውሳኔ ተከትሎ አሜሪካ እንዳሻት የምትነዳው የቅኝ ተገዢዎች ስብሰብ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር መሞከሩን የሚጠቅሱት ወገኖች፣ የጸጥታው ምክር ቤት አካሄድ አሁንም ቀጣይ ዲስኩር ለማድረግ እቅድ መያዙ ኢትዮጵያ ላይ ለሚካሄደው የማያቋርጥና ዓላማና ግብ ያለው ዘመቻ መሳካት የሚደረገው ትንቅንቅ ቀላል እንደማይሆን ነው።

ዛሬ ካርቱም የገቡት አልሲሲ “ከሱዳን ጎን እንቆማለን” ሲል በንግግራቸው አጉልተው አሰምተዋል። የህዳሴ ግድብ ሙሌት የሚደረግ ከሆነ ሱዳንና ግብጽ ካልፈቀዱ ውርድ ከራስ አይነት ዛቻም አሰምተዋል። በድርድሩ አውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታት ከአፍሪካ ህበረት ጋር እንዲቀላቀሉ ኢትዮጵያ በግድ መስማማት እንዳለባት ጠቁመዋል። ይህ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በትግራይ ተስታከው ሊጠመዝዟት ካሰቡት አካሎች እጅ እንድትገባ የሚደረገውን አካሄድ መሆኑን ይፋ የሚያድርግ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩን የአፍሪካ ህብረት እንዲይዘው፣ ሙሌቱም በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚቀጥል ይፋ ካደረገች በሁዋላ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለየ ምላሽ አልሰጠችም? ግን ግብጽ ለምን የተባበሩት መንግስታት፣ በአገር ደረጃ አሜሪካና አውሮፓ ህበረትን መረጠች? ይህ ሁሉ የሚያሳየው ግብጽ ከሁሉም ጨዋታ በስተጀርባ መሆኗን ያሳያል የሚሉ እስራኤልን እንደ ዋና የጨዋታው ድብቅ አከተር አድርገው ማስቀመጥም ከጀመሩ ሰንብተዋል።

ይህ ከላይ የተባለው ሁሉ እየሆነ ባለበት ዛሬ የካቲት 27 “የአሜሪካ እጅ መጠምዘዣ፣ዋና የፍላጎትዋ ማስፈጸሚያ ነው” የሚባለው ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ሁኔታ እንደሚያሳስበው አስታውቆ በኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅዶች መነሻነት ለኢትዮጵያ ሊያደርግ ቃል የገባውን ድጋፍ እንደሚያጤን ይፋ አድርጓል። ” ተከፋይና ልዩ አጀንዳ አራጋቢ” የሚል ስም በተሰጣቸው ሚዲያዎችና ውስን አክቲቪስቶች፣ እንዲሁም በትራምፕ ዘመን ከዋይት ሃውስ ፖለቲካ የተገለሉ ዲፕሎማትና ባለስልጣናትን ውስወሳ እየጋመ የመጣው ዘመቻ ኢትዮጵያን ምን ሊያደርጋት እንዳሰበ ተገልጾለት ቁርጥ ያለ ጉዳይ ያስቀመጠ አካል አለመኖሩ ለአብዛኛው ዜጎች ራስ ምታት ሆኗል። ለትህነግ ደጋፊዎችና ” ኢትዮጵያን እንበትናለን” ለሚሉ ደግሞ ሰርግና ምላሽ ሆኗል።

” እየሆነ ያለውን አጤናለሁ ” ሲል ስጋቱን የገለጸው ዓለም ባንክ አድሮ ምን ቅድመ ሁኔታ እንደሚያስቀምጥ ቃል በቃል ባይታወቅም ማስፈራሪያው ልክ አሜሪካና አውሮፓ ህብረት እንዳደረጉት ገንዘብ መያዝ እንደሚሆን የድርጅቱ ባህል ያረጋግጣል። በዚህ መነሻ ” ታላላቅ” የሚባሉት አገሮች፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ዓለም ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረትንና የአሜሪካን ዱካ ተከትለው በጫና ኢትዮጵያን ለማሽመድመድ መነሳታቸው እያደር ግልጽ እየሆነ መምጣቱ ከውስጥ የፖለቲካ ቀውሱ ጋር ተዳምሮ አደጋውን የከፋ እንዳያደርገው ስጋት የገባቸው ” በአስቸኳይ የውስጥ ፖለቲካው ቀውስ እንዲለዝብ መደረግ አለበት” ይላሉ። አያይዘውም ” የውስጥ ቀውሱና አንድ አለመሆኑ ለውጭው ጫና ዳርጎናልና ፖለቲከኞች ቅድሚያ ለአገር እንዲሰጡና ሊመጣ ያለውን ችግር በህብረት ለመቋቋም ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ መድረክ መዘጋጀት አለበት” እያሉ ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ቀውስ ውስጥ ናት። አሜሪካና አውሮፓ ህብረት ድጎማ ከልክለዋታል። የዓለምን ኢኮኖሚ ሽባ ያደረገው የኮቪድ ጣጣ ኢኮኖሚዋን ጎድቶታል። ላለፉት ሶስት ዓመታት ለውጡ ያስኮረፋቸው መልካቸውን እየቀያየሩ ባደረጉት ዘመቻ ለቁጥር የሚያታክት ኪሳራና ሰብአዊ ቀውስ ጎድቷታል። በዚሁ ሳቢያ የውጭ ንግዷ ተዳክሟል። ሆን ተብሎ በበጀት ሲፈጸም የነበረው የዜጎች መፈናቀል፣ አሰቃቂ ግድያ፣ አፈና፣ ንብረት ማውደም፣ የደቦ ፍርድ … ” እንደ ዛሬው የትርክት ጩኸት ለዓለም ሚዲያዎች ግብዓት እንዳይበቃ በር ቢዘጋበትም ጠባሳው አሁን ድረስ አለ። በቅርቡ የሚቆምም አይመስልም።

አገሪቱ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በአክራሪ ብሄርተኞችና “የውጭ አጀንዳ ተሸካሚዎች ናቸው” በሚባሉ አካላት ቤንዚን ሲርከፈከፍባት፣ በዩቲዩብ አብዮት የታፈነ ሁሉ ምን እንደሚያስከትል ሳያሰሉ ገቢያቸውን ብቻ በማየት መርዝ ሲረጩባት በአገሪቱ የተካሄደው ለውጥ እንከን ፈላበት። ተጠርቅሞ የቆየው የ27 ዓመቱ አገዛዝ ሲከፈት ከየአቅጣቻው በማወቅና ባለማወቅ፣ በተላላኪነትና በከፍተኛ ክፍያ የእሳት ወላፈን በሚረጩ ዜጎቿ አገሪቱ መወጠሯ ከተረጋገጠ በሁዋላ የአገር መከለከያ ላይ በድንገት እሳት ተለኮሰ።

ምሁሩ፣ ታላቁ፣ አዋቂና ሃይማኖተኛ የሚባሉት በአብዛኞች እዘር ቅርቃር ውስጥ ገብተው በዩቲዩብ ሲፏከቱ፣ መርዝ ሲያከፋፍሉ ኢትዮጵያን ትከሻው ላይ አድርጎ ሲጓዝ የነበረው የአገር መከላከያ መመታቱ፣ መታረዱና በጭነት መኪና መጨፍለቁ ተሰማ። ተከፋዮች የሚለያይ ፖለቲካና አጀንዳ እየሰፈሩ አገሪቱን ሲያነዱ፣ መለያት ማስፋታቸው ከዓላማው አንጻር ኢንቨስትመንቱ ውጤታማ መሆኑንን በስኬት የገመገመው ትህነግ ” መንግስት እንዲሆን ዳግም ህዝብ ጠየቀኝ” ሲል አስነገረ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የመናከሻ አጀንዳ እያስቀመጠ ተቆርጦ ባላለቀው እጁ መንግስትን መሰረሰር፣ በውጭ አገር ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ያለ አንዳች ጣልቃ ገብነት በገነባው ዓለም አቀፍ መስመር ከፍተኛ ክፍያ በሚከፍላቸው ወስዋሾቹ አማካይነትና በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ስም በሰገሰጋቸው ልጆቹ አማካይነት የዲፕሎማሲ ዘመቻውን አፋፋመ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የገባቸውም ያልገባቸውም ለተቀጣሪ የዩቲዩብ ገጾችና አክቲቪስቶች ምላሽ ለመስጠት ደፋ ቀና ሲል የከረመው ዜጋ ዛሬ ዓለም በፍርደ ገምድል የሚዲያ ዘመቻ ተጠናብራ ኢትዮጵያ ላይ በውል የማይታወቅ ዘመቻ ስትከፍት መንግስትን በዲፕሎማሲ ደሃ መሆኑንን ይናገር ጀመር። መንግስት ከአለፈው 27 ዓመታት ጥፍጥፍ የትህነግ ተላላኪ አገልጋዮቹ እንዳይገላገል የከፋ የቤት ስራ እየተሰጠው እሳት አጥፊ እንዲሆን ሲሴርበት፣ ዛሬ ወቀሳ ላይ ያሉ ወገኖች ቢያንስ ከተራ ሃሜት አለወጡም ነበር።

መድረሻቸውን አስበው ተላላኪ በማዘጋጀት፣ ቅጥረኞችን በመልመል፣ የሃሰት ሚዲያዎችን በግልጽና በተዘዋዋሪ በማዘጋጀት፣ በተሰወረ ማንነትና በሌሎች ብሄሮች ስም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ ሲከፈት፣ ሳያነብ ሼር ሲያደርግና አብሮ ሽብር ሲያባዛ የኖረ ሁሉ ዛሬ ወቃሽ መሆኑ አሳዛኝ ሆኗል። ዛሬ አገሪቱ በምርጫ ዋዜማ ላይ ባለችበት ወቅት፣ ከላይ የተዘርዘረው ዘመቻ ሊከፈትባት የቻለው በራሳቸን ችግር መሆኑንን ዛሬም ያልተረዱ መርዛቸውን አሁንም እየረጩ ነው። እነዚህ ዜጎቻችንና የደቦ ዘመቻ እያካሄዱ ያሉት አገሮች ልዩነታቸው ግልጽ ባይሆንም ነገሮች ወደ ማብቂያቸው እየሄዱ ይመስላል።

አውሮፓ ሕብረት፣ አመሪካ፣ የሴኩሪቲ ካውንስልና ” ና ሲሉት” የሚባለው ዓለም ባንክ ጅራፋቸውን እያጮሁ ነው። እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚያስፈልገው ሁለት አንኳር ጉዳዮች አሉ። አውሮፓ ህብረት የሚጮኸው ስደተኛ ፍርሃቻና ፍርሃቻ ብቻ የመሆኑንን ጉዳይ ነው። የወላይታ ወይም ይትግሬ፣ ወይም የከንባታ ወይም አማራ ነበስ በስትራቴጂክ ጉዳይ ሲለካ ለአውሮፓ ህብረት አገራት አኩል ነው። ለትግራይ የሚጮሁት አንድ የአካለ ጉዛይ አርሶ አደር ከመተከል ገበሬ በልጦባቸው ሳይሆን ” ስደተኛ ተቀበሉ” የሚለው ውሳኔ በህብረቱ እንዳይወሰን ነው። ሩጫው ይህ ሳይሆን አማራን አውግዘው ኢትዮጵያን እጇን ጠምዝዘው ስድተኞችን ከመከፋፈል ጣጣ ለመውጣት እንደሆነ፤

ሁለተኛው እውነት አሜሪካም ሆነ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትህነግ ጋር ፍቅር ኖሯቸው አይደለም። ከትህነግ ጋር ያላቸው ፍቅር ስላበቃ ነው እንዲያስረክቡ ስም ተጠቅሶ የተነገራቸው። በዚህ ብስጭት ስም ተጠቅሶ እንዴት አስረክቡ እንባላለን በሚል ነው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ” እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መሪ ቃል ነገቶ እስክመሽ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲደበድቡ የከረሙት፣ አሁንም የቀጠሉበት። በዚህ መነሻ አሜሪካም ሆነች አውሮፓ በመርህ ደረጃ ትህነግን የሚናፍቁበት ምንም መነሻ የለም። እናም ጩኸቱና አድማው ምን ምክንያትን አንግቦ ነው? ሱዳን የተገኙት የግብጽ መሪ በድርድሩ በደቦ ከዘመቱት ሚዲያዎች በቀር ኢትዮጵያን ቀለበት ያደረጉት ተቋማት እንዲሁም አሜሪካ በድርድሩ በአስቸኳ እንዲሳተፉ በይፋ ጥሪ ሲያቀርቡ ጨዋታውን ይፋ ያደርገዋል የሚሉ ወገኖች እየተሰሙ ነው። ዓለም ባንክ ውስጥ እነማን አሉ? አገርህን የምትሸጥ አስብበት!!

    You may also like...

    Leave a Reply