My new book, US Policy Toward Africa: Eight Decades of Realpolitik, is now available. I draw on both the documentary record and my personal experiences as a diplomat to analyze how US-#Africa policy has evolved through fourteen US administrations. https://t.co/nEmRatDEQB
— Herman J. Cohen (@CohenOnAfrica) January 14, 2020በሎንደን ትህነግን ከትከሻው በላይ ስልጣን በመስጠታቸው የሚወቀሱትና ከለውጡ በፊት ለቪኦኤ ያን ማድረጋቸው እንደሚቆጫቸው ያስታወቁት አንጋፋ ዲፕሎማት ኸርማን ኮሆን ከምርጫው በሁዋላ አዲስ መላ እንዳላቸው አስታወቁ።
ኮሆን በቲውተር ገጻቸው እንዳሉት “የትህነግ ቱባ” ያሉዋቸው በነጻ ወደ ሱዳን እንዲወጡ ቢደረግ እንደሚሻል አመልክተዋል። ዛሬ መከላከያ እግር በግር እያሳደደ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ አሰሳ መቀጠሉን ባስታወቀበት ወቅት ኮሆን ይህን ማለታቸው ጥያቄ አጭሯል።
ኮሆን ያቀረብት መላ ወይም ሃሳብ ” የሰው ልጆች ሰቆቃ አሁን መቆም አለበት” በሚል መነሻ ነው። ይህም እንዲሆን ” የትህነግ ቁንጮዎች / መሪዎች በነጻ ወደ ሱዳን እንዲወጡ ይደረግ፣ መሳሪያ ይፍቱና በዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጥላ ስር እንዲቀመጡ ይደረግ” ባይ ናቸው።
ከዛም መላቸውን ሲያጣፉት ” ከዛሬ ምርጫ በኋላ የአሜሪካና የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የጠበቀ ትብብር መጀመር አለባቸው” ብለዋል። ይህ ዜና ዝም ብሎ የመጣ እንዳልሆነ ይገመታል።
በለውጡ እውን መሆን ዋዜማ ” አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አለበት” ሲሉ የተከራከሩት ኮሆን እንደ ሌሎች ሁሉ በቀድሞው መንፈሳቸው ኢትዮጵያ ላይ ዘመተው ነበር። ዛሬ ምርጫውንና የምርጫውን የህዝብ ግብረ መልስ ካዩ በሁዋላ ይህ ውስጥ ውስጡን ሲባል የቆየና ኢትዮጵያ አይሆንም ያለችውን የድርደር ሃሳብ ” መሳሪያ ጥለውንው በስደተኞች ድርጅት ስር እንዲቀመጡ ተደርጎ” የሚል ሃረግ አካተው ያመጡት የእርዳታ ድርጅቶች ላማስወጣት ያደረጉት ተከታታይ ሙከራ ባለመሳካቱ እንደሆነ ተገምቷል።
ምርጫው ፖለቲካውን እንደሚቀይር የተነገረው እውነት መሆኑንን ግን የኮሆን መላ አመላካች እንደሆነ ማረጋገቻ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።