Site icon ETHIO12.COM

8 ሺህ 400 ክላሽንኮ፣ ሽጉጥና ጥይት አዲስ አበባ ከገባ በሁዋላ ከነባለቤቶቹ ተያዘ

በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ጥይቶች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B-13357 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ጥይቶችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአ/አ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው 18 ማዞሪያ መብራት ሀይል ቀለበት መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በወቅቱ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ 8ሺህ 400 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ እና 998 የኢኮልፒ ሽጉጥ በአጠቃላይ 9ሺህ 398 ጥይቶች በጥይት ማሸጊያ ሳጥን እና በጨርቅ ተጠቅልለው እስኮርት (ቅያሪ) ጎማ ውስጥ እንዲሁም በተሽከርካሪው የፊተኛው ክፍል ተደብቀው ተይዘዋል፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሃገር እና በህዝብ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ በዚህ እና በሌሎች ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ማቅረቡን ኢዜአ ዘግብቧል


Exit mobile version