በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ጥይቶች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B-13357 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ጥይቶችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአ/አ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው 18 ማዞሪያ መብራት ሀይል ቀለበት መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በወቅቱ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ 8ሺህ 400 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ እና 998 የኢኮልፒ ሽጉጥ በአጠቃላይ 9ሺህ 398 ጥይቶች በጥይት ማሸጊያ ሳጥን እና በጨርቅ ተጠቅልለው እስኮርት (ቅያሪ) ጎማ ውስጥ እንዲሁም በተሽከርካሪው የፊተኛው ክፍል ተደብቀው ተይዘዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሃገር እና በህዝብ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ በዚህ እና በሌሎች ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ማቅረቡን ኢዜአ ዘግብቧል
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF