Site icon ETHIO12.COM

በአምቡላንስ ተጭኖ ከቡራዩ ወደ አምቦ ሲጓጓዝ የነበረ ጥይት ከነባለቤቶቹ ተያዘ

ጥይቱ መድሃኒት በማስመሰል በሴቶች ታይት ውስጥ ሞልተው በማዳበሪያ ከተው ነበር ሲያጓጉዙ የተገኙት። ጥይቱን መድሃኒት አስመስለው ዚጓዙ የተጠቀሙት የመንግስት አምቡላንስ ነው። ፋርማሲስት፣ ሁለት ተቀባዮችና አሽከርካሪው ተይዘዋል

በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በመንግስት አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል።ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው አዋሮ ቆራ አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ትናንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው ግለሰቦቹን ከነጥይቶቹ መቆጣጠር የተቻለው ብለዋል።

ኮማንደር ሲሳይ እንዳመለከቱት፤ ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በሴቶች “ታይት” አልባሳት ጠቅልለው በማዳበሪያ ውስጥ መድሃኒት አስመስለው በመጫን ከቡራዩ ከተማ ወደ አምቦ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው የተደረሰባቸው።በዚህም አሽከርካሪው፣ ፋርማሲስት እና ሁለት የጥይቱ ተቀባዮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ ይገኛል።ፖሊስ ህገወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ኅብረተሰቡ አጥፊዎችን በመጠቆም የድርሻውን እንዲወጣም ኮማንደር ሲሳይ ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version