ETHIO12.COM

ወገኛ ምርኮዎች !!

የሽብር አለቃው ወያኔ አገራችንን ለማፈራረስ በከፈተው ውጊያ አማካኝነት መዋያቸው በትምህርት ቤት ሊሆን የሚገባቸውን መለመል የትግራይ ታዳጊዎች በበሬው ወለደ ፕሮፖጋንዳ በዘር ትብትብ እያሰረ ወደለኮሰው የእብሪት ጦርነት እየማገደ ሲሆን ከሰሞኑ በማይጠምሪ ግንባር በከፈተው ውጊያም በግንባሩ በተሰማራው የመከላከያ ሰራዊታችን ፣ የአማራ ልዩሃይል ፣ ሚሊሻና ፋኖ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡

የነበራቸውን የስራ ባህሪ ፣ የቅልጥፍና ሁኔታና አካላዊ ሁኔታ መሰረት ባደገረ መልኩ የተለየ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የነበሩና የተማረኩ የሽብር ቡድኑ አባላት አብዛኞቹ አገርና ህዝብን በከዱ አመራሮቻቸው ስውር አጀንዳ የተጠለፉና ብዙ እውር አላማ እንደነበራቸው ከግንባሩ የሚዲያ ቡድን ጋር የነበራቸው ቆይታ ያመላክታል፡፡ ከእድሜዋ በላይ የሆነ የሽብርና የተንኮል እውቀት አሸክመው ለተልዕኮ ያሰማሯት ነፃነት ሰይፈ በተሰጣት የመረጃ እና የመሃንዲስ ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመመሳሰል የሰራዊቱን እንቅስቃሴ በመከታተል መረጃ የመሰብሰብ ፣ በተሽከርካሪ ላይ ፈንጅ የመጥመድ ፣ የአማራ የሆኑና የሚዘረፉ ንብረቶችን የመለየት ፣ የማቃጠል ፣ የጦር መሳሪያ ያላቸውን የአማራ ብሔር ተወላጆች በመለየት የማሳወቅ ግዳጅ ተሰጥቷት ነበር፡፡

የጁንታውን እኩይ አላማ ለማሳካት በተመሳስሎት ብዙ ርቀት ተጉዛ ዘሪማና አካባቢው የደረሰችው ነፃነት ሰይፈ ምንም እንኳ በማይጠምሪ ግንባር በተሰማራው ሰራዊታችንና የፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ብትውልም በአድርቃይና በማይጠምሪ በነበራት ስምሪት የአማራ ብሄር ተወላጆች ሃብትና ንብረት ሲዘረፍ እንዲሁም በማንነታቸው ተለይተው እየተመረጡ ሲገደሉ ማየቷን መስክራለች፡፡

የአክሱም ነዋሪ የነበረው አብዱልቃዲር ያሲን የአገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ረዳት ሆኖ ሲሰራ በተለይ የአማራ ክልልን በብዙ የስራ አጋጣሚ ስለሚያውቀው ተብሎ ተመርጦ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በሚደርሱባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ከሚገኙ ድርጅቶች የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን በመዝረፍ ወደ ትግራይ እንዲጫን የማድረግ ተልዕኮ ተቀብሎ ነበረ ዳሩ በውጊያ ቆስሎ ተማረከ እንጂ፡፡

ለትግራይ ህዝብ ካለው ላይ ቀንሶ የተለያዩ የመሰረተ-ልማቶችን የሠራውንና የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት ከኋላ በመውጋት ክህደት የፈጸመው የሽብር ቡድን የትግራይን ህዝብም ከኢትዮጵያዊ ወገኑ በመነጠል ለሰቆቃና እንግልት እንደዳረገውና ለአላማው ማስፈፀሚያም በጦርነት እንደማገደውም ተናግሯል፡፡ አሸባሪው ትህነግ በአክሱም የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ግፍ ሲፈጽም መኖሩን የሚገልፀው አብዱልቃድር ለአላማው ማስፈፀሚያ ሲሆን ግን “መንግስት ሃይማኖታችንን ለማጥፋት በትግራይ ላይ ጦርነት አውጆብናል” በማለት ህዝቡን እያሰለፈ መሆኑንም ምርኮኛው በአንክሮ ገልጿል፡፡

ቡድኑ ህዝባዊ ጦርነት በማወጅ በአሁኑ ወቅት የሃይማኖት አባቶችን ፣ አዛውንቶችንና እናቶችን የእኩይ አላማው ዋና ተዋናይ በማድረግ ህፃናትን በዕፅ እያደነዘዘ ከማሰለፉም ባለፈ ሀሺሹን በጨርቅ በመጠቅለል “የአክሱም ፅዮን ማርያም ፀበል ነው ፤ ጥይት አያስመታችሁም” በማለት በአንገታቸው ላይ አስረው ወደ አውደ ውጊያ እንዲገቡ መደረጋቸውን ያጋለጠችው ደግሞ ሌላኛዋ የማርያም ሸዊት ተወላጇ ሴት ምርኮኛ ፅገ ጉዑሽ ስትሆን በውጊያ ወቅት ቆስላ እየታከመች ባለችበት ወቅትም በአንገቷ ላይ ተገኝቷል። “ወደ አማራ ክልል ገስግሰን መሬታችንን አስመልሰን ጎንደርን ፣ ባሕርዳርንና ፣ አዲስ አበባን ተቆጣጥረን ተጋሩዎች የማንሸነፍ ጀግኖች መሆናችንን እናሳያቸዋለን፡፡

” በሚል ማነሳሻ ይኖርበት ከነበረው እንዳምባጉና የ5ኛ ክፍል ትምህርቱን አስትተው ከእኩዮቹ ጋር ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስድ አድርገው ወደጦርነት እንዳሰለፉት የተናገረው ሙሉዓለም መኮንን ደግሞ እሱ በተሰለፈበት ግንባር ብዙ ታዳጊዎች ያለእድሜያቸው መቀጨታቸውን ተናግሮ ደፋር ትሆናላችሁ በሚል አደንዛዥ-ዕፅ ይጠቀሙ እንደነበርና ጥይት አይመታችሁም በሚልም በአንገታቸው ላይ ሀሽሽ አስረው ወደ ውጊያ እንዳስገቧቸው መስክሯል።

አፈ-ቀላጤዎቹ እነ ጌታቸው ረዳ “መንግስት በየሚዲያው የጦር ምርኮኞች ናቸው ብሎ የሚያቀርባቸው ከአረብ-አገር ተመላሽ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችን ነው፡፡” ብለው የሚያቀርቡት ጭፍን ውሸት መሆኑን ያረጋገጡት ምርኮኞቹ እነሱም በማይጠምሪ ግንባር ከተሰለፉበት ውጊያ ቆስለው ከተማረኩት ጊዜ ጀምሮ የተደረገላቸውት ህክምና እና እንክብካቤ በከሃዲ አመራሮቻቸው እንደተነገረው ሳይሆን ሰራዊቱም ድሮ አካባቢያቸው ላይ እንደሚያውቁት አዛኝ ህዝቡም ወዳጅ እንጂ ጠላት አለመሆኑን በእዝነት ገልፀዋል።

ህዋሃታዊያን ጀሌዎች “ያለእኛ አገር ማኖርና ህዝብ መምራት ዘበት ነው” ብለው በዘረፋ ያግበሰበሱትንና ያከማቹትን አንጡራ ሃብትና ንብረት ሁሉ አርፎ መብላት አላስችላቸው ብሎ የትግራይ ወጣቶችንና ታዳጊዎችን በህዝብና በስርዓት ጠል የሃሰት አጀንዳ በመጥለፍ ብዙ እንደሰራባቸው ከእድሜያቸውና ከትምህርት ደረጃቸው በላይ የጁንታውን አላማዊ ማንነት አቀላጥፈው የሚተነትኑት እኚህ በማይጠምሪ ግንባር የተያዙ ወገኛ-ምርኮዎች አስረጂ ናቸው፡፡

“ኢትዬጵያ ታሸንፋለች” መላክ በቃሉ (ከግዳጅ ቀጣና)ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ – መከላከያ ፌስ ቡክ የተወሰደ

Exit mobile version