“በዋግ ኽምራ ዞን የሽምቅ ዉጊያዉ አሁንም ቀጥሏል፡፡ የአሸባሪው ታጣቂዎች ተደምሥሷል”

ወደ ዋግ ኽምራ ዞን የገባው የህወሓት ታጣቂ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻዎች እና ሌሎቸ ታጣቂ ሀይሎች ባደረሱበት ከባድ ምት የሽብርተኛው ታጣቂዎች ተደምሥሠዋል። ቡድኑ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቅቆ እየሸሸ ይገኛል።

የኢፕድ ዘጋቢዎች ባደረሱን መረጃበዋግ ኽምራ ዞን ሽብርተኛው ህዋሓት የከፈተውን ወረራ ለመቀልበስ የወገን ጦር ደሀና እና ዝቋላ በተባሉ
ሁለት ግንባሮች በወራሪው ሀይል ላይ የማጥቃት እርምጃ ወስዷል። በሁለቱም ግንባሮችሽብርተኛውን እየተፋለሙ ያሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ፣ ሚሊሻዎች እና ሌሎቸ ታጣቂ ሀይሎች የጋርግንባር በመፍጠር ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ያለው የወገን ሀይል የከፈተውየሽምቅ ውጊያ ከቆዝባ ወደ ሶስት አምባ እና ሚዝርብ የሚባሉ ቦታዎች የተሻገረ ሲሆን፤ የወገን ጦር አሁንም ዉጊያዉን ቀጥሎ በቡድኑ ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ከወገን እየተወሰደባቸው ባለው ወታደራዊ እርምጃ ከፍተኛ ሰብአዊና
ቁሳዊ ኪሳራ እየገጠማቸውና ድሎችም እየተመዘገቡ ነው። የወገን ሀይል በጁንታው ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ ስሬል እና ፀመራ የሚባሉ ቦታዎች ላይ
የአገዉ ሸንጎ ታጣቂዎችም ጭምር ከሸብርተኛው ጋር በመቀናጀት የጣለትን እኩይ ዓላማ በመደገፍ
ለመመከት ቢሞክሩም፤ መቋቋም አቅቷቸው የአርሶአደሩን እህል ከአዉድማ ጭምር እየዘረፉና እየጫኑ
ለማሸሽ እየሞከሩ ሲሆን ልዩ ሃይሉ፡ ፋኖና ሚሊሻው በየአካባቢው በከፈተው የሽምቅ ጥቃት መውጫ መግቢያ አጥተዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply