Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ ሲያካሂድ የነበረው የሃሰት ትርክትና የመረጃ ስርጭት ተቀባይነት እያጣ ነው

አሸባሪው ህወሓት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ሐሰተኛ ተረኮችን በማቅረብ ሲያካሂድ የነበረው የተሳሳተና የተዛባ መረጃ ስርጭት በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት እያጣ እንደመጣ ተመላከተ።

የኢትዮጵያን እውነት በማንጸባረቅ የሚታወቁት አቶ ነአምን ዘለቀ በአልጀዚራ ኢንሳይድ ስቶሪ በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን በማብራራት ግንዛቤ ሰጥተዋል።አቶ ነአምን በሰጡት ማብራሪያ “አሸባሪው ህወሓት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ሐሰተኛ ተረኮችን በማቅረብ ሲያካሂድ የነበረው የተዛባ መረጃ ስርጭት አሁን ተቀባይነት እያጣ መጥቷል” ብለዋል።

“ለምሳሌ የፌዴራል መንግስት የተናጠል ተኩስ ማወጁን ተከትሎ አሸባሪው ቡድን የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ተገድበዋል ቢልም በተጨባጭ መረጃዎች ክሱ ወደ ራሱ ዞሯል” ነው ያሉት።ይልቁንም የኢትዮጵያ መንግስት በቢሊዮን ብር የሚቆጠር በጀት መድቦ በትግራይ ክልል የመሰረተ ልማት መልሶ ግንባታ አካሂዷል ሲሉ አመልክተዋል።

የትኛውም መንግስት የሀገሩን ሉአላዊነትና የህዝቦቹን ደህንንት የማስጠበቅ ግዴታ እንዳለበት አስታውሰው፤ መንግስት ካደረገው የተናጠል ተኩስ ማቆም በኋላ የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ሃይል በአፋርና አማራ ክልሎች ላይ ወረራ መፈጸሙን ገልጸዋል።አሸባሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የጅምላ ግድያን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙንና ንብረት ማውደሙን አስታውቀው፤ በዚህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ በትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች ሌሎች መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰውን ውድመት በማስረዳትም እንደዚህ አይነት የሽብር ተግባር ከሚፈጽም ድርጅት ጋር የትኛው መንግስት ነው ለድርድር የሚቀርበው? ሲሉ ጠይቀዋል።አሸባሪው ሕወሃት ከ5 ሚሊዮን በላይ የትግራይ ህዝብንም እጅግ አስከፊ በሆነ የጭቆና አገዛዝ ስር መጣሉን ነው አቶ ነአምን ያብራሩት።የቡድኑ አፈ ቀላጤዎች በተደጋጋሚ እንደገለጹት አሸባሪው ህወሃት ወደ ስልጣን የማይመለስ ከሆነ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ለመበታተን እንደሚሰሩ በአደባባይ መናገራቸውን አቶ ነአምን ከአልጀዚራ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውሰዋል።

Exit mobile version