ETHIO12.COM

የማስራብ ስትራቴጂ

3d rendering of stone question mark hatching out of golden egg on yellow background. Digital art. Signs and symbols. Objects and materials.

ተምበርካኪ መንግስትና ህዝብ በመፍጠር መጪው ትውልድ በሁለንተናዊ ደህነት ቀንበር ተጠምዶ ስለ ሉዓላዊት ሃገርና እድገት ያለነሱ ቡራኬ እንዳያስብ ህዝቡን በማስራብ ለተለያየ ችግር በመዳረግ ተስፋ ማስቆረጥ የተካኑበትና ጥርስ የነቀሉበት ነው።

ደሃ ሰው ስለመብት የመናገር አቅምና ሞራል ያጥረዋል ብለው ያስባሉ። ግርማ-ሞገስ እንዲሁም ተሰሚነት የለውም ብለው ያምናሉ። ድህነትና ጉስቁልና መታወቂያዎቹ ናቸውና አንገቱን ይሰብራል ይላሉ።

እውነት ነው እንደ ድህነት የከፋ ነገር የለም። ይሁንና ይህ እውነታ ግን በቁርጠኛና በጠንካራ የስራ ባህል አንገትን ቀና ማድረግና መለወጥ ይቻላል! ይህ ለግለሰብም ለሃገርም የሚሰራ ሃቅ ነው።

ምዕራባውያን በተለይ ደግሞ አሜሪካ ድሃ የሆኑ ሃገራትን ከጭቃ ጠፍጥፈው የሰሯቸው የሚመስላቸውም ለዚህ ይመስለኛል።

አሜሪካና ግብረ-አበሮቿ ስጋት የሆኑባቸውን ሃገራት ለመቅጣትና ለማዳከም ከቀጥታ ጦርነት ይልቅ በተዘዋዋሪ ማእቀብ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥርና ጉዳት የሚያደርስ እጅ ጠምዛዥ ከባድ መሳርያ መሆኑን በተግባር እና ካለፈው ተሞክሯቸው ጠንቅቀው ያውቁታል – ዜጎችን ማስራብና መንግስትን አቅም አልባ ማድረግ።

ያቋቋሟቸው የ”ተራድኦ” እና “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” እንዲሁም የሽብር መፈብረኪያ ሚዲያዎቻቸውም ይሄንኑ የስውር ጦርነት ስልቶቻቸው ማሳኪያ መሳሪያዎቻቸው ናቸው።

ሃገራትን እንደትሮይ ፈረስ እንደፈለጋቸው መጋለብ የሚያስችላቸውን ደካማ እና የሙሰኞ ጥርቅም የመንግስት መዋቅር እንዲፈጠር በትኩረት መስራትም ሌላኛው የምእራባውያንን ጥቅም ማስጠበቂያ ስትራቴጂ ነው።

ከዚህ አንፃር የሰብአዊ መብት፣ የእርዳታና የዲሞክራሲ አታሞ እና ጩኸት የድብቅ አጀንዳቸው ሽፋን ማድመቂያ ቋንቋቸው ናቸው።

ሃገራትም ሆኑ ዜጎች በኑሮ እንዲቸገሩ እና እንደሃገር/እንደዜጋ በራስ መተማመን እንዳይኖራቸው እንዲሁም ተስፋቸውን ለማጨለም መትጋት የሰርክ ተግባራቸው ነው። ይህንን እውነታ ደግሞ በተለያዩ ሃገራት በግልፅ አድርገውታል።

ተምበርካኪ መንግስትና ህዝብ በመፍጠር መጪው ትውልድ በሁለንተናዊ ደህነት ቀንበር ተጠምዶ ስለ ሉዓላዊት ሃገርና እድገት ያለነሱ ቡራኬ እንዳያስብ ህዝቡን በማስራብ ለተለያየ ችግር በመዳረግ ተስፋ ማስቆረጥ የተካኑበትና ጥርስ የነቀሉበት ነው።

ይህ ስትራቴጂ በመሰረታዊነት ለሁሉም ድሃ ሃገራት የሚሰራ ሲሆን እንደየሃገራቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና የስጋትነት መጠንና ስፋት ላይ መሰረት በማድረግ እንደ ፅዋ በተራ የሚደርስና ይህን ታሳቢ በማድረግ ሃገራቱን በተቻላቸው አጋጣሚ ሁሉ በኢኮኖሚ፣ በፓለቲካ፣ በሃይማኖት፣ በብሄር ወዘተ …ዜጎችን ብሎም መንግስትን ማተረማመስና በማባላት አለመረጋጋት መፍጠር ዋና አላማቸው ነው። አሁን ሃገራችንን ያጋጠማት ፈተናም ይሄው ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ያጋጩህና ተመልሰው ደግሞ ሽማግሌ መስለውም ቲያትር መስራታቸው ነው – በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ይሉሃል ይሄው አይደል?

ለሆዱ ያደረ እንደ ህወሃት ያለ ሃገር በቀል ባንዳ መፍጠር ደግሞ ለዓላማቸው ማሳኪያ በሰንበት ላይ እንደደብረዘይት ይቆጥሩታል።

የዚህ ሁሉ መንስኤው በዋናነት ከስጋት የሚመነጭ ጭካኔ ሲሆን የአሜረካንን ብሎም የምእራባውያንን የበላይነት ማስጠበቅ ደግሞ ዋንኛ አላማው ነው።

ዜጎች ግን ይህንን ሸፍጥ በውል በመረዳት እንደ ሃገር የሚያጋጥሙንን ዘርፈ ብዙ ጫናና ፈተና በፅናት በመቋቋም ከምእራብያን እና ከባንዳ ተፅኖ ነፃ የወጣች ነፃነቷ የተረጋገጠ ጠንካራ ሃገር መገንባት የሁሉም ሃቀኛ እና እውነተኛ ዜጋ ሃላፊነትም ግዴታም ነው!! ለዚህ መሠረቱ ደግሞ ጠንካራ አንድነት ነው።

ህዝቤ ሆይ እንዳትራብ ለመስራት ሃገርህን አድን! አንድነትህን ጠብቅ! አንድነቱን የጠበቀ ህዝብ ያሸንፋል! ነፃም ይወጣል!

ኢትዮጵያዬ የጠላሽ ይጠላ!

በላይ ባይሳ
ህዳር 16/2014 ዓ.ም

Exit mobile version