”በጎድጓዳ ሰሀን የማስቀምጠው ዳቦ እስኪሻግት እመገብ ነበር”

ንጉሥ ሱልጣን ቢን ዛይድ የነገ ዙፋን ተረካቢ ልጃቸውን አቀማጥለው አንደላቀው አውሮፓ ለትምህርት አላኩትም የልጅነት ግዜውን ሞሮኮ በትምህርት እንዲያሳልፍ ስሙን ቀይረው የንጉስ ልጅ መሆኑ እንዳይታወቅ ሸሽገው እንደማንኛውም ተማሪ የንጉሥ ልጅ ተብሎ ሳይታወቅ በጥረቱ ዛሬ እና ነገውን እንዲታገል አስተምረውታል።

”በጎድጓዳ ሰሀን የማስቀምጠው ዳቦ እስኪሻግት እመገብ ነበር” ይላሉ።

የተንደላቀቀ ሕይወት የሚጠብቃቸው መሐመድ የኑሮን ፈተና ለመወጣት በአስተናጋጅነት ተቀጥረው የዕለት ጉርሳቸውን ጎርሰው አድረዋል።

አባታቸው ሰው የሚለካው በሰው በመሆኑ ብቻ ሳይሆን መልካም ስራ ነው ስራ ነው በሚለው አቋማቸው ብቻ ሳይሆን እጅግ ታታሪ መሪ በመሆናቸው ትላንት ደሃ የነበረች አገራቸውን በምድር ያለች ገነት አድርገው ሰርተዋታል።

ልጆቻቸውንም ከነሙሉ ስብዕናቸው ለአገር ኀላፊነት አብቅተዋል።

ሱልጣን ቢን ዛይድ ልጃቸው መሐመድ ቢን ዛይድ በስራው ምክንያት ወደተለያዩ አገራት በሚሰማራት ወቅት የፓስፖርት ስሙ ተቀይሮ አልጋወራሽነቱ ሳይታወቅ በሌላ ስም ነበር።

የንጉስ ልጅ በመሆኑ ብቻ የተለየ ክብር እንዳይሰጠው ከሰው ተለይቶ እንዳይከበር።

አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ የወታደራዊ ተቋም አዛዥ በነበሩበት ወቅት የእረፍት ግዜአቸውን በታንዛኒያ እንዲያሳልፉ ተልከው በተመለሱ ግዜ ለአባታቸው ታንዛኒያ ስላዩት ድህነት አብራርተው ሲያበቁ።

አባታቸው ይሄን ሁሉ አይተህ ምን አደረክላቸው? ብለው ልጃቸውን ቢሲጠይቁ ከአልጋ ወራሹ ያገኙት መልስ ”ሰወቹ ሙስሊም አይደሉም” የሚል ቢሆንባቸው ግዜ ከተቀመጡበት ተነስተው የአባትነታቸውን እጁን ጨምድደው እጅግ በመቆጣት ”ሁላችንም የአላህ ልጆች ነን” በማለት የአላህን ትዛዝ አስተማሩት።

አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ እሳቸውም ለልጆቻቸው የአባታቸውን ስርአት እንዲከተሉ አድርገዋል።

በቅርቡም ከልጆቻቸው አንዱን በቀይ መስቀል ሰራተኝነት ውስጥ በማሳተፍ ስሙን ቀይረው ወደ ኢትዮጵያ ለስራ ልከውት ነበር።

የአገሬ ሰው እኚህ ታላቅ መሪ ሆዳቸው ስልቻ ለሚያካክለው መሪወቻችንም ሆነ ለሸንቃጦቹ ልጅን እንዲህ ነው ማሳደግ ብለው ቢመክሩልን ስቃያችን እንደዚህ ባልበዛ ነበር።

የአባታቸው ልጅ የሆኑት መሐመድ ቢን ዛይድ ያሰቡትን ሳያሳኩ የማያድሩ፣ በቃላቸው የሚፀኑ፣ ከሕዛባቸው ጋር ቁጭ ብለው በማንኛውም ግዜ የሻይ ሲኒ የሚያጋጩ ለዜጎቻቸው ልብ የቀረቡ ናቸው።

See also  የዱባ ፍሬን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

በሐይማኖት ምክኒያት ሌሎችን ማግለል ሀጥያት ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን በሐይማኖት ሰበብ ሰውን የሚለዩ እና የሚያገሉንም ይቃወማሉ።

የሰው ልጅ በመቻቻል ነው መኖር ያለበት በማለት በ2014 አንድ መቶ ሰማኒያ ሐይማኖቶች የተሳተፉበት ጉባኤ አዘጋጅተው ከመቶ አገራት በላይ ተገኝተው ግቡን መቷል።

አልጋ ወራሽ መሐመድ መሪነትን ቀለል አድርገው የተረዱ ሰው ሲሆኑ ንጉሥ ማለት የሕዝብ አገልጋይ ነው ብለው ያምናሉ።

ግዙፏ ኤምሬትስ ውቧ እና ሀብታሟ በረሀማዋ ሀገር ወደ ገነት የተቀየረችው በዲሞክራሲ ሳይሆን በስራ እና በስ-ነምግባር ውጤት ነው ብለው የሚያምኑት አልጋ ወራሹ እንግዶቻቸውን ራሳቸው ሔሊኮፍተር እያበረሩ ሲያሻቸው በመኪናቸው አገራቸውን ያስጎበኛሉ።

እኚህ ሰው እጃቸው በግብፅ ፖሎቲካ ውስጥ ረጅም ከመሆኑም በላይ በእሳቸው አጠራር አክራሪ ለሚሉት የእስልምና እንቅስቃሴ የእግር እሳት ናቸው። ያላቸውን ሀይል በሙሉ ተጠቅመው ቢያጠፏቸው ይመኛሉ።

ካሜራ የማይወዱት የጋዜጠኛ ጋጋታ የማያስከትሉት በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ እንኳን የማይገኙት ብዙ የማይናገሩት ቃለ መጠየቅ የማይመቻቸው ስፖርት የሚያዘወትሩት ለሰላት መስኪድ በመሔድ ከሕባቸው ጋር የሚያሳልፉት ስነ-ፅሁፍ ወዳዱ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ እኚህ ትጉ ሰው ስለሳቸው አንድ አንድ አገራት እጅግ አስተዋይ÷ተመራማሪ÷ ስራ የማይደክማቸው÷ታማኝ እና ቁጥብ ሲሏቸው

የኛ ጠቅላይ ሚኒስተር ደሞ ደግ እና ለጋስ ይሏቸዋል።

አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ እጅግ በጥቂቱ እኚህ ናቸው።

(ምንጭ ሸገር መቆያ እና ሌሎች ማጣቀሻወች)

walia publisher /ዋልያ መጻሕፍት እና ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ/zagol book bank

Leave a Reply