Site icon ETHIO12.COM

የንብረት መሻሻጥና ማስተላለፍ አገልግሎት ዕግድ ተነሳ

ጦረንቱን ተከትሎ ጤማ ባልሆነ የንብረት ሽያጭና ከባንክ ባንክ ልክ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውር ሳቢያ ታግዶ የነበረው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚመለስ ተገለጸ። የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች አገልግሎትም በይፋ መጀመሩን የአዲስ አበባ አስተዳደር ማስታወቁ ይታወቃል።

ተቋርጠው የሰነበቱ የንብረት ሽያጭ፤ ስጦትን የማስተላለፍና ሌሎችም አገልግሎቶች ዕግዳቸው መነሳቱ የተሰማው ዛሬ ነው። የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑ ከሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጡትን አገልግሎቶች መስጠት እንደሚጀምር አመልክቷል።

አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ ቀደም በተለመደው አግባብ፣ በተቋሙ አሰራር መሠረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላትና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የኦንላይን አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በተቋሙ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። ኢትዮ ኤፍ ኤም ድርጅቱን ገልጾ እንደዘገበው አገልግሎቱ መጀመሩን ሲጠባበቁ ለነበሩ መልካም ዜና ነው።

Exit mobile version