Site icon ETHIO12.COM

ከ33 ሺህ በላይ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተው በተገኙ ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደረዊ እርምጅ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለጹት 17 ሺህ 424 ማስጠንቀቂያ ፣14 ሺህ 285 የታሸጉ፣ 260 የተሰረዘ ንግድ ፈቃድ፣ 107 የታገደ ንግድ ፈቃድ ፣ 120 ከትስስር የወጡ ንግድ ድርጀቶች፣ አንድ 495 ከተፈቀደው የልኬት መጠን በታች በመለካት ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

በርካታ የንግድ ማህበረሰብ በቅንነት እያገለገሉ የህብረተሰቡን ችግር ለማቃለል መስራታቸውንና ከ12 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችም ሚዛኖቻቸውን ወደ ዲጅታል መቀየራቸውን ተናግረዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የተለያዩ ህግ የማሰከበር ስራ እየሰራ በመሆኑ ህብረተሰብ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ከንግዱና ከሸማቹ ማህበረሰብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ግንዛቤ በመፍጠርና ህገ-ወጥነትን የመከላከል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል፡፡ ምንጭ – (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version