Site icon ETHIO12.COM

መለስ ከመቃብር ይጮሃሉ … ” በሁዋላ ላይ አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ይልቅ ከኤርትራ ላይ መውሰድ ስለሚቀል ነው”

በሰለሞን ቦጋለ የኔነህ – ግንፍሌ – ነጻ አስተያየት

ብታምኑም ባታምኑም ይህ እውነት ነው። ይህን ስጽፍ እውነት ለመሆኑ እማኝነቴን ለመስጠት ነው። በጆሮዬ ከዛሬ በግምት ሃያ ዓመት በፊት የሰማሁት፣ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ አቶ መልስ አፍ የወጣ እውነት!! መለስ ከመቃብር ይጮሃሉ ያልኩትም ለዛው ነው። ነገሩ እንዲህ ነው።

የዩክሬን ጦርነት በአጭር የሚቆም አይደለምና ትህነግ ትኩረት እየቀነሰበት እንደሚሄድ ይታመናል። ትህነግ አሁን ባለበት ሁኔታ ቆይቶ የዩክሬንና ሩሲያ ጉዳይ እስኪቋጭ መጠበቅ አይችልም። ምንም እንኳ ስንዴና መድሃኔት በብዛት ቢገባም፣ በዚህ መቀጠሉ ለኢሳያስ የተመኙትን ሞት እየሰለሉ ከመቀምስ ውጭ አማራጭ ስለማይሆናቸው ያለችው አንድ ካርድ የቀይ ባህር ፖለቲካ ለመጫወት የወሰኑ ይመስላል። ይህም በነሱ ውሳኔ ሳይሆን ” ሞክሩት” በሚል ከላይ በተጻፈው የተጠና ዘመቻ እንደሚረዱ ጭምር ቃል ተገብቶላቸው ነው። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ ደግሞ በቀይ ባህር ላይ ሚና እንድትጫወት የአውሮፓ ህብረት ጭምር በጀትና እውቅና እየሰጡ ነው። አብይ አህመድ ወደ ለሌላት አገር ባህር ሃይል ማቋቋማቸውን ሲተጩ የነበሩ “እጅ በአፍ” ብለዋል። እናም አዲሱ ካርድና ” የአይዟችሁ ፖለቲካ” እምን ያደርስ ይሁን? ኢሳያስ እንዳሉት ” ከተጀመረ እስከ መቃብር?” ወይስ አቶ ጌታቸው እንዳሉት ትህነግ የአፍሪቃ ቀንድ መሲህ ሊሆን? ወይስ ጡንቻውን እያሳበጠ የመጣው የኢትዮጵያ መከላከያ ለጠቅላይ ይጫወታል?

ከነበረበት አገር የመምራት ማማ ወርዶ በሶስት ዓመት ውስጥ በአሻሮና ዱቄት ሌብነት ራሱን የተካው ትህነግ ኢትዮጵያንና ኤርትራን ለማጣላት ሆን ብሎ ተንኮሳ እንደፈጸመ የመንግስት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። ይህ መረጃ ስትሰሙ “በአሻሮ ሌብነት የተሰማራ ሃይል በምን አቅሙ ይህን ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ ወደ ልቡናችሁ ከመጣ ትክክል ነው። አግባብነት ያለው ጥያቄም ነው። ምላሽም ያሻዋል።

በ1983 መንግስት የሆነው የተገንጣይ ቡድን መላ ኢትዮጵያ ላይ የጎሳ ፖለቲካ ዲዲቲ እየረጨ አሰብን ለኤርትራ ሲያስረክብ ከውስጡ ቅር ያላቸው “አሰብን ለምን?” ሲሉ መለስ ቃለ በቃል የመለሱትና ያብራሩት ” በሁዋላ ላይ አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ይልቅ ከኤርትራ ላይ መውሰድ ስለሚቀል ነው” ብለው ነበር። የሰማሁትን ከላይ ያስታወቅኩት ይህንኑ ነው።

እናም ዛሬ ላይ ” አሰብን አካለን” የሚለው ቆሞ ቀር ሃሳብ ጎልቶ የሚሰማው የትህነግ ዋንኛ ዓላማ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ኤርትራና ሕዝቧን ከጌቶቻቸው ጋር ሆነው በማዕቀብ በማድቀቅ ጉልበት ፈጥረው ዓላማቸውን ለማሳካት አብዛኛውን መንገድ ተጉዘው ስለነበር ነው። ይህ በአደባባይ የሚነገር ትግራይን “ታላቋ” በተቃራኒው ኤርትራን ” ተረት” የማድረጉ ስሌት አካል ነው።

ትህነግ አገር ምድሩን ተዋጊ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ በክህደት አርዶና መሳሪያውን ገፎ ሲናኝ ኤርትራ ተንደርድራ የገባችው በበቂ ምክንያት ስለመሆኑ በርካቶች ከፖለቲካ ሂሳብ አንጻር የሚስማሙት ለዚህ ነው። በአሸባሪ ፈልፋይነት ያለ ስራዋ ተፈርጃ በማዕቀብ የዛለችው፣ አዛውንት ሳይቀር በሽሽት የራቋት ኤርትራ የአዞ ቆዳ ለብሳ፣ ሁሉንም ችላ የሞቷን ናፋቂዎች ሞት ለማየት በቅታለች። “የዓይናችሁ ቀለም” ተብለው ያላቸውን ተነጠቀው በየበረሃው እንደ ቸው የተበተኑት የኤርትራ ተወላጆች ” ነጻነት” ብቻ ብለው እንዲመርጡ ተደርገው ወይም ፈልገው ሲሄዱ ” መቼ ቅኝ ገዛናቸው፣ አዲስ አበባ ነጋዴዎቹ፣ ባለሃብቶቹ እነሱ …” በሚል በርካቶች ቢያዝኑባቸውም የኢትዮጵያ ውድ ልጆች በክህደት ሲታረዱ በመድረሳቸው የቅርሾው ግድግዳ ተደረመሰ። ድሮም ፌክ የነበረው “ንጻነት” አደባባይ ተሰቀለ። ያንን ሁሉ ተዓመር ህዝብ ወዶና ፈቅዶ ሲከውን ታየ። ትህነግ እንደዛ በሚያምረው የፍቅር ቀለም ውስጥ ድኝ አጭሶ ….

ወደ መነሻዬ ስመለስ አሰብ የትህነግ አጀንዳ የሆነው ዛሬ አይደለም። የቀይ ባህር አፋር እያለ ሲያደራጅ፣ ከዋናው የኢትዮጵያ አፋሮች ለይቶ ሲያያቸው የነበረውም ለዚሁ ዓላማው ነበር። አፋር ግመሉ ሳይቀር ኢትዮጵያን ስለሚያውቅ በአሰብ ደልሎ ከባንዲራና ኢትዮጵያ መለየት ስለሚከብድ የቀይ ባህር አፋሮችን ሲያደራጅና ግብር ሲያስገባ የኖረው ትህነግ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪሰለቸው መንግስት ሆኖ እንደሚቆይ ያምን ስለነበር፣ ኤርትራ ሟምታ ስትፈርስ በሶምሶማ አሰብንና ደጋማውን ክፍል ሊረከብ ነበር ቀን የሚጠብቀው።



በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ የሞት የፈጠራ አዋጅ ከማወጅ ጀመሮ ” እሱም አርፈ፣ እኛም አረፍን፣ ኤርትራም ተገላገልች” የሚል ርዕሰ አነቀጽ አዘጋጅተው የኢሳያስን መውደቅ ሲተባበቁ የነበሩ እንዳሉም በርካታ ምስክሮች ሲናገሩ ተሰምቷል። ሁሉም ሳይሆን ቀርቶ፣ ዛሬ ላይ ትህነግ ኤርትራን ለመግጠም ሙሉ በሙሉ መዘጋጀቱ፣ በመልሶ ማጥቃት አብረቅራቂ ድል መቀዳጀቱ በወዳጆቹ እየተነገረ ነው። ከዛው ጎን ለጎን ” ሴራው ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማናከስ ነው። ይህ አይሳካም” የሚል ምላሽ ከኢትዮጵያ ተሰምቷል። በዚሁ ፍጥነት ውስጥ ነገሩ የተጠናና በድርጅት የሚሰራ ስራ እንደሆነ አመላካች ጉዳዮች ተሰምተዋል። እናም ትህነግ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንዲጣሉ የማድረግ አቅሙ የሚመነቸው እንደ ልምሻ ከተብረከረከውና ከተሽመደመደው አቅሙ ውስጥ ሳይሆን በሌላ መነገድ ነው። በድርጅትና በሂሳብ!! እንዴት?

የዘመቻው መሪዎች እነማን ናቸው?

ትህነግ “ኤርትራ ወረርችኝ” ሲል መናገር ከጀመረ ቆይቷል። ትግራይ በአማራና በኤርትራ መካከል ተጣብቃና ታንቃ እንዳለች፣ ከዚህ ማነቆ ለመውጣት የሚበጀውን አማራጭ መከተል እንዳለባቸው ለአለም በይፋ አስታውቀዋል። ይሳካ አይሳካ ሌላ ጉዳይ ሆኖ፣ ወልቃይትን ዳግም ለመረከብም ዛቻው መሰማት ከጀመረ ቆይቷል። ከሁሉም ለጊዜው የፈጠነው ግን ኤርትራን የመግጠሙ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ በኩል የትህነግ የሶስተኛ ዙር ዕቅድ ስለታወቀ መከላከያና ሁሉም ዓይነት የጸጥታ መዋቅር በተጠንቀቅ እንዲቆም ታዟል። ኤርትራን መግጠሙ ቅድሚያ የሆነው ለምንድን ነው?

ሮይተርስ በትግራይ ያሉ ዕርዳታ ሰጪዎች የላኩትን ሚሞ – የውስጥ መጻጻፊያ ጉማጅ ወረቀትና የተባበሩት መንግስታትን የዘርፉ ሰዎች ሪፖርት ጠቅሶ የኤርትራ ወታደሮች ህጻን መግደላቸውን፣ ነጹሃንን በጅምላ ማቁሰሉን፣ የሰላማዊ ተፈናቃዮች መጠለያ ማፍረሱን አስታውቋል። ይህ ልክ ኢትዮጵያ ላይ በደቦ እንደተደረገው የተጠናና የተደራጀ የሚዲያ ዘመቻ ተመሳሳይ አካሄድ የተከተለና ቀጣይነት ያለው ነው። ገና ቪዲዮ፣ ኦዲዮና ሌላ መረጃ ይከተላል።

ይህ ሲሆን ኢሳያስ አፉውርቂን ለመብላት ያሰፈሰፉት፣ ቀይ ባህር ለምን የሩሲያና ቻይና ሆነ በሚል ከቀድሞው በላይ ጥላቻቸው የከረረባቸው የአሜሪካ ታዛዦች ኤርትራ ላይ ዘመቻ አፋፍመው የሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲገባ፣ ተጭማሪ ዕቀብ እንዲደረግ፣ በህግና በጫና ያዛሏት ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ድምጽ እንድትሰጥ የመጫን፣ የማስፈራራትና ማዕቀብ በማጠናከር የማስገደድ ሂደት ውስጥ ለመግባት ዕቅድ እንዳለ ለትልቁ ቤት ቅርበት ያላቸው የአፍሪካ ልጆች ሹክ እያሉ ነው። “የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ እያለቁ ለኢሳያስ በማድላት የዓለምን ውሳኔ አይቀበልም” በሚል ዘመቻ ሊከፈት እንደሚችልም እየገለጹ ነው።

ትህነግ የኢትዮጵያን ካባ ለብሶ ያልቻለውን ኢሳያስ ዛሬ አሻሮና የልመና ኮዳ ተሸክሞ ለመግጠም የከጀለበት ሚስጢር እዚህ ጋር እንደሚገኝ የሚናገሩ፣ እግረ መንገዳቸውን አንድ ቀጭን ግን ሊሆን የሚችል የፈጠነ ኦፕሬሽን ሊኖር እንደሚችል ይገምታሉ።

አማራ ክልል ተረጭተው የነበሩና በአሁኑ አጠራር ” አስመሳይ አማራ” የሚባሉትን በድነገተኛ የህግ ማስከበር ዘመቻ መለቀማቸው የቀጣይ ዘመቻ አመላካች እንደሆነ ነው እየተጠቆመ ያለው። ኤርትራም የዚሁ ኦፕሬሽን አካል ልትሆን እንደምትችል ከግምት በላይ እየተገለጸ ነው። የአገር መከላከያም ሌት ተቀን የጋራ ልምምዱን ተያይዞታል። አየር ሃይል ” እኔን አያድርገኝ” እያለ ነው። የጦር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ” በአጭር ጊዜ ፣ በአንስተኛ መስዋዕት ግዳጁን የሚወጣ ሃይል ገንበተናል” ሲሉ እያስታወቁ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ውሏቸው ወታደሮቻቸው ጋር ነው። ይህ ሁሉ ተዳምሮ ቅጽበታዊ ለአቤቱታ የማይመች እርምጃ ሊኖር እንደሚችል አመካች እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። ትህነግም እድሜ ገደቡን አንስቶ አገሩን ሁሉ ወታደር አድርጓል። “ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” በሚል መነሳቱን እያስታወቀ ነው። ምንም ሆነ ምን አንድ መስማሚያ አለ።

የዩክሬን ጦርነት በአጭር የሚቆም አይደለምና ትህነግ ትኩረት እየቀነሰበት እንደሚሄድ ይታመናል። ትህነግ አሁን ባለበት ሁኔታ ቆይቶ የዩክሬንና ሩሲያ ጉዳይ እስኪቋጭ መጠበቅ አይችልም። ምንም እንኳ ስንዴና መድሃኔት በብዛት ቢገባም፣ በዚህ መቀጠሉ ለኢሳያስ የተመኙትን ሞት እየሰለሉ ከመቀምስ ውጭ አማራጭ ስለማይሆናቸው ያለችው አንድ ካርድ የቀይ ባህር ፖለቲካ ለመጫወት የወሰኑ ይመስላል። ይህም በነሱ ውሳኔ ሳይሆን ” ሞክሩት” በሚል ከላይ በተጻፈው የተጠና ዘመቻ እንደሚረዱ ጭምር ቃል ተገብቶላቸው ነው። በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ ደግሞ በቀይ ባህር ላይ ሚና እንድትጫወት የአውሮፓ ህብረት ጭምር በጀትና እውቅና እየሰጡ ነው። አብይ አህመድ ወደ ለሌላት አገር ባህር ሃይል ማቋቋማቸውን ሲተጩ የነበሩ “እጅ በአፍ” ብለዋል። እናም አዲሱ ካርድና ” የአይዟችሁ ፖለቲካ” እምን ያደርስ ይሁን? ኢሳያስ እንዳሉት ” ከተጀመረ እስከ መቃብር?” ወይስ አቶ ጌታቸው እንዳሉት ትህነግ የአፍሪቃ ቀንድ መሲህ ሊሆን? ወይስ ጡንቻውን እያሳበጠ የመጣው የኢትዮጵያ መከላከያ ለጠቅላይ ይጫወታል?

መለስ ከመቃብር ” ቃሌን ጠብቁ” እያሉ ነው። አሰብን የታላቋ ትግራይ በማድረግ የሰማእታትን ህልም ዕውን አድርጉ ሲሉ እየጮሁ ነው። ኢሳያስም ጩኸቱ ይሰማሉ። አብይም የዚህ ጩኸት መስሚያ ጆሮ አላቸው። በአራት ዓመት ዱቄት የሆነውና ከአፍሪቃ ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የገነባው ትህነግ … ልሶ !!

በሰለሞን ቦጋለ የኔነህ – ግንፍሌ


Exit mobile version