ETHIO12.COM

ጎረቤት አልባነት “ጎንደርና አስመራ መሄድን ህልም ያደረገ የ47 ዓመታት ፖለቲካ”

ኦባሳንጆ በአይናቸው ብቻ ማየት አቅቷቸው በቫይናኩላር ተደግፈው በጎበኙት የባሌ የስንዴ ነዶ ላይ ቆመው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአርባ ሰባት ዓመቱን ፖለቲካ ” ጎንደርና አስመራ መሄድን ህልም ያደረግ” ሲሉ የትህራይ ሕዝብም ሆነ ልሂቃን በተለይም ወጣቱ እንዲጠይቅ አሳሰቡ። እግር ጎታችሁ ቢበዛም መንግስት በገባው ቃል መሰረት ሁሉንም አከናውኖ፣ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ እንደሚጀምርም አመልክተዋል።

አስራ ሰባት ዓመት ትህነግ ጫካ በነበረበት ወቅት በአስር ሺህ ሰዎች የሚቆጠሩ መሞታቸውን፣ ከመንግስትነት ከተነሱም በሁዋላ አሁንም ሰዎች መሞታቸውን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” የ47 ዓመቱ ፖለቲካ አስመራና ጎንደር [ ጎረቤት አልባ] መርገጥን ህልም ካደረገ ቆሞ ምን አተረፍን በሚል ማሰብ ይገባል” ሲሉ በደፈናው ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል።ተከፍለ የሚባለው መስዋዕትነት ስለምን ፍሬው ወዳጅና ጎረቤት አልባ ሊያደርግ እንደቻለ መመርመር የወቅቱ ጥያቄ እንደሆነ ሲያነሱ “ዛሬም አማራን ኦሮሞን፣ጉራጌን፣ ወላይታን መጥላት አንድ መንደር መግባት የማይቻልበት ጊዜን መፍጠር ነው” ሲሉ አሁን የተጀመረውን አካሄድ መደገፍና ማገዝ እንደሚገባ አመልክተዋል።

በስፋት የተንጣለለውን የስንዴ ማሳ እያሳዩ ” ኦሮሚያ ሳይሆን ባሌ ኢትዮጵያን ካልቀለበ፣ እንዴት ነው ስንዴ ከዩክሬን … የሚባለው” በማለት ኢትዮጵያዊያን ” ረሃብ፣ ልመና፣ ውርደት በቃን” በማለት ስንዴ ማምረት ልማድ እንዲሆን ተጋግዞ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

የጎጥና የዘር ፖለቲካን በስሙ ሳይጠሩ ውጤቱን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስራት ሲጀመር ጎታቹ ብዙ እንደሆነ አንስተዋል። በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ መንግስታት ሲጎተቱ እንደኖሩ ያስታወቁት አብይ አሕመድ፣ ከመጎተትና መሪዎቹ ከጎታቾቹ ጋር ሲታገሉ ጊዜ እንዲያባክኑ አድርጎ በሁዋላ ከመውቀስ፣ እያገዙ ወደፊት በመሄድ ጊዚያቸው ሲያልቅ ስልታኑንን መረከብና መተጀመረው ማስቀጠል እንደሚበጅ ጠቁመዋል።


ኦባሳንጆ [ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ነች] ሲሉ መመስከራቸው ብስጭት ፈጠረ

“ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘው ስራ አበረታችና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር ነው” ሲሉ ምስክረነታቸውን እዛው ማሳው ላይ ሆነው የሰጡትይ አደራዳሪ፣ “ይህን ማለታቸው ከድርድሩ ጋር ምን ያገናኘዋል” በሚል ቁጣቸውን የገለጹባቸው ድምጻቸውን ያሰሙት ወዲያው ነው።


የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን አገሪቱን የመሩ መሪዎች ኢትዮጵያን እንደማያቁ ” ኢትዮጵያን አናውቃትም” በማለት ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ “ብናውቃትማ ኖሮ ስንዴ አንለምንም ነበር” ሲሉ ሁሉም የቁጭት መንፈስ ውስጥ እንዲገባ ጠይቀዋል።

“ስንዴ መለመን በቃን” ሲል በተደጋጋሚ የሚሰሙትና ወደ ስልጣን በገቡ ማግስት እሳት ከማጥፋቱ ጎን ለጎን ስንዴ ላይ ትኩርት የሰጡት አብይ አህመድ፣ መስቀል አደባባይን፣ ዩኒቲ መናፈሻ ለመገናባት ሲጀመር የነበረውን ተቃውሞና ውግዘት እንደ ማሳያ በመጠቆም ” ማንም ምንም ቢል ያሰብነውን ከማድረግና ሰርቶ ከማሳየት የሚያስቆመን የለም” ብለዋል።

አሁን የተጀመሩትን በአማራ፣ በደቡብና ኦሮሚያ የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እንደሚያልቁ ያስታወቁት አብይ አሕመድ፣ ስንዴ ወደ ውጭ እንደሚላክና ስንዴ ታሪክ እንደሚሆን በልበ ሙሉነት ገልጸዋል። “ኢትዮጵያን በልኳ ለማበልጸግ ስለምንሰራ የሚያስቆመን ነገር የለም” ብለዋል።


Africa has what it takes to feed itself, ADB chief tells G7 development ministers Ethiopia’s wheat production skyrockets to 2.6 million metric tons, plans to export to Kenya, Djibouti in 2023


“የጀመርነውን ፕሮጀክት ሁሉ ጨርሰን፣ ስንዴ ኤክስፖርት አድርገን በድል ላይ ቆመን አብረን እንነጋገራለን” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የቀድሞ የናይጀሪያ መሪና የአፍሪቃ ተሿሚው ኦባሳንጆ ባዩት የስንዴ ማሳ መገረማቸውን በይፋ ማስታወቃቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የአፍሪካ ልማት ባንክና ዓለም ባንክ የስንዴ ማሳ ላይ እየተሰራ ያለውን አይተው መደመማቸውን፣ እገዛ ለማድረግ ሙሉ ፈቃደኛ መሆናቸውን፣ ተግባሩ ለአፍሪካ አገራት ምሳሌ እንደሚሆን ማስታወቃቸውን አይዘነጋም።


Exit mobile version