Site icon ETHIO12.COM

የፕሪቶሪያው ስምምነት ትርጉም በ360 ደርዝ ለዞረባችሁ

….አዎ ፖለቲካ ያለ ትንታኔ የእውር ድንብር ጉዞ ነው የሚሆነው። ሁልጊዜ ማወቅ ያለብህ ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ያለው ፍላጎት ሁሉ የአንተ ብቻ አለመሆኑን ነው። ብዙ ፍላጎቶች፣ ብዙ ውጣ ውረዶች ባለባት ሐገር ላይ ተቀምጠህ እኔን ብቻ ስሙኝ ማለት አንድም ፖለቲካን አለመረዳት አለፍ ሲልም ቂልነት ነው። ይልቁንስ የሌሎቹን ፍላጎት ተረድተህ ከአንተ ፍላጎት ጋር ማቀራረብ እና ማስማማት ነው ፖለቲካ።


በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን ያለብህ በራስህ አቅም ነው። አቅም አልባ ከሆንክ ማንም የማይፈልግህ ውዳቂ ትሆናለህ። የራስህን አቅም በሚገባ ከገመገምክ በኋላ ማን ነው አጋሬ ወደሚለው ትዞራለህ። አጋርህ ከጠላትህ እና ከአንተ ጋር ያለውን መስተጋብር ትገመግማለህ። አጋርህ ከጠላትህ ይልቅ አንተን ለምን እንደመረጠ አንተም ለምን እንደመረጥከው በተጨባጭ መረጃ ላይ ተንተርሰህ መገምገም የአንተ ድርሻ ነው። አንተም ለምን አጋርህ እንዳደረከው ማወቅ ይኖርብሃል። ታማኝ አጋር እንደምትሻ ሁሉ ለአጋርህ ታማኝ መሆንም የግድ ነው። እዚህም እዚያም የምትዘል ከሆነ ለአጋርነት አትመጥንም ብሎ ሜዳ ላይ ያሰጣሃል

አንዳንዴ የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው የሚለው ብሂል ገዥ ነው። ዘላቂ ጠላትም ሆነ ዘላቂ ወዳጅ እንደሌለ ተረድተህ ግምገማህን በየጊዜው መተንተን ግን ከአንተ የሚጠበቅ ነው። ያልተተነተነ ፖለቲካ ስሜት እንጅ ስሌት አይደለም። ብዙዎች ፖለቲካ ሳይተነትኑ ይጀምሩና መካከሉ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይጠፋባቸዋል። መስቀለኛ መንገድ ላይ የጠፋ ህጻን ይሆናሉ እያልኩህ ነው። ወደ የትም ሄደህ የማትፈልገው እንደማለት ነው። አዎ ፖለቲካ ያለ ትንታኔ የእውር ድንብር ጉዞ ነው የሚሆነው። ሁልጊዜ ማወቅ ያለብህ ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ያለው ፍላጎት ሁሉ የአንተ ብቻ አለመሆኑን ነው። ብዙ ፍላጎቶች፣ ብዙ ውጣ ውረዶች ባለባት ሐገር ላይ ተቀምጠህ እኔን ብቻ ስሙኝ ማለት አንድም ፖለቲካን አለመረዳት አለፍ ሲልም ቂልነት ነው። ይልቁንስ የሌሎቹን ፍላጎት ተረድተህ ከአንተ ፍላጎት ጋር ማቀራረብ እና ማስማማት ነው ፖለቲካ።

ሁልጊዜም የፖለቲካውን አካሄድ ማንበብ እና መረዳት ከአንድ የፖለቲካ ኃይል የሚጠበቅ ነው። አንዳንዴ የማትችለው ኃይል ከፊት ለፊትህ ከቆመ ጊዜ መግዛት ብልህነት እንጅ ፍርሃት አይደለም። አባቶችህ “ቅዝቅዝም እና ክፉ ቀንን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ብልህነት ነው” የሚሉት ወደው አይደለም። ከሚምዘገዘግ ሚሳኤል ጋር መላተም ሞኝነት እንጅ ብልሃት ሊሆን አይችልም። ሲቻልህ ኃይል ማካበት፣ ካልተቻለህ ግን ኃይል ማባከን አይገባህም። ጠላትህ እንዲዳከም መጠበቅም የፖለቲካ ብልጠት ነው። መጮህ የቁራ ተፈጥሮ ነው። በሆነ ባልሆነው አትጩህ። በሆነ ባልሆነው የምትጮህ ከሆነ በወሳኝ ጊዜ የምታደርገውን ጩኸትህን የሚሰማህ አይኖርም።

በቃ ይኸው ነው…!

ጋሻው መርሻ ፌስ ቡክ የተወሰደ

Exit mobile version