Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የ32 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

 ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶችን አዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ተፈራርመዋል:: ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪኔ ኮሎና ተፈራርመዋል፡፡

ድጋፉ በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት እና የአርሶ አደሮችን የምግብ ዋስትና በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ እንደሚውል ተገልጿል።

በሁለት ምዕራፍ የሚደረገው ድጋፉም በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ በመገንባት 12 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በግጭት ምክንያት ተጎጂ የሆኑ ሴቶችን ጨምሮ 400 ሺሕ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትናቸውን በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተጠቅሷል።

በዚህም የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ 28 ሚሊየን ዮሮ እንዲሁም አውሮፓ ህብረት ደግሞ የ4 ሚሊየን ዮሮ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version