Site icon ETHIO12.COM

ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የአፋር ህዝብ ሱልጣን ሆኑ

በአፋር ሱልጣኔት የአውሳ ሱልጣኔት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ 15ኛው የአፋር ሱልጣን በመሆን ንግስናቸውን ተረክበዋል። በአፋር ሱልጣኔት ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የንግስና ስነስርዓታቸው ተካሂዷል። ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ የሱልጣን አሊሚራሕ ልጅ ሲሆኑ ፥ 15ኛ ሱልጣን በመሆን የሱልጣንነት ሹመታቸውን ተረክበዋል።

በአለ ሲመቱ በአውሳ ሱስለጣኔት መናገሻ በሆነችው በአይሳኢታ ከተማ ነው የተካሄደው። በበዓለ ሲመቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ,የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች, በጀቡቲና ኤርትራ የሚገኙ የአፋር ማህበረሰብ ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት አካላት እና የተለያዩ አምባሳደሮችም ተገኝተዋል።

የንግስናው ስነ ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዴሞክራሲ ስርዓት አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን መሰረት ለማስያዝ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባደረጉት ንግግር ወንድማማችነትንና መቻቻልን የሚያጎለብቱ ባህሎችን መንከባከብ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ መላው ኢትዮጵያዊያን የሚያጋጥሙንን ችግሮች በፅናት ማለፍ እንችላለን ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የጋራ ባህል እና እሴቶቻችንን መንከባከብ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የጂቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትርን በመወከል በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጂቡቲ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአፋር ሱልጣኔት ከዓዳል ሱልጣኔት በኋላ የአፋር ህዝብ አንድነትና ወንድማማችነት በማስቀጠል ቁልፍ ሚና አየተጫወቱ የመጣ ሱልጣኔት እንደሆነም ነው የሚገለፀው። ንግስናቸውን የተረከቡት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ስለ ቀጣይ የስልጣን ዘመናቸው ንግግር ማድረጋቸውን ኦቢኤን ዘግቧል

Exit mobile version