የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ745 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፈቀደ

የዓለምን ባንክ ለኢትዮጵያ ለጤና አገልግሎትና ለጎርፍ አደጋ መከላከል ሥራዎች የሚውል የ745 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፈቀደ።

ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በኮቪድ 19፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ይህ ቀውስ ተገቢ የሆነ የጤና አገልግሎት እንዳይሰጥ ከማድረጉም በላይ ላለፉት አስርት አመታት ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ባስመዘገበችውን መሻሻል ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች እስከ 24 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በቂ የሆነ የጤና አገልግሎት እያገኘ እንዳልሆነ የጠቀሰው ባንኩ፤ የጎርፍ አደጋም በተመሳሳይ እስከ 300 ሺህ ሠዎችን ማፈናቀሉን 288 ሞት ማስከተሉንም አብራርቷል።

ባንኩ ባደረገው ጥናትም በጎርፍ አደጋ እስከ 358 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሷል።

ከእነዚህ ጉዳቶች በመነሳት የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ችግሩን ለመቋቋም ያግዝ ዘንድ ሁለት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁን አስታውቋል።

በመጀመሪያው ፕሮጀክቱ የአንደኛ ደረጃ የጤና ተቋማት አገልግሎትን ለማጠናከር ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር (አይዲኤ) 400 ሚሊዮን ዶላር፣ ከዓለም አቀፉ ፋይናንስ ፋሲሊቲ (ጂኤፍኤፍ) 45 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታውቋል።

ሀለተኛው ለጎርፍ አደጋ መከላከል ሥራ የሚውልና ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር (አይዲኤ) የተገኘ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መፈቀዱን ባንኩ ገልጿል። ENA

See also       የስኳድ ሰነድ - ፩

Leave a Reply