ከግብርና ታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ገቢዎች እስከ 21 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ዝርዝር ይፋ አደረገ

ከግብር እና ታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ለተጨባጭ መረጃ አቅራቢ ስለሚሰጥ የሽልማት መጠን የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። በዚሁ ይፋ በሆነውና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ይፋ የሆነው የሽልማት ዝርዝር ጠቋሚዎችን የሚያበረታታ እንደሆነ ይገመታል።

በተጨባጭ መረጃው መሰረት የተገኘው ፍሬ ግብር/ታክስ እና ወለድ መጠን ከሚያስገኘው የሽልማት መቶኛ ጋር አቀናጅቶ ገቢዎች ከዚህ በታች በዝርዝር አስፍሯል። መረጃው ግብር ደባቂዎች ሂሳቡን ለሚሰሩላቸው ባለሙያዎች ከሚሰጠው ሽልማት በላይ ካልከፈሉ ሚስጥራቸው ይፋ ሊሆን ስለሚችል የሚፈለግባቸውን በአግባቡ መክፈሉ እንደሚቀላቸው መረጃው ያሳያል።

1. ከዝቅተኛው መጠን እስከ 60,000,000 (ስድሳ ሚሊዮን ብር) ከሆነ 5 %

2. ከብር 60,000,001 (ስድሳ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 70,000,000 (ሰባ ሚሊዮን) ከሆነ 6%

3. ከብር 70,000,001 (ሰባ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 80,000,000 (ሰማኒያ ሚሊዮን) ከሆነ 7%

4. ከብር 80,000,001 (ሰማኒያ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 90,000,000 (ዘጠና ሚሊዮን) ከሆነ 8%

5. ከብር 90,000,001 (ዘጠኝ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 100,000,000 (አንድ መቶ ሚሊዮን) ከሆነ 9%

6. ከብር 100,000,001 (አንድ መቶ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 110,000,000 (አንድ መቶ አስር ሚሊዮን) ከሆነ 10%

7. ከብር 110,000,001 (አንድ መቶ አስር ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 120,000,000 (አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን) ከሆነ 11%

8. ከብር 120,000,001 (አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 130,000,000 (አንድ መቶ ሰላሳ ሚሊዮን) ከሆነ 12%

9. ከብር 130,000,001 (አንድ መቶ ሰላሳ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 140,000,000 (አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን) ከሆነ 13%

10. ከብር 140,000,001 (አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን አንድ) እስከ ብር 150,000,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ከሆነ 14%

11. ከብር 150,000,001 (አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) በላይ ከሆነ 14% ሆኖ በማንኛውም ሁኔታ ለተሸላሚ የሚከፈለው የወሮታ ክፍያ ከብር 30,000,000 (ሰላሳ ሚሊዮን) መብለጥ የለበትም፤

የሽልማት ክፍያ ግብር የሚከፈልበት ስለመሆኑ

በዚህ መመሪያ መሰረት የሚከፈል ሽልማት በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/08 መሰረት ግብር ይከፈልበታል፡፡ ስለሆነም ሽልማት የሚከፍል የሚኒስቴሩ የሥራ ክፍል ክፍያ ሲፈጽም ግብሩን ቀንሶ ማስቀረት አለበት፡፡

See also  ሃብትና የገቢ ምንጭ "አናስመዘግብም" ያሉ 62 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች በህግ ሊጠየቁ ነው

ሽልማት ተመላሽ ስለማድረግ

ሚኒስቴሩ በማናቸውም ሁኔታ በስህተት ወይም ያለአግባብ የከፈለውን ሽልማት እንዲመለስ ያደርጋል፡፡

Leave a Reply