Site icon ETHIO12.COM

ተሃድሶ ኮሚሽን ትጥቅ ከፈቱ የሸኔ ታጣቂዎች ጋር ተወያየ

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የሰላም ጥሪን ተቀብለው ትጥቅ ከፈቱ እና ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ከወሰኑ የሸኔ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋር መወያየቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ገለጹ።

ታጣቂዎቹ መሣሪያ በማስቀመጥ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሰው በሀገሪቱ ሰላም፣ ዴሞክራሲ ግንባታ እና ልማት ውስጥ ለመሳተፍ የወሰኑ መሆናቸውን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት አስታውቀዋል።

እነዚህ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮሚሽኑ ብሔራዊ የተሃድሶ ፕሮግራም ውስጥ ለመሳተፍ እንደተስማሙም የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ “ሌሎችም የእነዚህን ታጣቂዎች ፈለግ እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። OBN

Exit mobile version