Site icon ETHIO12.COM

የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ

(ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን ‘አቶ አበበ’ እና ‘አቶ ከበደ’ የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን)

አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው መምጣት ጀመረ፡፡ ሕመሙ ሲብስባቸው ጎረቤታቸውን በማማከር ወደ ባሕል መድኃኒት ቤት ያመራሉ፡፡

ባለመድሃኒቱም የሚቀባ የባሕል መድሃኒት ይሰጣቸውና እንደሚያድናቸው አረጋግጦላቸው ይሸኛቸዋል፡፡ አቶ አበበ የተሰጣቸውን መድኃኒት እንደተባሉት መቀባት ይጀምራሉ፡፡ በሦሥተኛው ቀን ኪንታሮቱ ይፈነዳና መግል ማውጣት ጀመረ፡፡ በአራተኛው ቀን አቶ አበበ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ተደናግጠው ወደ ሆስፒታል ያመጧቸዋል፡፡

ሆስፒታል ሲደርሱ የአቶ አበበ የልብ ምት በጣም ይፈጥናል፡፡ የደም ግፊታቸው በጣም ወርዷል፡፡ በድንገተኛ ክፍል ያሉ የጤና ባለሙያዎች በመረባረብ በመርፌ መድሐኒቶችን ፣ ግልኮስ፣ ፈሳሻ ንጥረ ነገርና የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያደርጉላቸውም ቁስሉ ኢንፌክሽን ፈጥሮ በደም ውስጥ ስለተሰራጨ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ከዚህም የተነሳ አቶ አበበ ጽኑ ሕሙማን ክፍል በአስቸኳይ እንዲገቡ ተደርጎ የተለያዩ የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

ሌላኛው ታካሚ አቶ ከበደ ናቸው፡፡ እድሜያቸው 58 ሲሆን የባሕርዳር ኗሪ ናቸው፡፡ ከ5 ዓመት በፊት ጀምሮ የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) ጀምሯቸው በየጊዜው እየተባባሰቸው ይሄዳል፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ታዋቂ የባሕል ሕክምና አዋቂ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ባለመድኃኒቱም ከመረመራቸው በኋላ በመርፌ የሚወጋ መድኃኒት አዘዘላቸውና ያበጠው ኪንታሮት ላይ መድኃኒቱን በመርፌ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እንደሚድን ነግሯቸው ይሰነባበታሉ፡፡

ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ ኪንታሮቱ እብጠቱ እየጨመረ ይሄድና በሳምንቱ ይፈነዳል፡፡ ከዛም ተመልሰው ሲሄዱ ባለመድኃኒቱ እየቆየ እንደሚድንላቸው ነግሮ ይሸኛቸዋል፡፡ ይሁንና ቁስሉ ከመዳን ይልቅ እየሰፋ፣ መግል እያመንጨና እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ የዚህን ጊዜ ቁስሉን በጨውና በውሃ እያጠቡ በቤት ይቆያሉ፡፡ ቁስሉ እየሰፋ በመሄዱ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ከበደ ሰገራ መቆጣጠር ያቅታቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ዳይፐር መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ የሕመሙ ደረጃ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ አቶ ከበደ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተልከው በተደረገላቸው ምርመራ የፊንጢጣ መቆጣጠሪያ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ በመጎዳታቸው በሆዳቸው በኩል የሰገራ መውጫ (Permanent colostomy) እንዲሠራላቸው ተወሰነ፡፡

ከነዚህና መሰል ብዙ ታሪኮች እንደምንረዳው ለኪንታሮት ተብለው ከትልልቅ ከተማ እስከ ገጠር የሚሰራጩ የባሕል መድኃኒቶች በኅብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ነው፡፡

የባሕል ሕክምና በአግባቡ ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ቢዛመድ ለማኅበረሰባችን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ቢታመንም የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻች ይህ ዓይነቱ የኪንታሮት የባሕል ሕክምና ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመናገር ያስደፍረናል፡፡

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids) ምንድነው?

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)፦በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም ከ45 – 65 ዓመት ባሉት ሰዎች ላይ በብዛት ይከሰታል

የኪንታሮት በሽታ በዋናነት በሁለት (types) ይከፈላል

፩. ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ክፍል ላይ የከሰት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመምም (Pain) ያስከትላል፡፡

፪. ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመም አይኖረውም

ይህ የኪንታሮት ዓይነት 4 ደረጃዎች (grades) አሉት።

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

ምልክቶች (clinical features)

የኪንታሮት መዘዞቹ (complications)

ኪንታሮት እንዴት ይታከማል?

በመጀመሪያ ሕመሙ ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሕመም ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ ለመታከም ፍርሃትን/ሐፍረትን ማሰወገድ ይጠበቅበታል፡፡

፩. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ

፪. ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድ

፫. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ 20- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ ወይም ሦሥቴ መዘፍዘፍ (በበረዶም ሊሆን ይችላል)

፬. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹሕ ውሃ መታጠብ

፭. ሻካራ የመፀዳጃ ወረቀቶችን አለመጠቀም

፮. የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት

፯. የሚቀቡ የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም

አብዛኛውን ጊዜ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ሕመሙ ሊሻሻልና ሊጠፋ ይችላል፡፡በእነዚህ ሕክምናዎች ካልተስተካከለ

መከላከያ መንገዶች

ዶ/ር ዮሐንስ ክፍሌ ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ሬዚደንት

ቴሌግራም: t.me/HakimEthio Hakim


Exit mobile version