የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ

(ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን ‘አቶ አበበ’ እና ‘አቶ ከበደ’ የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን)

አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው መምጣት ጀመረ፡፡ ሕመሙ ሲብስባቸው ጎረቤታቸውን በማማከር ወደ ባሕል መድኃኒት ቤት ያመራሉ፡፡

ባለመድሃኒቱም የሚቀባ የባሕል መድሃኒት ይሰጣቸውና እንደሚያድናቸው አረጋግጦላቸው ይሸኛቸዋል፡፡ አቶ አበበ የተሰጣቸውን መድኃኒት እንደተባሉት መቀባት ይጀምራሉ፡፡ በሦሥተኛው ቀን ኪንታሮቱ ይፈነዳና መግል ማውጣት ጀመረ፡፡ በአራተኛው ቀን አቶ አበበ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ተደናግጠው ወደ ሆስፒታል ያመጧቸዋል፡፡

ሆስፒታል ሲደርሱ የአቶ አበበ የልብ ምት በጣም ይፈጥናል፡፡ የደም ግፊታቸው በጣም ወርዷል፡፡ በድንገተኛ ክፍል ያሉ የጤና ባለሙያዎች በመረባረብ በመርፌ መድሐኒቶችን ፣ ግልኮስ፣ ፈሳሻ ንጥረ ነገርና የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያደርጉላቸውም ቁስሉ ኢንፌክሽን ፈጥሮ በደም ውስጥ ስለተሰራጨ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ከዚህም የተነሳ አቶ አበበ ጽኑ ሕሙማን ክፍል በአስቸኳይ እንዲገቡ ተደርጎ የተለያዩ የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

ሌላኛው ታካሚ አቶ ከበደ ናቸው፡፡ እድሜያቸው 58 ሲሆን የባሕርዳር ኗሪ ናቸው፡፡ ከ5 ዓመት በፊት ጀምሮ የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) ጀምሯቸው በየጊዜው እየተባባሰቸው ይሄዳል፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ታዋቂ የባሕል ሕክምና አዋቂ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ባለመድኃኒቱም ከመረመራቸው በኋላ በመርፌ የሚወጋ መድኃኒት አዘዘላቸውና ያበጠው ኪንታሮት ላይ መድኃኒቱን በመርፌ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እንደሚድን ነግሯቸው ይሰነባበታሉ፡፡

ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ ኪንታሮቱ እብጠቱ እየጨመረ ይሄድና በሳምንቱ ይፈነዳል፡፡ ከዛም ተመልሰው ሲሄዱ ባለመድኃኒቱ እየቆየ እንደሚድንላቸው ነግሮ ይሸኛቸዋል፡፡ ይሁንና ቁስሉ ከመዳን ይልቅ እየሰፋ፣ መግል እያመንጨና እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ የዚህን ጊዜ ቁስሉን በጨውና በውሃ እያጠቡ በቤት ይቆያሉ፡፡ ቁስሉ እየሰፋ በመሄዱ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ከበደ ሰገራ መቆጣጠር ያቅታቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ዳይፐር መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ የሕመሙ ደረጃ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ አቶ ከበደ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተልከው በተደረገላቸው ምርመራ የፊንጢጣ መቆጣጠሪያ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ በመጎዳታቸው በሆዳቸው በኩል የሰገራ መውጫ (Permanent colostomy) እንዲሠራላቸው ተወሰነ፡፡

See also  በዚህ መሃል ግን አንድ ነገር ተከሰተ!!

ከነዚህና መሰል ብዙ ታሪኮች እንደምንረዳው ለኪንታሮት ተብለው ከትልልቅ ከተማ እስከ ገጠር የሚሰራጩ የባሕል መድኃኒቶች በኅብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ነው፡፡

የባሕል ሕክምና በአግባቡ ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ቢዛመድ ለማኅበረሰባችን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ቢታመንም የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻች ይህ ዓይነቱ የኪንታሮት የባሕል ሕክምና ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመናገር ያስደፍረናል፡፡

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids) ምንድነው?

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)፦በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም ከ45 – 65 ዓመት ባሉት ሰዎች ላይ በብዛት ይከሰታል

የኪንታሮት በሽታ በዋናነት በሁለት (types) ይከፈላል

፩. ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ክፍል ላይ የከሰት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመምም (Pain) ያስከትላል፡፡

፪. ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመም አይኖረውም

ይህ የኪንታሮት ዓይነት 4 ደረጃዎች (grades) አሉት።

 • አንደኛ ደረጃ (Grade-1) ይህ ደረጃ በፊንጢጣ ግድግዳ ላይ እብጠት ሲኖር ነው፡፡ እብጠቱ በዋናነት በስተ ግራ፣ በፊት ለፊትና በስተኋለኛው የፊንጢጣ ግድግዳ ላይ ይከሰታል፡፡
 • ሁለተኛ ደረጃ (Grade-2) በዚህ ጊዜ የእብጠቱ መጠን ጨምሮ ለሽንት ሲቀመጡ በሚኖር ማማጥ እባጩ ወደውጪ ሲወጣና በራሱ ጊዜ ወደውስጥ ሲመለስ ነው፡፡
 • ሦሥተኛ ደረጃ (Grade-3) – በዚህ ጊዜ እባጩ ለሽንት ሲቀመጡ ወደውጪ ይወጣና በራሱ ስለማይመለስ የግድ በእጅ መመለስ ሲፈልግ ነው፡፡
 • አራተኛ ደረጃ (Grade-4) በዚህ ጊዜ እባጩ ላይመለስ በፊንጢጣ ይወጣና ይቀራል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

 • የሆድ ድርቀት -አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር (ፓስታ፣ ማኮሮኒ፣ ነጭ ዳቦ…) እና በቂ ውሃ አለመጠጣት
 • እርግዝና
 • የትልቁ አንጀት ካንሰር
 • ሽንት ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
 • ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ (chronic diarrhea)
 • ዕድሜ መጨመር

ምልክቶች (clinical features)

 • ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደማቅ ቀይ ደም
 • በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ
 • ከፊንጢጣ የወጣ ሥጋ መሳይ እባጭ
 • በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር
See also  በገንዘብ ራስን ለመቻል ቁልፉ የገንዘብ ፍሰት ቁጥጥርን ማወቅ ነው።

የኪንታሮት መዘዞቹ (complications)

 • ኪንታሮቱ ውስጥ የደም መርጋት (thrombosis)ና ከፍተኛ ሕመም
 • ወጥቶ አለመመለስ (irreducible)ና መበስበስ (Necrosis)
 • መመርቀዝ (infection)ና መግል መቋጠር
 • ያልተለመደ የሰውነት ክፍተት (fistula)
 • የሰውነት መሰንጠቅ (fissure)
 • ሰገራን አለመቆጣጠር (Incontinence)
 • የተለመደ ባይሆንም የደም ማነስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ኪንታሮት እንዴት ይታከማል?

በመጀመሪያ ሕመሙ ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሕመም ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ ለመታከም ፍርሃትን/ሐፍረትን ማሰወገድ ይጠበቅበታል፡፡

፩. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ

፪. ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድ

፫. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ 20- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ ወይም ሦሥቴ መዘፍዘፍ (በበረዶም ሊሆን ይችላል)

፬. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹሕ ውሃ መታጠብ

፭. ሻካራ የመፀዳጃ ወረቀቶችን አለመጠቀም

፮. የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት

፯. የሚቀቡ የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም

አብዛኛውን ጊዜ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ሕመሙ ሊሻሻልና ሊጠፋ ይችላል፡፡በእነዚህ ሕክምናዎች ካልተስተካከለ

 • ቀለል ያለ ቀዶ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

መከላከያ መንገዶች

 • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ፣ ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድና የሆድ ድርቀትን ማስወገድ
 • ሰገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያሳልፉ ወደ ሽንት ቤት መሄድ
 • መፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ
 • ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶችን ሲያዩ ወደ ሕክምና ተቋም መሔድና ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ክፍሌ ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ሬዚደንት

ቴሌግራም: t.me/HakimEthio Hakim


 • የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ዜጎች የሚጠበቅባቸውን እንዲያወጡ ጥሪ አቀረበ
  በመጪው አዲስ ዓመት ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ አካሂዷል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩ አዲሱን 2016 ዓመተ ምህረት በይቅርታና በእርቅ መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጉባኤው የጳጉሜን ቀናትን የጸሎትና ንስሐ መርሐ … Read moreContinue Reading
 • የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ
  (ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን ‘አቶ አበበ’ እና ‘አቶ ከበደ’ የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን) አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው … Read moreContinue Reading
 • ካንሰር ግን ምንድን ነው?
  “ካንሰር ግን ምንድን ነው?” ብላቹ ለምትጠይቁ በሙሉ። ቀለል ባለ ቋንቋ ለማብራራት ልሞክር እስኪ ምንም ይህ በሽታ ከግዜ ወዲህ በስፋት ቢታወቅም ለረጅም አመታት ‘ነቀርሳ’ በሚል ስሙ በብዛት ይጠራ ነበር። ካንሰር ማለት በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ህዋሶች (በጤና ግዜም ሰውነታችን የተገነባው ከነሱ ነው) እብደት ነው ብንለው ይቀላል። በተለያዩ እስካሁን በሚታወቁም ሆነ በማይታወቁ … Read moreContinue Reading
 • ብጉር | Acne vulgaris
  1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል 2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production) 3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት 4-ብግነት (Inflammation) ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች ጭንቀት (stress) ከመጠን ያለፈ ውፍረት በወር አበባ አካባቢ የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin…) በስራ ሁኔታ … Read moreContinue Reading
 • የጦርነት ጠባሳ – ትግራይ በመድሃኒት እጥረት ሳቢያ ህይወት እያለፈ ነው፤
  ከትግራይ የሚወጡ ዜናዎች የሜብሹ ናቸው። የጦርነቱ ጠባሳ እያደር የሚያሰማው ዜና እረፍት የሚነሳ ቢሆንም ጦርነቱን ሲያጋግሉና “ግፋ በለው” ሲሉ የነበሩ ወገኖች ለመልሶ ማቋቋም ሲተጉ አልታየም። በርካቶች እንደሚሉት የፌደራል መንግስት በጀትና ቋሚ እገዝ እንዳለ ሆኖ በጦርነቱ ወቅት ሲደጋገፉ የነበሩ ዲያስፖራ የትግራይ ተወላጆች ወገኖቻቸውን መደገፍ ይገባቸዋል። ሪፖርተር በመድሃኒት እጥረት ዜጎች በትግራይ መሞታቸውን ከዚህ … Read moreContinue Reading

Leave a Reply