Site icon ETHIO12.COM

በወለጋ ወላዶችን የሚያገለግል የቀይ መስቀል አምቡላን በቆመበት በታጣቂዎች ተቃጠለ፣ ” አምቡላንስ ማቃጠል ዓላማው ምንድን ነው?

” በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ” ሲል ቀይ መስቀል በድርጊቱ ግራ መጋባቱን ጠቅሶ ዜናውን ይፋ አድርጓል።

ቀይ መስቀል ብቻ ሳይሆን ዜናውን የሰሙ ከየአቅጣጫው “ምን የሚሉት ፖለቲካ ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? ህዝብ በተለይም ወላድ እናቶች በወሊድ እንዳይሞቱ በፍጥነት ህክምና ስፍራ ለማድረስ የሚያገለግል ተሽከርካሪ ማንደድ ለየትኛው ህዝብ የሚደረግ ትግል ነው? እስከመቼ በዚህ ዓይነት ድንቁርና ተቀጥላላችሁ?” በሚሉና እጅግ ብስጭትን በሚገልጹ ቃላቶች ተቃውሞ ተሰንዝሯል።

እየተደበቁና እያደቡ ማህበራዊ መገልገያዎችን ማውደም ልዩ ምልክቱ አድርጎ በየአቅጣጫው የሚካሄደው የትጥቅ ትግል ምግባር የጎደለው፣ ስርዓት የነጠፈበት፣ ዓላማ ቢስ፣ ለማንና ለምን እደሚታገል የማይለይ፣ የሚምልበትን ህዝብ መልሶ የሚበላና የሚጎዳ፣… እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ አስነዋሪ ተግብራት እየታዩበት ነው።

ነጹሃን ከመግደል፣ ከማፈናቀል፣ መኖሪያቸውን ከማንደድና ከማፈናቀል በዘለለ ይህን አስነዋሪ ድርጊት እንደ ቅዱስ የትግል አማራጭ አድርገው የሚያቀርቡ የንቅናቄና ነጻ አውጪ መሪዎችና አክቲቪስቶ በየቀኑ መፍላታቸው ” አገርቱን ለመረከብ በመናበብ እየተረባረቡ የሚሰሩት ሃይሎች በታሰቡ ቁጥር ተስፋ የሚያስቆጥር ነው” ሲሉ በሚሰሙትና በሚያዩት ግራ የተጋቡ እየተናገሩ ነው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የምዕራብ ወለጋ ዞን ሀሩ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንብረት የሆነና ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ ET05-01939 አምቡላንስ ተሽከርካሪ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በሀሩ ወረዳ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በቆመበት በታጣቂ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡

ማኅበሩ መሰል ድርጊቶች ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶች የሚጥሱና በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች በሰብዓዊ አገልግሎቱ ላይ እንቅፋት እየፈጠሩበት እንደሚገኙ ማህበሩ አመልክቷል።

በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ሲል አስገዝቧል።

ማህበሩ ” አሁንም በድጋሚ በመላው አገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች እንዲሁም አምቡላንሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ መሰል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን ” ብሏል።

ዜናው ከቲክቫህ፣ ከማህበራዊ ገጾችና በዚያው ላይ ከተገኙ አስተአየቶች የተሰባሰበ ነው


Exit mobile version