“አርቲስት ቴዲ አፍሮ የጥምቀት በዓልን ወደ አደባባይ ወጥቶ ማክበሩን የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል” ሲሉ ነው በርካቶች ባሰራጩት አስተያየት ” ነገሩ ምንድን ነው?” ሲሉ ግራ በመጋባት ማብራሪያ የጠየቁ ቢበዙም፣ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው የነበሩ አካላት ላይ ውግዘት መድረሱን ያስታወሱም አልታጡም።
የሚያደርገውን በማወቅ፣ ጊዜና ሰዓት በማስላት በሚያከናውናቸው ተግባሮቹ ስኬት የለኩት “ቴዲ ሳያውቅ ይህን ለበሰ ለማለት ያስቸግራል” ሲሉም ተድምጠዋል።
የዲዛይን ችሎታ አካታ እንዳያዘች የሚነገርላት ባለቤቱ አምለሰት በጥንቃቄ እንደምትሞሽረው የሚያውቁ “ይህን እንደ ስህተት መቀበል ያዳግታል” ሲሉ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደሚሹ አመልክተዋል።
ፎቶውን በማጋራት ሰፋ ያለ አስተያት ከጻፉት መካከል ቶማስ ጃጃው በቴሌግራም ገጹ ” እንደ ማንኛውም በብርሃነ ጥምቀቱ እንደሚያምን ክርስቲያን በዓሉን በማክበሩ ከማንም በላይ የበዓሉ በረከት ተካፋይ የሚያደርገው ደስተኛው ራሱ የሚሆን መሆኑ ቢታወቅም፣ በሙዚቃው ዓለም ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት አርቲስቶች አንዱ እንደመሆኑ የጥምቀት በዓልን በአደባባይ ተገኝቶ ታቦታቱን በእልልታ በጭብጨባና በዝማሬ እያጀቡ ከሸኙት ታዊቂ ሰዎች መካከል እንደመታየቱ የእሱ አድናቂ የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ብዙዎችን እንደተለመደው ሊያስደስት የመቻሉ ጉዳይ አያጠራጥርም” ሲል አስተያየቱን በጥቅል እውነት ይጀምራል።
ያክልና ” በእውነቱ እኔም ጥምቀትን ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ተገኝቶ ማክበር በመቻሉ ጊዜውን በመልካም ቦታ አሳልፏል ብዬ አምናለሁና ደስ ይለኛል። ነገር ግን ቴዲ አፍሮ ለጥምቀት በዓል ለብሶት የወጣው ልብስ ላይ የመስቀል ምልክቱ የተዘቀዘቀ በመሆኑ ጥምቀትን ሲያከብር ተመልክቶ ደስ ይላል ያለ የእምነቱ ተከታይ የእሱ አድናቂዎች ጭምር እንኳን ቢሆን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይና በጥምቀት በዓል ላይ ለብሶት የታየ ስለሆነ ብለው ጉዳዩን በቀላሉ ሊመለከቱት ይችላሉ ብዬ መደምደም አይቻለኝም” ብሎ መከራከሪያውን ያቀርባል።
“በተዘቀዘቀው መስቀል ግራ የሚጋቡበትና ሊቆጡበት የሚችሉ የእምነቱ ተከታዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ነው የማስበው” የሚል ፍርድ የሰጠው ቶማስ፣ ሲያስረዳ ” ምክንያቱም የቴዲ አፍሮ አድናቂ የሆኑት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ‘መስቀል ሃይላችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው’ የሚሉ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ከዚህ በፊት የመስቀል ምልክቱን እንደ ቴዲ አፍሮ ዘቅዝቆ ለበሰ የተባለ ሰውን አንዴ ‘666’ ሌላ ጊዜ ‘ደግሞ ፀረ-ኦርቶዶክስ’ የሚል ዘመቻ ተከፍቶበት እንደነበር የሚታወቅ ነውና”
የቶማስ አማላካችና ንፅራዊ አስተያየት የሙግት ሃሳቡን ሲያጸና “እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ የተዘቀዘቀ የመስቀል ምልክት ያለበትን ልብስ ራሱ ያሰራው፣ ሱቅ ላይ የገዛው፣ ወይም በስጦታ የተሰጠው፣ የመስቀሉን ሁኔታ ያላስተዋለው ጉዳይ ነው ሊባል ይችል ይሆናል” የሚል ግምት ያስቀድምና “የታዋቂ ለዛውም እንደ ቴዲ አፍሮ ላሉት ለአለባበሳቸው፣ ለአነጋገራቸውና ለአረማመዳቸው ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፤ ነገሮችን በጥንቃቄ ይከታተላሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ሰዎች ሺዎች በሚሰበሰቡበትና በሚገኙበት በጥምቀት ለሚለበስ ልብስ ልዩ ትኩረት በሚሰጥበት አደባባይ የተዘቀዘቀ መስቀል ያለበት ልብስ ያለማስተዋል የተለበሰ አድርጎ ለመቁጠር እንዴት እንደሚቻል አላውቅም” በሚል ድርጊቱ ሆን ብሎ የተደረገ የሚመስልበትን ማሳያ ያመላክታል።
“የመስቀሉ መዘቅዘቅ ችግር የለበትም ከተባለ” ይላል ጸሃፊው “ከዚህ ቀደም መስቀል ዘቅዝቀው ለብሰዋል በሚል የተሰጡ ትርጉሞች የተደረጉ ውግዘቶች ዋጋ ያጣሉ እንደማለት ይሆናል” ሲል ቴዲ አፍሮን ለእይታና ለግምገማ አንገዋሎ አቅርቦታል።
ጉዳዩ ውሎ አድሮ የሚያስነሳውና የሚከተለው አስተያየት ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ቢያስቸግርም፣ ” በትቁር ልበሱ” ዘምቻ ወቅት የመሪነቱን ተግባር ከሚወጡ አስተባባሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ባለቤቱ ሃምለሰት ሙጬ “ነገሩን ታቃናዋለች” የሚል አስተያየት የሰጡ ጥቂቶች ታይተዋል። ይህ እስከተባለ ድረስ ቴድሮስ ካሳሁን በግሉ ያለው ነገር የለም።