Site icon ETHIO12.COM

የኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ተማረኩ፤ መተከል መሽጎ የነበረ የታጣቂዎች ቡድን ” ነፍጥ በቃኝ” ብሎ ተመለሰ፤

በወለጋ የተለያዩ ግንባሮች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሪ ናቸው የተባሉትን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ይፋ ያልሆነ ታጣቂዎች መማረካቸው ተሰማ። በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መመለሳቸውን ተቤኒሻንጉል ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ምስልና ቪዲዮ አስደግፎ አስታወቀ።

በዳሬ ሰላም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራሮች ጋር ንግግር እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ኦፕሬሽኑ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቁት ክፍሎሽ እንዳሉት በሰሙሉ ወጊያ በተለይም ከትናንት በስቲያ የኦነግ ሸኔ አዋጊዎች ናቸው የተባሉ መማረካቸውን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል በሚያደርጉት የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ላይ ታቂዎች ላይ በተመሳሳይ ሙሉ ማጥቃትና ማጽዳት መጀመሩ ይፋ በተነገረበት ወቅት፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሰፊ ይዞታቸውን እያጡና እየተማረኩ መሆናቸው መንግስት በይፋ ባይገልጽም በአካባቢው ያሉ ምስክሮች አረጋግጠዋል።

“በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጠቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመልሰዋል” ሲል ነው ቢሮው ይፋ ያደረገው።

በመኩሪያው ዚፋሃ እና በመኮነን ፋኖ በሚባሉ ግለሰቦች ሲመራ የነበረው የጉህዴን ታጣቂዎች ቡድን በውይይት የሰላም ስምምነት መቀበሉ ታውቋል። ውይይቱ ሰፊና ከፍተኛ ጥረት የተደረገበት እንደሆነ ተመልክቷል።

በማንዱራ ወረዳ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ሲገቡ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች በገነተ ማሪያም ከተማ በመገኝት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ፣ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ በመቀበል ወደ ህብረተሰቡ መመለሳቸው የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት የተረጋጋ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።

ተመላሾችን በተማሩበትና ፍላጎታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ለማሰማራት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ጫካ ውስጥ መቀመጫቸውን አድርገው በአዋሳኝ አካባቢዎች ስጋት ሲፈጥሩ የነበሩ ታጣቂዎች በውይይት መምጣቸው ለህብረተሰቡ ሰላም ዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰጥም ነው የተገለጸው።

የሰላም ስምምነቱን ተግባረዊ ለማድረግና ወደ ሰላምና ልማት ለመግባት የሀገር ሽማግሌዎችና አመራሮች በተገኙበት ከሰላም ተመላሾች ጋር በጉሙዝ ብሄረሰብ ባህል መሠረት የእርቅ ስነ ስርዓት መካሄዱን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ ያመለክታል።


Exit mobile version