“ነጻ በወጡ አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ ነው” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎ
ከአሸባሪው ህወሃት ነጻ በወጡ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በሰጡት መግለጫ “የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር ባከናወኑት ምርመራ ውጤትና ምክረ ሃሳብ መሰረት መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል” ብለዋል።
መልሶ ግንባታና አገልግሎቶችን ከማስጀምር ጎን ለጎን በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል።
“በወራራ ተይዘው በነበሩ አካባቢዎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመረምር የወንጀል ምርመራና የማስቀጣት ቡድን በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል ተቋቁሞ የምርመራ ስራው ተጀምሯል” ብለዋል።
“የምርመራ ቡድኖቹ በአሸባሪው ትህነግ ተይዘው በነበሩ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የደረሱትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎችን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት በሚያስችል መልኩ ቅኝት ለማድረግ ተሰማርተዋል” ነው ያሉት።
በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ የንጹሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋትን፣ የአካል መጉደልን፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን፣ ከቤት ንብረት መፈናቀልን፣ የንብረት ውድመትን፣የመንግስታዊ ተቋማት ሰነዶች ውድመት እና ሌሎች እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎችን ለማጣራት እነዚህ የመርማሪ ቡድኖች ተሰማርተዋልም ሲሉ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል መርማሪ ቡድን መሰማራቱንና በስሩ ሁለት ንዑሳን ቡድኖችን ይዞ ምርመራ እያከናወኑ ይገኛል ያሉት ሚኒስተር ዴኤታዋ “በአማራ ክልል ደግሞ በርካታ ቡድኖች መሰማራታቸውን አንስተው ሸዋሮቢትን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአስር ወረዳዎች፣ በደቡብ ወሎ ስምንት ወረዳዎች፣ የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች፣ በደሴና ኮምቦልቻ፣ ጋሸናን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ምርመራና ምልከታዎችን ለማድረግ ቡድኖቹ ተሰማርተዋል” ብለዋል።
ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ ቡድኖቹ ወደ ዋግኽምራ አካባቢዎችና ወደ ወልድያ መሰማራታቸውንም አንስተዋል።
ምርመራዎቹና ምልከታዎቹ የሚካሄዱት በአሸባሪው ትህነግ የተካሄዱትን ጥፋቶች በተጨባጭና በሁለንተናዊ መልኩ ማሳየት በሚችሉበት ደረጃ እንደሆነም አስታውቀዋል። via (አሚኮ)
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋገጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋገጠ