Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ለህ.ግ ለነጮች በወር ከ1.1 ሚልዮን ዶላር በላይ ይከፍላል፤ ወጪው የሚዲያና ሌሎች ተከፋዮችን አይጨምረም

የትግራይ ሕዝብ ነሳ አውጪ ግንባር / ትህነግ ” ብቸኛ የአሜሪካና አውሮፓ ጥቅም አስጠባቂ ነኝ፣ የተረጋጋች አገር መምራት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ” በሚል የአሚሪካን ፖሊሲ አውጭዎች ለማሳመን በወር ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ተጠቆመ። ወጪው የነሳ አውጪውን ድርጅት ዓላማ የሚስተጋቡ የሚዲያ ሰዎችና ነጭ አክቲቪስቶች የሚከፈለውን አይተቃልልም።

አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ለምግብ ችግርና አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለከፋ ችጋር እንደታጋለጡበት የሚነገርለት የትግራይን ክልል ነጻ ለማውጣት የትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው ትህነግ፣ ይህን ያህል ከፍተኛ ሃብት የሚያፈሰው ለስምንት ከወስዋሾች የገዘፉ የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶች ነው።

በቂ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሰው ከኢትዮ 12 ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር ሓይማኖት እንዳሉት “ትህነጎች ስምንት የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶ ቀጥረዋል። ከለውጡ በፊት በወር አርባ ሺህ ዶላር ይከፍሏቸው ። ከልወጡ በሁዋላ ከ100 እስከ 140 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሏቸው መረጃ አለኝ። ይህን ሁሉ ሃብት እያፈሰሱ ነው ኢትዮጵያ ስሟ እንዳየሳ፣ ጉዳይዋ እንዳይሰማ ሁሉንም በሮች የተቆጣጠሩት። ስልጣን ላይ እየሉ ባከማቹት የዘርፊያ ሃብት የህዝብ ግንኙነቱን ስራ በገንዘብ ቆላልፈው ይዘውታል።”

ለዲሞክራቶች፣ ለሪፐብሊካኖች፣ ለሃይማኖቶች ጥምረት፣ለጥቁር አፍሪካ አሜሪካኖች ጥምረት፣ ለዋይት ሃውስ፣ ለኮንግረንስ፣ Lesbian, Gay, Bisexual and Transgender. q ለሚባሉት ጥምረቶችና ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል በህዝብ ግንኙነት የሚሰሩ የታሰበባቸውና የተመረጡ አቅጣጫዎች መሆናቸውን የስምንቱን ተቋማት ሚና በማስረዳት ዶክተር ሃይማኖት አስረድተዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን እዚህ ላይ ይመልከቱ። የዚዲዮውን ምልልስ ደግሞ በዩቱብ ቻናላችን እዚህ ላይ ያገኙት።


Exit mobile version