Site icon ETHIO12.COM

አማራ ክልል – ትምህርት፣ህክምን፣አገልግሎት የለም … በልጠን ካልተገኘን?

አማራ ከጠላቶቹ በልጦ ካልተገኘ በስተቀር፤ በአሁኑ ወቅት በከፊል አማራ ያየነው ሁለንተናዊ ውድመትና ውርደት፤ እንዲሁም የሥነ-ልቦና ስብራት፤ ነገ ወደ ጎንደርና ጎጃም ተስፋቶ መላ አማራን በማዳረስ የመላ አማራን ውርደትና ስብራት ሊያስከትል እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል፡፡ ይህ ታሪካዊ እፍረት እንዳይከሰት ከፈለግን፤ የአማራ ህዝብ ልጆቹን ወደ መከላከያ ዛሬውኑ ይላክ፤ የአማራ ወጣቶችም የሁኔታዎችን አስቸጋሪነት በመገንዛብ ዛሬውን መከላከያን ተቀላቀሉ፤ የምዝገባ ጊዜው እያለቀ ነው፤ነገ ከነገ ወድያ ዕድሉ ላይገኝ ይችላል፡፡

ነጻ አስተያየት በ Chuchu Alebachew በልጠን ካልተገኘን….!!!

በአሁኑ ወቅት ሕይወት በአማራ ክልል ተጎሳቁሏል፡፡ ይህ መጎሳቆል በተለይም በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን፤ ሰሜን ወሎ፤ደቡብ ወሎ፤ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሙሉ በሙሉ፤ እንዲሁም በሰሜን ሽዋ፤ ደቡብ ጎንደርና ሰሜን ጎንደር ዞኖች በከፊል በከፋ ሁኔታ የሕይወት መጎሳቆል ተከስቷል፡፡ ማህበራዊ ቀውሱ በእነዚህ አካባቢዎች አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ ትምህርት የለም፤ የጤና አገልግሎት የለም፤ የግብርና ልማት የለም፤ መሰረተ ልማት የተባለ በሙሉ ወድሟል፡፡

ዓላማው ከጭፍጨፋ የሚተርፍ አማራ ካለ፣ አንድ መቶ ዓመት በድህነት ወደኋላ መመለስ ነው። ከሁሉም በላይ በህዝባችን ላይ የደረሰው የስነ ልቦና ጉዳት እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ቀላል ግምት የማይሰጠው ሰብዓዊ ኪሳራ ደርሶብናል፡፡ አሳዛኙ እና ቁጭት ሊፈጥርብን የሚገባው ጉዳይ፤ ይህ አውዳሚና ታሪክ ይቅር የማይለው የጥፋት ተግባር የተፈፀመው ከ5 ሚሊየን በማይበልጥ ህዝብ በወጡት የትግራይ ወጣቶችና ጎልማሳዎች መሆኑ ነው፡፡ ልብ በሉ ከዚህ ከአማራ አንፃር ሲነፃፀር በቁጥር አናሳ ከሆነ ማህበረሰብ የተገኙ ወሮበላዎች ናቸው 30 ሚሊየን በሚሻገረው ህዝባችን ላይ ይሄን ሁሉ አስቃቂና በታሪክ የማይረሳ ሁለንተናዊ ውድመት ያደረሱት፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የትግሬ ወራሪ ይሄን ያክል ውድመት እያደረሰ፤ እንደ አማራ የተሰጠው ምላሽ በልኩ አለመሆኑ እጅግ ያበሳጫል፡፡

እኛ አማራዎች ካወቅንበት ራሳችንን እንድንመረምር የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን ፡፡እውነት ነው መጀመሪያ አካባቢ መዘናጋት ስለነበር የአማራ ህዝብ በጠላቶቹ ልክ አለመዘጋጀቱ ያን ያክ ላይገርመን ይችላል፡፡ነገር ግን የጠላት አውዳሚነት በተግባር ከተረጋገጠ በኋላም ቢሆን እንደ አማራ እየተሰጠ ያለው ምላሽ በልኩ ነው ማለት አልችልም፡፡ለምሳሌ ዛሬም ቢሆን ወጣቱ ሊከት በሚገባው ልክ ወደ መከላከያ እና ልዩ ኃይል እየከተተ አይደለም፡፡

በተለይም የአማራ ወጣት መከላከያን እዲቀላቀል ብዙ ተደከመ፤ብዙ ተለፈለፈ፤ ምላሹ ግን አሁን አጥጋቢ ሁኖ አይታይም፡፡ እንዴው የእውነት እንነገጋር ከተባለ በአሁኑ ወቅት አቅሙ ለጦርነት የፈቀደለት በተለይም የአማራ ወጣት ቴክኖሎጂን መሰረት ካደረገው ከዘመናዊ ውትድርና ውጭ ሌላ የሚያስበው ነገር መኖር አለበት? አማራ እንደ አማራ በማንነቱ እየተጠቃ፤ ንብረቱ እየተዘረፈና እየወደመበት፤ እናቶቻን እና እህቶቻን እየተደፈሩ፤ …ወዘተ የአማራ ወጣት እንዴት እንቅልፍ ተኝቶ ሊያድር ተቻለው? ዛሬ ላይ የዋግ፤ ኦሮሞ ብ/ሰብ፤ የድፍን ወሎና ሸዋ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነው እያለ፤ የጎንደር፤ አዊና ጎጃም ወጣቶች የሚማሩት ትምህርት እንዴት ሊጣፍጣቸው ይቻላቸዋል? በአጠቃላይ ጊዜው ዛሬም ሆነ ነገ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ እጅግ አሳሳቢ ነው። ይሄንን አሳሳቢ ሁኔታ መቅረፍ የሚቻለው ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ከገነባን ብቻ ነው፡፡

በተለይም ትህነግ ዛሬም ሆነ ነገ በሕይወት እስካለ ድረስ አማራን ሳያንበረክክና ፤የጀመረውን ውድመት ወደ ጎንደርና ጎጃም ሳያስፋፋ ተኝቶ ያድራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ መንታ ልብ አማራ ካለ፤ ይህን መሰሉ አማራ መቸም ቢሆን የትህነግን ባህሪና ዓላማ ከአማራ አንፃር አይረዳውም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የአማራ ህዝብ የት*ግሬ ወ*ራሪ ዛሬም ሆነ ነገ እያደረሰብን ካለውና ሊያደርስብን ከሚችለው ውድመትና ውርደት መትረፍ የሚችለው፤ ጠንካራ የመከላካያ ሠራዊት ኃይል ሲኖር ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ በመከላካያ ውስጥ የአማራ ተሳትፎ በእጅጉ እንዲጨምር አልሞ መስራት አለበት፡፡

በመከላከያ ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ሳይኖርህ ተወረርን፤ ንብረት ወደመ፤ እህቴ ተደፈረች ብትል ጩኽት መፍትሄ አይሆንም፡፡ መፍትሄው ጠላት የሚፈራው የፀጥታ ኃይል በተለይም መከላካያ ሠራዊት እንዲገነባ አስተዋፆ ማድረግ ነው፡፡ በመጨረሻም! የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱ፣ በተደጋጋሚ የሚቀርብልህን መከላከያን ተቀላቀል ጥሪ አሁንም እንደተለመደው ችላ ብለህ ካለፍነው፤ ዛሬም ሆነ ነገ የትግሬ ወራሪ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ላለውና ለሚያደርሰው ውድመት አሜን ብሎ እንደመቀበል ይቆጠራል፡፡

አማራ ከጠላቶቹ በልጦ ካልተገኘ በስተቀር፤ በአሁኑ ወቅት በከፊል አማራ ያየነው ሁለንተናዊ ውድመትና ውርደት፤ እንዲሁም የሥነ-ልቦና ስብራት፤ ነገ ወደ ጎንደርና ጎጃም ተስፋቶ መላ አማራን በማዳረስ የመላ አማራን ውርደትና ስብራት ሊያስከትል እንደሚችል ማመን ያስፈልጋል፡፡ ይህ ታሪካዊ እፍረት እንዳይከሰት ከፈለግን፤ የአማራ ህዝብ ልጆቹን ወደ መከላከያ ዛሬውኑ ይላክ፤ የአማራ ወጣቶችም የሁኔታዎችን አስቸጋሪነት በመገንዛብ ዛሬውን መከላከያን ተቀላቀሉ፤ የምዝገባ ጊዜው እያለቀ ነው፤ነገ ከነገ ወድያ ዕድሉ ላይገኝ ይችላል፡፡

Exit mobile version