Site icon ETHIO12.COM

የመድ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት ያለመ የውሳኔ ሀሳብን (resolution) በሙሉ ድምጽ አጽድቋል!

ባለፈው አርብ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አባል አገሮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

‘Countering disinformation and promotion and protection of human rights and fundamental freedoms’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ የውሳኔ ሀሳብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በሰብዐዊ መብቶችና መሰረታዊ በሆኑ ነጻነቶች እንዲሁም ዘላቂ በሆኑ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals) ላይ እያስከተለ ያለውን አሉታዊ ሚና አጽኖት ሰጥቷል።

ሀሰተኛ መረጃ ለግጭት፣ ለመድሎ፣ ለሰብዐዊ ቀውሶች መከሰትና ለአለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የውሳኔ ሀሳቡ እውቅና ሰጥቷል። በተጨማሪም የውሳኔ ሀሳቡ የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በማናቸው የመገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ጥላቻንና ግጭትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎችን አውግዟል።

የውሳኔ ሀሳቡ አገሮች ለሰላምና ለትብብር ጠንቅ የሆነውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጻረር መልኩ የመዋጋት ሀላፊነት እንዳለባቸውም ያሳሰበ ሲሆን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

የውሳኔ ሀሳቡ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ያሰመረ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽነትን በማስፈንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚያበረታቱ አሰራሮችን በመቀነስ የራሳቸውን በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ቀዳሚ ሚና እንዲጫዎቱም ሀላፊነት ሰጥቷል።

ይህ የውሳኔ ሀሳብ በፓኪስታን አርቃቂነትና በበርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን ለወራት ውይይት ሲደረግበት ነበር።

EthiopiaCheck Updates


Exit mobile version