ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱን አመለከቱ።
ዶክተር ሚዛን ኪሮስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ የኮቪድ -19 ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በሽታው ያለባቸው እና በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በየጊዜው እየጨመረ መምጣት የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ይህም የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡
የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተው፣ በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ አመልክተዋል። የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅም በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)
- “አብይ ባህር ዳር እንዳይመጣ ለማስጠንቀቅ ቦንቦች አፈንድተናል” ፋኖ – አብይ በባህርዳር ድልድይ መረቁበአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የ380 ሜትር ርዝመትና 43 ሜትር ስፋት… Read more: “አብይ ባህር ዳር እንዳይመጣ ለማስጠንቀቅ ቦንቦች አፈንድተናል” ፋኖ – አብይ በባህርዳር ድልድይ መረቁ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት።… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?