የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊዎች የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ

December 6, 2021 topzena1 0

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ።
በቅናሹ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 20 ቀን 2021 ድረስ ትኬት የሚቆርጡና፥ ከፈረንጆቹ ጥር 1 እስከ 31 ቀን 2022 ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ የዘመቻው ተሳታፊ መንገደኞች መሆናቸውን አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡