“በተካድኩ” ስሜት መከላከያ አማራ ክልልን ለቆ ሊወጣ ነው?

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አላስፈላጊ መስዋዕትነት ላለመክፈል በሚል የአማራ ክልልን ለአማራ ልዩሃይል እና ለሌሎች የፀጥታ ሃይሎች አስረክቦ ለመውጣት የሚያደርገውን ዝግጅት በፅኑ እቃወማለሁ። የዶ/ር አብይ አስተዳደር ይህን ውሳኔ ካሳለፈ ታሪካዊ ስህተት እንደፈፀመ እቆጥረዋለሁ። እውነት ነው መሬት ላይ አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ትንኮሳዎች እና በሶሻል ሚዲያው የሚደረጉ ግብረ-ገብነት የጎደላቸው ቀረርቶዎችና ዛቻዎች እንዲሁም የጥላቻ ዘመቻዎች አሉ። ነገር ግን ይህ የመላው አማራ ድምፅ አለመሆኑን ለመናገር ብዙ ማተት አያስፈልገውም።
የአማራ ሕዝብ ከግፈኞችና ከስርዓት አልበኞች ጋር ፈፅሞ ሕብረት የለውም። “በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ይልቅ፣ ያለ ፍርደ የሄደች ጭብጦዬ ትቆጨኛለች” ብሎ ስለፍትህ የሚራቀቅ ሕዝብ ነው። ለሕግ የበላይነት መስፈን እንጅ ለስርዓት አልበኝነት መንገስ የማይተባበር በስርዓት የኖረና የሚኖር ሕዝብ ነው። የሐገሩን ሕልውና የሚጠብቅለትን መከላከያ ሰራዊትን የሚወጋ ሳይሆን ደጀን ከመሆን አልፎ ቀድሞት ለመሞት የሚሻኮት ሕዝብ ነው። ይህን ኢትዮጵያ የሕልውና ጦርነት በገጠማት ወቅት በየ ጦር ግንባሩ ያስመሰከረው ነው። የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የአማራ ሕዝብ ስርዓት አልበኝነትን በፅኑ የሚታገል ታታሪና ሰርቶ አዳሪ ኩሩና ደግ ሕዝብ ነው። ስርዓት አልበኝነትን ለማንገስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው፣በመከላከያ ላይ ትንኮሳ እየፈፀመ ያለው እና ጥቃት ለመክፈት በመንቀሳቀስ ላይ ያለው የአማራ ሕዝብ አይደለም። ይህን ራሱ መከላከያ ሰራዊቱ ምስክርነቱን የሚሰጠው ጉዳይ ነው።
በጌታቸው አሰፋ ቡድን ስር በተለያዩ የአማራ ከተሞች የሚንቀሳቀሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂዎች የግብፅ ቅጥረኞች ለአሜሪካ መሩ ምዕራባውያን ጥቅም ከፊት የተሰለፉ የ”E” ነጭ ለባሾች የ”X” እና የ”ገ” ጉዳይ አስፈፃሚ አካላት መሆናቸው እንኳን ለመንግስት ለተራ ሰውም ግልፅ ነው። ስለሆነም መከላከያ

ሁሌም በየትኛውም ጊዜ ከጎኑ ለሚቆመው ለደጀኑ ለአማራ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲል በጥፋት ሃይሎች በኩል የሚከፈል አላስፈላጊ መስዋዕትነት ሊኖር ቢችልም ሕዝቡን ያስቀድም። በወጣና በገባበት ሁሉ እየተከለ ምርኩዙ ለሚሆነው ሕዝብ ደህንነትና ሰላም ዘብ ይቁም። ቢርበው የሚያበላው ቢጠማው የሚያጠጣው ደግ ርህሩህ ሕዝብ ነው የአማራ ሕዝብ። ፈፅሞ የመከላከያን ክፋት ማየት የሚፈልግ ሕዝብ አይደለም። በመከላከያ ላይ እጁን ሊያነሳ ቀርቶ የሚያነሱትን የሚታገል ሕዝብ ነው። ይህ ደግና ጀግና ሕዝብ ለአማራ ልዩሃይል እና ለሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ብቻ ሰላሙንና ፀጥታውን ያስከብሩለት ብሎ ጥሎት ለመውጣት ማሰብ ለእኔ እንደ ክህደት የምቆጥረው ጉዳይ ነው።ለአማራ ክልል ሕዝብ ሰላምና ደህንነት አለመቆርቆር ነው።
በተለያዬ መንገድ “በአማራ ልዩሃይል እንመካለን መከላከያ አያስፈልገንም እንዲያውም እንወጋዋለን እንዋጋለን” የሚለው ድምፅ የመላው የአማራ ሕዝብ ድምፅ አይደለም።የእነዚህ ሃይሎች ዋና አላማ ታውቆ ያደረ ነው። በመሆኑም መከላከያ ከአማራ ክልል ለቆ ለመውጣት የሚያደርገውን መሰናዳት መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን። የአማራ ክልል ሕዝብ ከመከላከያ ጎን በመቆመበት ሁኔታ የአማራ ሕዝብ የጥሞና ጊዜ እንደሚያስፈልገው አይነት ይዘት ባለው መንገድ ለቆ ለመውጣት ታስቧል የተባለውን ጭምጭምታ ተቀባይነት የሌለውና ኋላፊነት የጎደለው አድርገን እንወስደዋለን።የአማራ ክልል መንግሰት ይህን ጉዳይ ተግባራዊ እንዲሆን ይተባበራል ብለን አናስብም ይህን የሚያደርግ ከሆነ ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ይሰራል።
የጥፋት መልዕክተኞች በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በየትም ክልል ያለ ጉዳይ ነው።
የአማራ ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ነበረ ወደፊትም ይሆናል!!!

See also  የኢዜማ ነገር !

Thomas jajaw telegram

3 Comments

  1. እንዴት ነው አማራን የአብይን ወይም የኦሮሞ ብልጽግናን ችሮታፈላጊ ወይም ደግሞ በአቻ ፍችው አብይን የሁሉ ነገር ፈላጭ ቆራጭ እሱንም law and order አድርገህ ለመሳል ጌታው ካልፈቀደ አማራ የማይተነፍስ አድርገህ ለማቅረብ የምትሞክረው ?? በነገራችን ላይ አማራ እና ትግሬ ያልፈለጉት መንግስት 3 አመት ሊዘልቅ አይችልም… አሁን ላይ በሁለቱም የሰሜን ክፍሎች በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ደረጃ ድጋፍ ያጣ ብቻ ሳይሆን ቢችሉ በነብስ የሚፈልጉት መሪ ሁኗል … ያሰበው እና የሚሳሳለት ረጅም ጊዜ ኢትዮጲያን የመምራት እቅዱ ከፊቱ ላይ እየተነነ ነው። ይሄን ያህል የጭንቅላት በሽታ ያለበትን psychopath በዚህ ደረጃ ዜናውን በማጣመም እና በተዘዋዋሪ የሱን ስም በማግነን መከላከያን የአንድ ሰው አድርገህ ለማቅረብ አትሞክር ። መከላከያ አማራም ኦሮሞሞም ስልጤም ጉራጌም ነው እንጂ አብይ አይደለም ። አብይ ስልተሰደበ አማራ ክልልን ለቆ ሚወጣ አብይ ሲወደስ ክልሉ ላይ ሚሰፍር የአንድ ግለሰብ ኃብት አይደለም

    1. Author

      Thanks for your comment. I am not a suporter of any parti or individuals. Anyway, please read this comment from
      ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በፍፁም ግጭት ውስጥ መግባት አያሻም። መከላከያ ሰራዊት የምትጠብቀው የሚጠብቅህ ተቋም እንጅ ልትገጥመው የሚገባ አይደለም። ማንም ኃይል ወደ መከላከያ ትንኮሳ የሚያደርግ ከሆነ እርሱ አሰላለፉ ከጠላት ጎራ እንጅ ከወገን ጎራ ሊሆን አይችልም።

      የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ትግስት እንድታሳዩ ይጠበቃል። ህዝብ ውስጥ ተደብቀው ትንኮሳ የሚያደርጉ ኃይሎች ቢኖሩ እንኳን በትግስት ማለፍ የተገባ ተግባር ነው።

      የልዩ ኃይል አባላትም ሆነ ሌላው ህዝብ ወደ ሰማይ ቢሆን እንኳን ጥይት መተኮስ አግባብ አይደለም። ጥይት መተኮስ ጥያቄን ሊፈታ አይችልም። ጥያቄው ጆሮ የሚያገኘው በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ ሲጠየቅ እንጅ ጥይት በመተኮስ ሊመለስ አይችልም።

      ህዝባችን በአገር ሽማግሌዎች፣ በኃይማኖት አባቶች እየተመራ በየቦታው ያሉ መካረሮችን ማርገብ ይኖርበታል። ወንድም ከወንድሙ ጋር ቢካረር ትርፉ ኪሳራ ነው። ፈፅሞ ወደማይጠበቅ ነገር እንዳያመራ ከአሁኑ ልጓም ማበጀት ይገባል።

      እዚህ ሶሻል ሚድያ ላይ ያላችሁ ወገኖች ቅስቀሳችሁ ኃላፊነት የተሞላበት መሆን ይገባዋል። ለጉዳዩ በቦታም በይዘትም ሩቅ ሆናችሁ በለው፣ ጣለው የምትሉ ወገኖች በጊዜ አድቡ። በለው፣ ጣለው ተያይዞ ገደል ይከታል እንጅ ጥያቄን መፍታት አይችልም።
      Gashaw mersha

  2. ጋሻው መርሻን የሚያውቅ ያውቀዋል /// እኔም በተመሳሳይ ቶሎሳ ኢብሳ ያለውን አምጥቼ ላሰፍርልህ እችላለሁ /// የፓርቲ ደጋፊ አይደለሁም ባልከው ጉዳይ ላይ ግን ከባለፈው የፓርላማ ዉሎ በኋላ ባለፉ ቀናት የጻፍካቸውን ሳነብ አንድም ቦታ ላይ ሀገር ብናፈርስ ማን ይከለክለናል ብለው ጠሚ አብይ አህመድ የደነፋበትን ንግግር አልከተብክም /// በአንጻሩ ግን ከፍተኛ ስጋቶች ያሉበት የአማራ ክልል የክልሉ ምክርቤት በህገ ደምቡ መሰረት ተወያይቶ ሳያጸንድቀው … ለምን ትጥቅ ይፈታል ብሎ ሲጠይቅ ሰሚ አጦ ህዝቡም ታክሎበት ያቀረበውን ተቃውሞ አሸውርረህ ስትዘግብ ይሄ 6 ወይም 5ኛህ ነው /// እነ ሽመልስ አብዲሳ ፖለቲካ ቁማር መሆኑን በአዳራሽ ዉስጥ በሚናገሩበት ሀገር የትኛውም የብልጽግና ተመራጭን ማመን አይቻልም

Leave a Reply