MIMI
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች
MIMI
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧን ድርጀቱ አስታውቋል፡፡
እያደገ በመጣው ገበያ ከ20 ዓመታት በላይ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ባለሞያነት ልምድ ያላት ሚሚ ለቦርድ አባልነት አብቅቷታል ተብሏል፡፡
ሚሚን ለቦርድ አባልነት ያበቃት በተለያዩ አዳጊ ገበያዎች በመንግሥት እና የግል የኢንቬስትመንት እና የፋይናንስ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ በመስራት ያካበተችው ልምድ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ሚሚ ያላት ይህ ሰፊ ተሳትፎ እና ልምድ ትዊተር በዓለም ዙሪያ የህዝብ ውይይትን ለማዳበር የያዘውን ተልዕኮ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ ፒቼት ገልፀዋል፡፡
ሚሚ የትዊተርን ማህበራዊ ኃላፊነት እና ዓለምአቀፋዊ ማህበረሰብን የመፍጠር ተልዕኮ ትጋራለች ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ትዊተር በተለይ በአፍሪካ ያለውን ተልዕኮ ለማስፋፋት በጋና ቢሮ በመክፈቱ የሚሚን ስራ እንፈልገዋለን ብለዋል፡፡
በዓለም ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲዳብሩ ዓልሞ እየሰራ ያለውን ትዊተር አደንቃለሁ ያለችው ሚሚ በበኩሏ የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ አባል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡
ሚሚ አለማየሁ በማስተርካርድ የመንግስት እና የግል ጥምረት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያለገለች ትገኛለች፡፡ ENA
- ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋገጡ፤ በትግራይ አስተዳደር ስም ማስተባበያም አውጥተዋልበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት… Read more: ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋገጡ፤ በትግራይ አስተዳደር ስም ማስተባበያም አውጥተዋል
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ