ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ በ2001 ዓ.ም. የማሽላ ተክልን በተመለከተ በአስገኟቸው አዲስ የምርምር ግኝት የአለም የምግብ ሽልማት (World Food Prize) አሸናፊ ሆነዋል። በኢትዮጵያም ከፍተኛውን የሀገር ሽልማት (Highest National Award) አግኝተዋል።
ገቢሳ ኤጄታ (ፕሮፌሰር) በ1950/60ዎቹ ዓ.ም. በቀድሞው የጅማ እርሻ ቴክኒክ ት/ቤት (Jimma Agricultural Technical School – JATS) ተምረው የጨረሱና በኋለም በአለማያ እርሻ ኮሌጅ ቀጥለውም በሰሜን አሜርካ (Indiana) በፕሩድ ዩኒቨርስቲ (Prude University) የPhD ድግሪአቸውን በማግኘት ከዛም ለብዙ ዓመታት በእርሻ ሰብል ላይ ጥናቶችን ፣ ምርምሮችን በማካሄድ ቆይተዋል።

የፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ ምርምር ግኝት ለአፍሪካና ለብዙ የዓለም ሀገራት የማሽላ ተክል (Sorgum) አርቢ ገበሬዎች የምስራች ነው። በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የምግብ አቅርቦት ያሳደገ የሳይንሳዊ ምርምር ውጤት ነው።
የምርምር ጥናታቸው ያተኮረው በማሽላ እርሻ ውስጥ የሚበቅሉ አረሞች በተለይም ‘ስተሪጋ’ (Striga) የሚባለው የአረም ዝርያ የማሽላውን ምርታማነት በእጅጉ የሚቀንስ (የሚያቀጪጭ) በመሆኑ ፣ ይህን የአረም ዝርያ ለይቶ በማጥናትና የማሽላ ተክሎች አረሙ እንዲበቅል ፣ ከተኛበት እንዲነቃቃና እንዲስፋፋ የሚያደርገውን ምክንያቶች ማጥናትና የማሽላ ተክል አረሙን የሚቋቋምበትን መንገድ መፈለግና አዲስ አረሙን የሚቋቋም (Striga-resistant) ዝርያ ማግኘት ነበር።
እነኚህ ማሽላን ጎጂ የአረም ዘሮቹ ለብዙ አሥርተ ዓመታት በአፈር ውስጥ ተኝተው ሊቀመጡ ይችላሉ።
ከሳይንቲስቱ ገቢሳ ኤጄታ በፊት ብዙ የዓለም ቀደምት የእርሻ ሰብል ተመራማሪዎች አረሙን ለመቆጣጠር ብዙም ሳይሳካላቸው ለዓመታት ሞክረዋል።
ይህን የተረዱት ኤጄታ ገቢሳ እና የፑርዱ ዩንቨርስቲ የምርምር ቡድናቸው የማሽላ ተክልን የሚጎዳውን የአረም ዘር “ስትሪጋ አረም” (Striga weed) የሚባለውን ለይተው ካወጡ በኋላ ፣ ይህን አረም ከተኛበት የሚነሳበትን እንዲነቃቃ የሚያደርገው ከማሽላ ተክል የሚመነጭ የኬሚካላዊ Signal መኖሩን ለማወቅና ለመለየት ብዙ ምርምሮችን አካሄዱ። በምርምር ውጤታቸውም የ”ስትሪጋ አረም”ን የሚያነቃቁ “የኬሚካላዊ ምልክትን” (Chemical signals) የሚፈጥሩትን የማሽላ ዝርያዎችን እና “የኬሚካላዊ ምልክቱን” የማይፈጥሩትን ለይተው አገኙ።
[ Striga አረም ፣ በተለምዶ “ጠንቋይ አረም” በመባል የሚታወቅ ነው። ስሙም Striga የመጣው ከላቲን strī̆ga ሲሆን ፣ “ጠንቋይ ማለት ነው። በተፈጥሮ በአፍሪካ፣ በእስያ እና በአውስትራሊያ በከፊል የሚከሰት ጥገኛ የእፅዋት (parasitic plant) ዝርያ ነው። አንዳንድ የStriga አረም ዝርያዎች የእህል ሰብል በሽታ አምጪ ናቸው ]።
በጥናታቸው “የኬሚካላዊ ምልክቱን” የማይፈጥሩትን የማሽላ ዝርያዎች የ”ስትሪጋ አረም”ን መቋቋም መቻላቸውን ካረጋገጡ በኋላ ፣ የስትሪጋ አረምን መቋቋም የሚችል አዲስ የማሽላ ዝርያ ግኝታቸውን ለዓለም አስተዋወቁ።
በኋላም እነዚህን ዝርያዎች በማባዛት (breeding) በተለይ በአፍሪካ የ”ስትሪጋ አረም”ን መቋቋም የሚችል የማሽላ ዝርያ በማሽላ አርቢ ገበሬዎች ተስፋፍቶ በእጅጉ የማሽላ ተክል ምርት እድገትን ለማስገኘት አስችሏል።
እነዚህ አዳስ ዝርያዎች በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች እንኳን ከአካባቢው የማሽላ ዝርያዎች እስከ አራት እጥፍ የሚበልጥ እህል ያመርታሉ
Translated and presented on her
https://s7.addthis.com/static/standaloneExpandedMenu.html