ስለ ጨጓራ ካንሰር ይህን ያውቁ ኖሯል?

የጨጓራ ካንሰር መንስዔ

-ረጅም ጊዜ የቆየ የጨጓራ መብገን /ክሮኒክ ጋስትራይተስ/

-የጨጓራ ባክቴሪያ ሌላዉን የሰዉነት ክፍል አያጠቃም ፣ ለመኖር እንዲመቸዉ ጨጓራ ላይ ይጣበቃል፡፡

-የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራን አሲድ የመቋቋም አቅም ስላለዉ ለረጅም ጊዜ አሲዱን በማሟሟት ጨጓራ እንዲቆጣ እና ያንን መታከም ካልተቻለ ወደ ካንሰርነት ይቀይረዋል፡፡

ምልክቶች

-አብዛኛዉን ጊዜ ምልክት ላያሳይ ይችላል
-ምግብ አለመፈጨት
-ከእምብርት በላይ ያለ ሆድ ህመም
-ማስመለስ፣ ምግብ ሊሆን ይችላል አልያም ደም ማስመለስ
-ቶሎ መጥገብ
-ሆድ መነፋት
-ያለፍላጎት ክብደት መቀነስ ሊከሰት ይችላል፡፡

ህክምናዉ

-እንደ ደረጃዉ እና እንደሚያሳየዉ ምልክት ይወሰናል
-ደረጃዉ አንድ እና ሁለት ከሆነ ዕጢዉ ያለበትን የጨጓራ ክፍል ማዉጣት
-ኬሞቴራፒ

የሚያስከትላቸው ተጓዳኝ ጉዳቶች፡-

-ጉበትን በማጥቃት ጉበት እንዳይሰራ ሊያርግ ይችላል
-ቆሽትን፣ትልቁን እና ትንሹን አንጀት ሊያጠቃ ይችላል

ቅድመ ጥንቃቄ

-አመጋገብ ማስተካከል
-ጨዉ የበዛባቸዉ ምግቦችን መቀነስ
-በተለይ ሲ ፉድ የምንላቸዉ ምግቦችን መቀነስ
-ማጨስ ማቆም
-አልኮል መጠቀም ማቆም ይጠቀሳሉ፡፡

የባለሙያ ምክር

አመጋገብ ማስተካከል ይገባል፡፡
እድሜያችን ከፍ ሲል ከእምብርታችን በላይ አዲስ የሆነ ሆድ ህመም ካለ፣
ደም ማስመለስ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለምንወስዳቸዉ መድሀኒቶች ምላሽ የማይሰጥ ህመም ካለ፣ሰዉነት መቀነስ ካጋጠመ፣
ምግብ ቶሎ መጥገብ ካለ የጨጓራ ካንሰር ሊሆን ስለሚችል መታየት ያስፈልጋል፡፡

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አጠቃላይ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም እና የአንጀት እና ተያያዥ ጉዳዮች ህመም ስፔሻሊስት ከሆኑት ከዶክተር ቢኒያም ዮሀንስ ጋር በጨጓራ ካንሰር ዙሪያ ካደረግነዉ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ነው፡፡

ethiofm107.98

See also  “ወደ ጦር ግንባር አልሄድም፣ ትምህርት እፈልጋለሁ ብሎ መቅረት በአሸባሪው ህወሓት ያስገድላል”

Leave a Reply