በእውነቱ ተሰማከፔንሲልቫኒያ (አሜሪካ)

የግዕዝ (ኦ ይቅርታ) የአማርኛ ፊደል ሶስትሀ፣ ሐ፣ ኅ ሁለትዐ፣ አሁለት ‘ፀ’፣ ‘ጸ’ ይጠቀማል። በተጨማሪምግዕዝ፣ ካይብ፣ ሳልስ፣ ራብዕ፣ሀምስ ፣ ሳድስ እያለ በአንድ ፊደል የሚፈጥረውን ድምፅ ላቲን በሁለት ወይም ሶስት ፊደል Ha, Hu, Hi, Ha, Hè, Hee, Ho እያለ ይፈጥራል። ላቲን ‘ኘ’ ፊደል ስለሌለው በሶስት፣ አራት፣ አምስት ፊደል ነው ‘ኘ’ የሚለውን ድምፀት የሚያወጣው።

ለምሳሌ አንዱን እንይ:—-ኘ (Gne) ፣ ኙ (Gnu)፣ ኚ (Gnee)፣ ኛ (Gnaa) ኜ (Gnèè)፣ (Gno)የጳውሎስ ኞኞ አባት ስም በአማርኛ በሁለት ፊደል ቅልጥፍ፣ እምር፣ ሽክን ብሎ ይፃፋል። በላቲን ግን እንዴት ይፃፋል? አብረን እንይ Gnogno። መርቆሬዎስ! የሊቀ መላኩ ያለህ!!!! ስድስት ፊደል??? ኦሮምኛን ምን ነገር ውስጥ ነው የከቱት? ጎጠኞች፣ ዘረኞች አማርኛን በመጥላት ብቻ ብዙ ችግር ፈጥረዋል። ችግሩ አፍጦ እየመጣ እነርሱም መደበቂያ እያጡ ነው። በኦሮምኛ ቋንቋ ውስጥ ያሉ የአማርኛ ፊደል የሚፈጥራቸው ድምፆች (Sound) ላቲን ፊደል ውስጥ የሉም።

በምሳሌ ላስረዳ:– ማንም ፈረንጅ ወይም አፉን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የፈታ ‘ጠ’፣ ‘ጨ’፣ ‘ቀ’፣ ‘ጰ’፣ ‘ኘ’ ‘ፀ’ ‘ጸ’ ማለት ፈፅሞ፣ (እደግመዋለሁ) ፈፅሞ አይቻለውም። የአማርኛ ፊደል ታዳጊ ነው ለምሳሌ ‘በ’ እንጂ ‘ቨ’ አልነበረንም። ፈረንሳይኛ ስንማር ይሄ ድምፀት ጋር ተዋወቅን ፊደል ‘በ’ ላይ ከአናቱ ስርዝ ጨምረን ‘ቨ’ ን ፈጠርን። በኦሮምኛ በዳዳ ሲፃፍ ‘ዳ’ ምላስን የላይኛው የውስጥ ድዳችን ላይ በመለጠፍ የሚወጣው ድምፀት በግዕዝ ፊደል ላይ ስላልነበረ ‘ደ’ ፊደል ላይ ከላይ ክቡ ውስጥ ሰረዝ በመጨመር ድምፀቱን ፈጥረናል።

የ67ቱ እና የ68ቱ የዕድገት በሕብረት ዘመቻ በዚህ ረገድ ራሱን የቻለ ሪቮሉሽን ተካሂዶበታል። በምኖርበት ቀበሌ የመሰረተ ትምህርት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኜ የእኔ ቀበሌ የዩኒቨርስቲ እና የሀይስኩል መምህራንን አሰማርተን ከአዲስ አበባ አንደኛ ወጥቶ ተሸልሟል። ሰርቲፊኬትም ተስጥቶኛል። አሁን የምፅፈው ያኔ ካወኩት ያልተረሳኝን ብቻ ነው። በጣም ሰፊ ልምድ እና ዕውቀት ነው ያገኘሁበት። በተለይ አሁን አሜሪካ ነው ይባላል ታደስ የሚባል ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ መምህር የነበረ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል ።

አሁን ባገኘው ደስ ይለኛል።ሶስት ሀሁለት ፀሁለት አ መኖሩ ትክክልም ነው። ለኦሮምኛ X ን ጠ ማለት ይቀላል ወይስ የአማርኛውን ጠ መጠቀም???????????ሐዲስዓለማየሁሁለት አ ፣ ዐሶስት. ሀ፣ ሐ፣ ኅ አያስፈልግም ፣ አንዱን እንጠቀም ሲሉ ቆይተው ስማቸውን ሲፅፉ ከተከራከሩበት የሚጋጭ ተጠቅመው ከሽልማቱ ተቀንሶባቸዋል ሲባል ሰምቻለሁ። ሀይ ስኩል የአማርኛ አስተማሪዬ መሰሉኝ የነገሩኝ። አቤ ጉበኛ ግን መሞከር የለበትም ብሎ ሽንጡን ገትሮ ተሟግቷል። መጭው ትውልድ የኛን ሊትሬቸር አይረዳውም ብሏል።

የተለያዩ (ሀ፣ሐ፣)፣ (ዐ፣ አ) ለትግርኛ፣ ለኦሮምኛ፣ ለሶማልኛ ወዘተ የየራሳቸው አግባብ ይኖራቸዋልም ብሏል። በላቲን ኦሮምኛ ሲፃፍ ሶስት መቶ ገፅ የሚፈጅ መፅሀፍ በአማርኛ ፊደል (ይቅርታ በግዕዝ ፊደል) ሲፃፍ አንድ መቶ ገፅ ብቻ ይሆናል። ሶስት ቫወል የሚጠቀም grammatical structure ያለበት ቋንቋ በዓለም ላይ ኦሮምኛ ብቻ ነው።

ምናልባት ሶማልኛም ላቲን ፊደል ስለሚጠቀም ይኖረው ይሆናል። ሱማልኛ አማራጭ አጥቶ ነው። ኦሮምኛ ግን ለእንግሊዝኛም ሆነ ለፈረንሳይኛ በተለይ ለጣልያንኛ ተስማሚ የሆነውን የግዕዝ ፊደል ትቶ በላቲን መጠቀሙ ቋንቋውን እያቀጨጨው መሆኑን የቋንቋ ሰዎች ሲናገሩ ይሰማል። በበታችነት ስሜት የሚደረግ ነገር ለዚህ ዓይነት ክፉ ውጤት ያጋልጣል። የአራት መቶ ገፅ መፅሀፍ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሲሆን አያሳዝንም ትላላችሁ?????ይህንን ቁቤ የሚባል ጅል ነገር የፈጠሩት የጀርመን ቀጣፊ ሚሲዮኖች ናቸው። አፄ ኃይለስላሴ ፈቅደውላቸው ገብተው ኦነግን ፈጠሩ።

እነዚህ በስም ክርስትያን በተግባር ሰይጣን የሆኑ ፈረንጆች አሁን አሁን ዓይን አውጥተው፣ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ኦሮሞ ጥቁር ጀርመን ነው እያሉ ይፎግሯቹዋል። “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት”ከጀርመን ሰይጣን የቁጩ ክርስትያኖች ተቀብሎ ዶር ኃይሌ ፊዳም የወቅቱን በኮሙኒስቶች እንቅስቃሴ የተፈጠረ ሙቀት በየዋህነት ተከትሎ ማለትም ቻይናዎችም በላቲን ሊጠቀሙ ትንሽ ተንደፋድፈው የነበር መሆኑን፣ ሶማሌ በላቲን መጠቀሟን እንደ ፋሺን በመያዝ ቁቤን ደግፎ ጽሑፍ አዘጋጅቶ ነበር። ነገር ግን ከመሞቱ በፊት ተሳስቻለሁ ማለቱን ሰምተናል።ስህተትን ማመንና ማረም አስተዋይነት ነው። ካፈርኩኝ አይመልሰኝ በሚል በስህተት ውስጥ መዘፈቅ ቂልነት ነው

አዘጋጁ – ጽሁፉ የጸሃፊውን እምነት ብቻ የሚያንጸባርቅ መሆኑንና የተለየ አስተያየት ላለው ክፍት እንደሆን ማሳወቅ እንወዳለን። ሃሳብ አይገደብም


    Leave a Reply