“የሆነብንን ባንረሳም – ቁስል አካኪዎች አይደለንም”

በሚያምኑት መከዳት የሚከስተውን የልብ ስብራትና ስቃይ በደንብ አውቀነዋል።

አፍላ የወጣትነት ዘመንን ፈቅዶ ወዶ የመስጠት መልካምነታችን – ያስገኘልንን የጭካኔ ግድያና ዘግናኝ አይጠሬ በደሎች – አጥንት ድረስ ዘልቆ እስከሚሰማ ህመም ጋር ለታሪክ ይቀመጥ ብለናል።

የዛሬ ስምንት ወር ጥቅምት 24 እንደሆነብን መከዳት ፣ እንደደረሰብን ግፍና በደል ቢሆንማ ኖሮ………. ። እኛ ግን በኛ ከሆነው ይልቅ በምንወዳት ሀገራችንና ለሉዓላዊነቱና ክብሩ በቆምንለት ህዝባችን ሊደርስ የሚችለው ያሳስበናልና ቁስል አካኪ አንሆንም ብለን ፈተናዎችን በፅናት አልፈናቸዋል።

ዋንኞቹን የጥላቻ አቋማሪ ጋንግስተሮች የገቡበት ገደልና ዋሻ ገብተን ግንባር ግንባራቸውን እያልን ምሳቸውን ስናቀምሳቸው ያቆመን ኃይል እንዳልነበር ህዝባችን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚመሰክርልን ሀቅ ስለመሆኑ ቅንጣት አንጠራጠርም።

ለእነሱ መኖር በለጋነት የተቀጩ ልጆች ደም ምንም ሳይመስላቸው – ሲደረስባቸው ተንቦቅቡቀው በአዛውንትነታቸው – ቀሪ ጥቂት ዓመታትን መኖር ከመሻት ጉጉት እጃቸውን ያንከረፈፉትንም ዘብጢያ እንዲወርዱ ከማድረግ ያገደን አልነበረም።

“ያዙኝ ልቀቁኝ” በሚል ዕብሪት አገር አማን ብለን በተኛንበት ያሳረዱንን ከሃዲ የሽብር አባቶች በራሳቸው መንገድ ሄደን ዋጋቸውን ስንሰጣቸው ማንም ሊያቆመን እንዳልቻለ የትግራይ ገደሎች ተራራ ሸለቆዎች ህያው ምስክር ናቸው።

ጁንታው ገንጣይ አስገንጣዩና ሽብርተኛው ወያኔ – የፈረደባቸው የትግራይ እናቶች ቀሚስ ውስጥ እየገባ በመደበቅ እና በማድባት – ጭር ያለ ሲመስለው በገዛ ህዝቡ ላይ የዕልቂት ቲያትር እያዘጋጀ ሞት በማስተወን ህፃናት ጭዳ ሆነው ለክሴታ የሚያመች ሴራ እየጠነሰሰ ድል አገኘሁ የሚል ሀፍረተ-ቢስ አረመኔና ሰይጣናዊ ስብስብ ነው።

ታዲያ ዛሬ ላይ የገነባ የመሰለው ሁሉ እንደባቢሎን ግንብ በቅፅበት ዱቄት የሆነበት ይህ ከሃዲና ባንዳ ቡድን – “በድሮ በሬዬ ልረስ” እያለ ነው።

ያም አዙሪታምና ኢትዮጵያን ገዳይ የሆነ ፊት ለፊት ሳይሆን እንደ ልማዱ – በእናቶች ቀሚስ ውስጥ አየገባና እየወጣ መከረኛ ህዝቡን ቀብድ ያስያዘ ቁማር።

ይሄ ቁማር ደግሞ ኢትዮጵያንም ሆነ ጀግናውን ሠራዊት በዚህ ዘመን አይመጥንምና አጫዋች ስለማያገኝ ካዋጣው እዛው የጓዳ አይጥነቱን ይቀጥል። ይህ ሲባል የትግራይ ህዝብ ይሁን ብሎ ከፈቀደለት።ህዝቡ ደግሞ የሚያዋጣውን ጠንቅቆ ያውቃል ብለን እናስባለን።

በነገራችን ላይ ወያኔ የራሱ የሆነ ነገር የሌለው ሁሌም የሌሎችን የራስ በማድረግ የሌባ ዓይነ- ደረቅነት የተሞላ ብቻ ሳይሆን በበታችነት ስሜት የሚያሰቃየውን ህመም ከመታከም ይልቅ ሌሎችን ሰላም በመንሳት የመፅናናት ባህል ያዳበረ እኩይ ነው።

ሌላው ቀርቶ መለያው /ብራንዱ/ ያደረጋቸው ሽርጥ፣ቁምጣ፣ኮንጎ ጫማ ጭምር ከህዝባዊ ግንባር ኮርጆ የኔ ነው በማለት የገገመ ሀሳዊ ነው። እናም እነዚህ እንኳን የሱ ካልሆኑ ሌላ ምን የሱ ሊሆን ይችላል።

ለማንኛውም እኛ የሆነብንን ሁሉ – በጁንታው ክህደት የደረሰብንን ሁሉ – ለታሪክ አስቀምጠን ቁስል ባለማከክ አርቆ አሳቢነት ታላቋን ኢትዮጵያ አሻግረን እንመለከታለን።

በማንኛውም ጊዜ ለመላው ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ሉዓላዊነት ክብር አንድነትና ታላቅነት ዛሬም እንደወትሮው በፅናት ዘብ ቆመናል።
“ይብላኝ” አቧራውን ማራገፍ እንኳን ለማይችለው – ሽብርተኛ ወያኔ እያልን።

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች”

ሻምበል አስቻለው ሌንጫ Defence force FB

Leave a Reply