የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከ700 ሺህ በላይ ኩንታል የምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን አስታወቀ። መንግስት ይህን እያደረገ ” ረህብን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ያደርጋል መባሉ አሳዛኝ ነው”
ካለፈው ወር አንስቶ በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የቆዳ ስፋት በአጋር አካላት ቀሪው 14 በመቶ ደግሞ በመንግስት እንደሚሸፈን መገለፁ ይታወሳል። ይህ እውነት እያለ ነው መንግስት እርዳታን ለፖለቲካ እንደሚጠቀም የሚገለጸው።
በዚህም መሰረት ምዕራብ ዞን፣ ደቡብ ዞን አምስት ወረዳዎች፥ በመንግስት የሚሸፈኑ ሲሆኑ ደቡብ ሶስት ወረዳዎች፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና የመቐለ ከተማ ደግሞ በአጋር አካላት የሚሸፈኑ መሆናቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንዳሉት ኮሚሽኑ በግጭትም ሆነ በሌሎች የአደጋ ክስተቶች ተጎጂ ለሆኑ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ያደርጋል።
ኮሚሽኑ በአማራ፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጊዜያዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በትግራይ ለ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የሶስተኛ ዙር ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ በመንግስትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ጥምረት እየተሰጠ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ቀደም ሲል ድጋፉ 70 በመቶ በመንግስት ቀሪው 30 በመቶ በአጋር አካላት ይቀርብ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ 86 በመቶ በአጋር አካላት 14 በመቶ ደግሞ በመንግስት እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል።
እስካሁን ባለው ለትግራይ ክልል 772 ሺህ 954 ኩንታል እህልና 289 ሺህ 339 ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ መላኩንም ጠቁመዋል።
ኮሚሽኑ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ኀብረተሰቡ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ኮሚሽኑ በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችም መሰል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ 124 ሺህ 49 ኩንታል እህል እንዲሁም በአማራ ክልል አጣዬ የተፈናቃዮች 32 ሺህ 520 ኩንታል ምግብ ተልኳል ብለዋል።
በዚህ መረጃ መሰረት መንግስት አስራ አራት በመቶ የሚሆነውን የቆዳ ስፋት ብቻ ለይቶ እርዳታ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ ረሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ እንዳዋለው ተደርጎ የሚነገረውን ዜና ውድቅ እንደሚያደርገው ባለሙያዎች እርዳታ ከሚሰጡትና ሃሰት ሪፖርት ለሚያደርጉት ክፍሎች አስታውቀዋል።
86 መቶኛውን የትግራይን የቆዳ ስፋት እርዳታ የሚመሩት ወገኖች ስለምን እንዲህ ያለውን ቅጥፈት ይናገራሉ? ለሚለው ምላሹ ሌላ እንደሆነና ሕዝብን ዛሬ ላይ ተንቅቆ እንደሚረዳው ባለያዎቹ አመልክተዋል።
- “አብይ ባህር ዳር እንዳይመጣ ለማስጠንቀቅ ቦንቦች አፈንድተናል” ፋኖ – አብይ በባህርዳር ድልድይ መረቁበአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የ380 ሜትር ርዝመትና 43 ሜትር ስፋት ያለው ግዙፍ ድልድይ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ጠቅላይ… Read more: “አብይ ባህር ዳር እንዳይመጣ ለማስጠንቀቅ ቦንቦች አፈንድተናል” ፋኖ – አብይ በባህርዳር ድልድይ መረቁ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?