December 3, 2021

መረራ ” ጃዋር እየመከርኩት የኦሮሚያን ፖለቲካ አመሳቀለው”

ፎቶ – መረራ ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ በአምቦ ስታዲዩም የህዝብ ጎርፍ ሲቀበላቸው፣ ንግግር ማድረግ አቅቷቸው ባለቀሱበት ወቅት በኦሮሞ ጀግንነት ማዕረግ አጊጠው የተነሱት ምስል ነው – ፎቶ አዲ ስታንዳርድ

የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ጃዋር መሐመድን እስር ቤት ሄደው የማይጎበኙበትን ምክንያት ገልጸዋል። የኢትዮ12 የአዲስ አበባ ዘጋቢ መረጃውን ያገኘው ዶክተር መረራ ጉዲና ” ጓደኛህ ” ሲሉ ቅሬታቸውን ከገለጹለት አካል ነው።

ከመረራ ጋር የተገናኘው የመረጃው ባለቤት እንዳለው ጃዋርን ለመጎብኘት ወደ ማረሚያ ቤት አምርቶ ነበር። ከዛ ሲመለስ ዶክተር መረራን ያገናቸዋል። ማረሚያ ቤት ጃዋር መሀመድን ለመጠየቅ መሄዱን፣ እዛም ሄዶ ” ጃዋር አሞታል ሰው ማግኘት አይችልም” የሚል ምልሽ እንደተሰጠው ያጫውታቸዋል። አስከትሎም ” ለምን አይጠይቁትም? አሞታል አሉኝ” ይላቸዋል።

ዶክተር መረራ ” ጓደኛህ የኦሮሚያን ፖለትካ አመሳቀለው። ስመክረው እምቢ ብሎ ሁሉንም አበለሻሸው” አሉና ጀመሩ። ከዛም ” አልጠይቀውም። ወደፊትም አላደርገውም” ሲሉ በጃዋር ግፊት የኦሮሚያ ፖለቲካ መበላሸቱ እጅግ እንዳናደዳቸው መግለጻቸውን የመረጃው ባለቤት አስታውቋል። አስፈላጊ ከሆነ በአካል ወጥቶ እንደሚናገር አስታውቆ መረጃውን የሰጠው አካል አሁን ከተሰራጨው የመንግስት ምስረታ ሰነድ ጋር ጃዋር አለበት ብሎ እንደማያስብም አመልክቷል።

“የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት አዋጅ” በሚል የተሰራጨው ሰነድ በመግቢያው እንደሚለው “የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት (ኦብክሽመ) ለማቋቋም አዋጁን ያዘጋጁት ኦነግና ኦፌኮ ናቸው።

ከትግራይ ቀውስ ጋር በተያያዘ የውጭ መንግስታት፣ ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች ከፍተኛ ጫና በሚያደርጉበት ወቅት በኦሮሚያ ምርጫውን እንደማይቀበሉ ጠቅሰው የሽግግር መንግስት ያቋቋሙት ሁለቱ ድርጅቶች ሃሳባቸው በመላው ኦሮሚያ ተቀባይነት ስለማግኘቱ እስካሁን የተሰማ ነገር የለም። ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት መረራ ሰነድ አዘጋጅተው ለአሜሪካ መንግስት ማቅረባቸው ተሰምቶ ነበር። ” ጨዋታው ትህነግን ዳግም ወደ ፊት የማምጣቱ ስትራቴጂ” አካል ስለመሆኑና የውጭ ሃይሎች እንዳሉበት እየተተቆመ ነው። ከዚህ ሰነድ ዝግጅት ጋር በተያያዘ እንዴት እየተመከረበት እንደሆነ በርካታ የክልሉ ተጽዕኖ ፈታሪዎች ያውቃሉ። እነዚህ ክፍሎች እንዳሉት ጉዳዩ በፓርቲ ደረጃ በስሎ የተወሰነ እንዳልሆነም እየገለጹ ነው። ወደፊት በዝርዝር እንመለስበታለን።አቶ ታዬ ደንደአ ግን “ሽግግር የሚባል Joke የለም!” ሲሉ ባጭሩ ዜናውን ቀልድ ሲሉ በግል የፌስ ቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።

“በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል ነፃ ምርጫ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ህዝብ ከለሊት እስከ ለሊት ተሰልፎ የሚፈልገዉን መርጧል! ባዳዎችን ተማምኖ ከምርጫዉ ራሱን ያገለለ ባንዳ ደግሞ በምርጫ ማግስት “የሽግግር መንግስት” እያለ ይቀልዳል! አሁን ላይ ነገሮችን ግልፅ ማድረግ ያስፈልጋል! በኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ ስልጣን አይቀለድም! የነፃነትን ድንበር በመጣስ ሀገርን አተራምሶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት በማጥፋት ተጠርጥሮ የታሰረ እጩ ወንጀለኛም ከህግ ውጭ በግርግር አይፈታም! “ሽግግር” የሚባል የባዳና የባንዳ ቀልድ አይሰራም!” ሲል አቶ ታዬ አመልክተዋል።

እሳቸው ይህንን ቢሉም በሌላ አውድ በኦሮሚያ ክልል ኡዕርቅ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል። መረጃውን ያቀበሉንን ይዘን ይመከታቸዋል ያልናቸውን ፈልገን ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ ” ስራችንን አታበላሹ” ሲሉ ዝምታን እንድንመርጥ ነግረውናል። በኦሮሚያ ሁሉንም ወገን የሚያስገርም የዕርቅ ዜና እንደሚሰማ ግን እምነታቸው መሆኑንን አልሸሸጉም።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት አዋጅ

መቅድም

1. የኦሮሚያ አሁናዊ ሁኔታ

የኦሮሚያ ህዝብ ለብዙ ዘመናት ያጣዉን የአገር ባለቤትነትን መልሶ ለመጎናጸፍ በጠላቶቹ የተነጠቀዉን መልሶ መቀዳጀት በአጠቃላይ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰን መራራ መጽዋቶችን እየከፈለ ዛሬ ላይ ደርሷል ፡፡

ትግሉ በፖለቲካዊ ተቋም የኦሮሚያን ህዝብ አንድነትና ቅንጅትን ባማከለ መልኩ በኦነግ መመራት ከጀመረ ጊዜ ወዲህ እንኳን የተከፈለዉ ዋጋ በእጅጉ ብዙ ነዉ፡፡

ከ2015 ወዲህ በኦሮሚያ ህዝብ ከፍተኛ ተጋድሎ በተለይ በተለይ በታጋዮች ቄሮች በተደረገዉ ከፍተኛ የነጻነት ፍልሚያ የብዙ ሺህ ሰዎች ህይወት ጠፍቶኣል፤አካል ጎድሏል ፡፡ከፍተኛ ግምት ያለዉ ንብረት ወድሟል፡፡ ትግሉ በወቅቱ በድል ቢጠናቀቅም ቅሉ ውሎ ሰያድር ያልተጠበቀ አቅጣጫ እንዲይዝ ተደርጓል፡፡

የ2018ቱ የርፎርምና ጥገና ፖለቲካ በኢትዮጵ የዲሞክራሲን ጭላንጭል በማሳየት የህዝቦችዋን መብት በማስከበርና በማክበር ወደ ዴሞክራሲያዊነት የሚያሻግር ተደርጎ የተወሰደ ነበር፡፡ነገር ግን በተፈለገዉ መንገድ፤ በተጠበቀዉ መልኩ ያን ክስተት አላመጣም፡፡አንዳንድ የፖለቲካ አካላት ሁኔታዉ ከጅማሮ መሰረቱን እንዳይለቅና አስተማማኝ እንዲሆን ሀገር አቀፍ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ሙከራ ሲያደርጉም ነበር፡፡

ከእነዚህ አንዱ አንድነት ለህዝቦች ነጻነትና ዴሞክራሲ (AFD) የሚባለዉና ኦነግ በአባልነትና በዋና መስራችነት የሚገኝበት ቅንጅት ነዉ፡፡ ዳሩ ግን አልተሳካም፡፡ከመንግስት አካል የለውጡ አቀጣጣይ በማድረግና ቀጣይነት ያለዉ የዴሞክራሲ ስርአት የሚገነባ በማስመሰል በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራዉ ቡድን ሲወጣ የፖለቲካ ተቋቋማትና የኢትዮጽያን ሁኔታ በቅርቡ የሚከታተሉ ሃገራት ጭምር ለዉጡ እዉን የሚሆን መስሎአቸዉ ደግፈዉት ነበር፡፡በዚህ ሁኔታ ነበር እንግዲህ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል ምንም አይነት የፖለቲካ ስምምነት ሳይደረግ ገዥዉ ፓርቲ እስከ 6ኛዉ የ2020 ብሔራዊ ምርጫ ድረስ እንዲደርስ የተደረገዉ

ባለፉት ሶስት አመታት የዶ/ር አብይ መንግስት በፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ላይ የወሰደዉ የማዋከብ፣ የመግፋት እርምጃዎች የነበረዉን ተሳትፎና ዝግጅት እንዲሁም የዉድድር መንፈስን ሙሉ በሙሉ አጨልሞት አለፈ፡፡

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉት ቀድሞዉንም የዲሞክራሲ ሰነ ምህዳርን በእጅጉ ተጭኖት የነበረዉን መንግስት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመስፋፋቱና ያንን በመጠቀም ያለበቂ ጥናትና መረጃ ወረርሽኙን ምክንያት በማድረግ የ2020ን ምርጫ ወደ 2021 እንዲተላለፍ አደረገ፡፡ በመሆኑም በህገ መንግስቱ የተገደበዉን የመንግስት ስልጣን አራዘመ፡፡ኦነግ፣ ኦፌኮና መሰል ደጋፊዎች ይህን የመንግስት ስልጣን በኢ -ህገ መንግስታዊ አካሄድ የማራዘም ስልት ነዉ በማለት በግልጽ ተቃዉመዋል፡፡ መጣ የተባለዉም ለዉጥ ሁሉን አቀፍ ደሞክራሲያዊ ሽግግር ያመጣል ተብሎ ቢጠበቅም ዉሎ ሳያድር በመንሸራተትና ቀድሞ ከነበረዉም በማነስ የግፍ አረንቀዋ ሆኖ ዐረፈዉ፡፡ የህዝቡም ጥያቄ መልስ አጣ፡፡ ይልቁንም በብዙ መሰዋዕትነት የተገኘዉ፤ብዙ ህይወትና ደም ተገብሮበት የታየዉን የለዉጥ ጭላንጭል በማዳፈን በስመ የታላቁዋ ኢትዮጵያ አንድነት ግንባታ ያረጀዉን ስርአት መልሶ የመገንባት ተግዳሮቶች ላይ በመጠመዳቸዉ በነበረዉ የሽግግር ተስፋ ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ቸልሰዉበት አለፉ፡፡ በመሆኑም የለዉጥ መንግስት ነኝ ባዩ የአድር ባዮች፣ የግብዞችና ምንም ዓይነት ህዝባዊ ዐጀንዳ የሌለውና ዐላማው ህዝባዊ ያልሆነ ስብስብ መሆኑን በገሃድ አሳየ፡፡

ኦነግ እና ኦፌኮ ይህ ጉዳይ በግልጽ ክህደት መሆኑን በመግለፅ ህጋዊ አለመሆኑን ጠቅሰው ሁኔተው የህዝቦችን አበሮነት የሚያፈርስ ነው በማለት በግልፅ ተቃውመውታል፡፡ መንግስትም አካሄዱና አላማውን በመቀየር ህዝባዊ እንዲሆንና የህዝብን መሰረታዊ ነጻነትና ዲሞክራሲያዊነት እንዲያረጋግጥ ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የኦሮሚያ ህዝብና ኦሮሚያ በከፍተኛ ችግር ዉስጥ ናቸዉ፡፡ ለይስሙላ ካልሆነ በቀር ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ አንድም መንግሰታዊ ተቁዋም የለም፡፡ ኦሮሚያ ላይ ጦርነት ታዉጆ የጦር አዉድማ በመሆን በየቀኑ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችዋን ህይወት እየገበረች ትገኛለች፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ጦርነት በህዝቡ ላይ ተከፍቶ ይገኛል፡፡ ከአገር ዉስጥ ከመከላከያ ኃይል በተጨማሪ የኤርትራ ጦር በየቦታዉ ተሰማርቶ ህዝቡን እየወጋ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ኦሮሚያ በአብዛኛዉ አካባቢ የጦር አዉድማ ሆናለች፡፡ህዝቡ ከቀየዉ እየተፈናቀለ ነው፡፡የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ጎጆዎች በእሳት እየጋዩ ነዉ፡፡ከብቶቻቸዉንና ንብረቶቻቸዉን እየዘረፉአቸዉ ነዉ፡፡ ሴቶችን ለመግለጽ በሚያዳግት መልኩ እየደፈሩ ነዉ፡፡ እስራትና እንግልት ከመስመር የወጣ ነዉ ፡፡በተለይ ቄሮና ቀሬ መንገድ ላይ መዘዋወር አይችሉም፡፡ በተገኙ ጊዜ ይደፈራሉ ይደበደባሉ ፡፡ ይህ እንግልት አንገሽግሾት ለትግል ጫካ የገባዉም ስፍር ቁጥር የለዉም ፡፡በመሆኑም ህግ የሚባል ነገር የለም ፡፡ መንግስት ነኝ ባዩ የመሳሪያ አቅም ስላለዉ ብቻ የሚባለዉን ማድረግ ይችላል፡፡ነገር ግን ተጠያቂነት የሚባል ነገር የለም ፡፡

ባጠቃለይ ኦሮሚያ ዉስጥ መንግስት የሚመስል ነገር እንጂ በእዉኑ መንግስት የሚባል አካል የለም፡፡

አሁን በብልጽግና ስም አገርን አስተደድራለሁ የሚለዉ መንግስትና ፓርቲዉ አምባገነን ነዉ፡፡ የብጽግና ፓርቲን የመሰረቱት የቀድሞ የኢህአዴግ/ሕወሐት ሰዎችና ደጋፊዎቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ከዚህ አካል የተቀነሰዉ የህወሐት አካል ብቻ ነዉ ፡፡ ከዚህ በፊትም እንደተገለጸዉ ከዚህ በፊት ከህወሐት ጋር በመሆን ለግላቸዉ ብልጽግናና ለግላቸዉ ጥቅም በቻ የኦሮሚያን ሕዝብ መብትና ጥቅም አሳልፈዉ የሸጡት አካላት ናቸዉ ስማቸዉን በመቀየር ብልጽግና በማለት ብቅ ያሉት ፡፡አሁን ብልጽግና ነን የሚሉት ስበቦች የነበረዉን የግፍ ስርአት የመብት ረገጣና የስብእና ማበላሸት ዉርስ በማስቀጠል ብሎም የበለጠ በማባባስ ያሉ ናቸዉ፡፡

በስም ብቻ የነበረዉን የፌደሬሽን ጉዳይ ከነ አካቴዉ ለመደምሰስ ታጥቆ የተነሳ አካልም ነዉ፡፡ ከአንድ ተኩል ምዕተ አመት በላይ የቆየ፣ ያረጀና ያፈጀዉን ስርአት መልሰዉ ለመገንባትና በሙሉ ህልዉናዉ ለማስቀጠል የሚለፉ ንፉጋን ናቸዉ፡፡ ባጠቃላይ የኦሮሚያ ህዝብ እኩል መብት ካገኙ አገር ትፈርሳለች የሚሉ ናቸዉ፡፡

በመሆኑም የህዝብን መብት በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ማስከበር አይቻልም አይታሰብምም ፡፡

አሁን ያለዉ መንግሰት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን ለማፍረስና ህዝቡንም ለመከፋፈል ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን ጉዳይ ለማስፈጻም ይመቸኛል የሚሉትንና ጥቅም አደር ሰዎቻቸዉን በማሰበሳብ በሁሉም የኦሮሚያ አከባቢዎች ህዝቡ መሃል በማስገባት ግፊት እያደረጉ ነዉ፡፡ ነገሩን ከግብ ለማድረስ በቅድሚያ ሁኔታ ህዝብ ከመንግስት ማግኘት የሚሻዉን አገልግሎት በመንፈግ ጫና እየደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ መንግሰት የኦሮሚያን ህዝብ ከመግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት የዘለለ አንድም ህዝቡን የሚደግፍ ታሪክ የለዉም፡፡ የህዝብ መንግስት ነኝ ቢልም ቅሉ ህዝባዊነት አይተይበትም፡፡ የህዝብ ጥቅምን አሳልፎ የሚሻጥ ዋልጌ ነዉ፡፡

ባጠቃላይ ኦሮሚያ ለአንድ መቶ አምሳ ዓመታት ያህል በ አገዛዝ ስር ከወደቀች ጊዜ ጀምሮ አንዴም ለህዝቡ የሚሆን መንግሰትና የመንግስት አስተዳደር አግኝታ አታዉቅም፡፡ይህ የኢትጵያም እጣፈንታ ሆኖ ቆይተል፡፡

6ኛዉ አገራዊ ምርጫ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ፡፡ በኦሮሚያ ምርጫዉ የዉድድር ሳይሆን የብቻ ግልቢያ ነበር፡፡ ተወዳደሪ አልነበረዉም፡፡የኦሮሞ ግዙፋን ፓርቲዎች ኦነግና ኦፌኮ ተገፍተዉ የወጡበት ምርጫ ነበር፡፡ አመራሮቻቸዉም፤ አበላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸዉም ጭምር በእስር ላይ ሆነዉ ነዉ ምርጫ ተብየዉ ተካሄደዉ፡፡የእነዚህ ሁለቱ ፓርቲ ቢሮዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ተዘግትዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች የምርጫዉ ሂደት ፍትሃዊ እንዲሆን የተቻላቸዉን ሁሉ ሲያደርጉ ነበር፡፡ ምርጫዉ በታለመዉ መልኩ መካሄድ አንደማይቻል ከተገነዘቡ በኃላ ሁሉን አቀፍ ዉይይት እንዲደረግና ፖላቲካዊ መፍትሄ እንድደረግ ተደጋጋሚ ጥረቶችን ሲያደርጉና ጥሪዎችን ሲያደርጉ ቆይቱዋል፡፡ ያ ቅቡልነት የሌለው ምርጫ ከተደረገ በሁላ መፍትሄ አለመሆኑን በመጠቆም መፍትሄው ከሁሉም ተቋማትና ፓርቲዎች የተውጣጣ ጊዜያዊ አድን መንግስት እንዲቋቋም ጥሪ አድርጓል፡፡

ህዝቡ አገር አጥቱዋል፡፡ህዝቡ መብት አጥቶዋል፡፡ህዝቡ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን ዕድል ተነፍጉአል፡፡ነፃነትና ድሞክራሲን ተጠምቱአል፡፡ህዝቡ ሰላም እየፈለገ ሁሌም በሁከት ውስጥ እየዋለ ይገኛል፡፡ ለሱ እንደመታገል እሱን የሚታገል መንግስት ስለገጠመው አሁን ህልውናውን የሚጠብቅለትን መንግስት ይፈልጋል፡፡ የኦሮሚያ ህዝብ ለሱ የሚሆን መንግስት በሚፈልገው መልኩ እንዲቋዋቋምለት በተለያየ መንገድ ጥረት እያደረገ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአገሪቱ ፖላቲካ ስርዓት ይዞና ሰፍኖ ህዝቡን የሚወክሉት በህግ እሰኪመርጥና የራሱን ቅቡል መንግስት አስከያቋቁም ድረስ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋምለት ይፈልጋል፡፡ ካሉት አካላትና ይህንን ሊያደርጉ ይችላሉ ተብለዉ ከሚወሰዱት አንጋፋና ተመራጮቹ ኦነግና ኦፌኮ መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ከተመሰረቱበት ጊዜ ጀምሮ ለኦሮሚያ ህዝብ ብሎም ለሌሎች ብሄሮች መብት መከበርና መጠበቅ እየተፋለሙ የቆዩና አሁንም ድረስ የቀጠሉ ናቸዉ፡፡

በመሆኑም ኦነግና ኦፌኮ አሁን ያለዉን የአገሪቱን ፖላቲካ በጥልቀት ከጤኑና ከመረመሩ በኃላ ከምሁራንና ከሰፊዉ ህዝብ ጋር በመወያየት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት(ኦብክሽመ) አቋቁመዋል፡፡ ይህ መንግስት ህወሀት ተመልሶ የትግራይን ክልል በኃይል በመያዝና መንግስት መሆናቸዉን ባወጁበትና የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ዉጥንቅጡ በመጣበት በዚህ ወቅት ኦሮሚያ ዉስጥ ተጨማሪ የፖለቲካ ኪሳራ በመድረስ ሌላ ዉድመት እንዳይመጣ ለመከለከል ሲባል የተወሰደ ግዴታ ነዉ፡፡

ስለዚህ ይህ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት(ኦብክሽመ) ከሃምሌ 1 /2021 ጀምሮ ህጋዊ የህዝብ መንግስት በህዝብ ይሁንታ በህግና በምርጫ እሰኪመሰረት ድረስ ለሶስት አመታት ተቋቁሟል፡፡

2. የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት (ኦብክሽመ) እሴቶች

ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች የሚበሉትንና ኢትዮጲያም ፈርማ የተቀበለቻቸዉን መብቶች መቀበልና ማክበር እንደለ ሆኖ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት(ኦብክሽመ) በዚህ በሽግግር ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አሴቶች ያከብራል፤ ይጠብቃል ይመረበታልም፡፡

ሀ) የህዝብ የበላይነትና ነጻነት፡- የኦሮሚያ ህዝብ ነጻና ከሽግግር መንግስቱም በላይ የስልጣን በላቤትና ወሳኝ መሆኑን ያከብራል፤ ይጠብቃል፡፡

ለ) ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፡- ኦብክሽመ የኦሮሚያን ህዝብ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያከብራል፤ ይጠብቃል፡፡

ሐ) የፆታ እኩልነት፡- ኦሮሚያን ህዝብ የፆታ እኩልነት ያከብራል፤ይጠብቃል፡፡

መ) የኢፌዴሪና የኦሮሚያ ህገመንግሰቶች፤- የኢፌዴሪና የኦሮሚያ ህገመንግሰቶች ከየትኛዉም የኦሮሚያ ህግ በላይ መሆኑን ያምናል፤ ይጠብቃል፡፡ በመሆኑም የትኛዉም ኦብክሽመ የሚያወጠቸዉ ህግጋቶች ይህን ህገመንግስት የሚጸራሩ ከሆኑ ተቀባይነት የለቸዉም፡፡

ሠ) የመንግሰትና የእምነት ልዩነት፡-ኦብክሽመ በኦሮሚያ ዉስጥ እምነትና መንግስት የተለያዩ መሆናቸዉን ያምናል፤ ይጠብቃል፡፡ የመንገስት የሆነ እምነት የለም፡፡ መንግስት በእምነት ጉዳይ ዉስት ጣልቃ አይገባም፡፡እምነትም በመንግስት ጉዳይ ዉስጥ አይገባም፡፡

ረ) የብሄሮች(ብሄራሰቦች) መብት፡- ኦብክሽመ ኦሮሚያ ዉስጥ ያሉትን ብሄሮች(ብሄራሰቦች) መብት ያከብራል፤ይጠብቃል፡፡

ሰ) የፍርድ ቤቶች ነጻነት፡- ኦብክሽመ ዉስጥ ፍ/ቤቶች ነጻ ይሆናሉ፡፡

ሸ) የመንግስት ግዴታዎች፡- ኦብክሽመ መንግስት የተጣለበትን ግዴታዎች በሙሉ በግልጽነትና በሙሉ ኃላፊነት ይወጠዋል፤ በሚፈጠራዉ ግድፈትም በህግ ተጣያቂ ይሆናል፡፡

ቀ) የስልጣን ክፍፍል፡- ክልሎች፤ ብሄራዊ ክልሎችና ከፌዴራል መንግስት ጋር ህገመንግስታዊ የሆነ የአስተዳደር ትብብር ይኖራዋል፡፡

በ) ቀጠናዊ ትብብር ማጠናከር፡- ዴሞክራሲ፤ ድህንነት፤ አስተማማኝ ሰላም ብሎም ልማትና ትብብርን በማተናከር በአፍሪካ ቀንድ የንግድ መስመርን ቀጠና ለማድረግ እንዲሁም በቀጠናዉ ያለዉን ግጭት በድርደር ለመፍታት ይተጋላል፡፡

3. የኦብክሽመ መዋቅር

3.1) የኦብክሽመ የሽግግር ጨፌ፡- ከኦነግና ከ ኦፌኮ እንዲሁም ከሲቪል ተቋማት በሚወጡት አበላት የሚመሰረት ሲሆን 337 የጨፌ አባለት አሉት፡፡ ይህ የሽግግር ጨፌ አንድ ፕሬዝዳንትና ሶስት ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ከራሱ ከጨፌዉ በመምረጥ ይተዳደርበታል፡፡

3.2) ኦብክሽመ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እሰከሚተካ ህዝብ የሚያስተዳድር ሲሆን የስልጣን ዘመኑም ከሶስት ዓመት አይበልጥም፡፡

3.3) ኦብክሽመ አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ ይኖሩታል፡፡ እንዲሁም አሰፈላጊ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፤ አፈጉባኤዉ የሽግግሩን ጨፌ ስብሰባ ያካሄደል፤ይመራል፡፡

3.4) ኦብክሽመ በክልል፤በዞን፤ በወረዳና በቀባሌ ደረጀ የተዋቀረ ነዉ፡፡ ነገር ግን ኦብክሽመ አሰፈላጊነቱን ባመነ ጊዜ ሌላ የአሰተዳደር እርከን ማዋቀር ይችላል፡፡

3.5) የኦብክሽመ የህግ አዉጪ አካል የኦብክሽመ ጨፌ ነዉ፡፡ ጨፌዉም የሽግግር መንግስቱ የላይኛዉ የስልጣን አካል ይሆናል፡፡

3.6) የህግ አስፈጻሚዉ የበላይ አካል የክልሉ የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳነት ሲሆን ተጠሪነቱ ለኦብክሽመ ጨፌ ነዉ፡፡

3.7) ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱ የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈጻሚ የበላይ ተቆጣታሪ አካል በመሆን ይመራል፤ ምክትል ፕሬዝዳንቶቹን የተለያዩ ክፍሎች ተጣሪዎችን ፤ የቢሮዎችንና በተለያዩ ደረጃ ለክልልና ለዞኖች አሰተዳደሪነት በፓርቲዎች አቅራቢነት የሚቀርቡትን ሹማምንቶች ፤ ባለሙያዎች ለሽግግሩ ጨፌ በማቅረብ ያስወስናል፤ የተለያዩ መመሪዎችን በማዉጣት ለአስፈጻሚዎች ይሰጠል፡፡

3.😎 በዚህ በሽግግር ወቅት ከዚህ ቀደም ለህዝብ አገልግሎት የተዋቀሩት የመንግስት መዋቅሮች አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ፡፡ በክልሉ ዉስጥ የተጀመሩ ፕሮጄክቶች ያለ ምንም እንቅፋት የጀመሩትን የልማት ስራዎች እንዲቀጥሉ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡

3.9) ኦብክሽመ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፤ ከተባበሩት መንግስታት፤ የአፍሪካ ህብረት፤ የተለያዩ ሀገራት ድፕሎማቶች፤የአውሮፓ ህብረት፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ለሰብአዊ መብቶች የሚሞግቱ ድርጅቶች እንዲሁም ከኦሮሚያ ጋር ትብብር ካላቸው ድርጅቶች ጋር በቅርበት ይሰራል፡፡

3.10) ኦብክሽመ ከሌሎች ክልላዊ መስተዳድሮች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ስረኣት ስለመደረጉና ከምንም የፖለቲካ ሻጥር ነፃ መሆኑን ከቀጠናዊ አካላት ማለትም ከአፍሪካ ህብረት፤ አውሮፓ ህብረት፣ለሰብአዊ መብቶች የሚሞግቱ ድርጅቶች፣ ከአምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ሁማን ራይት ወች፣ከታዋቂ ግለሰቦች፣ምሁራን በግልና በጋራ መጥተው እንዲታዘቡ በማድረግ በምስረታው ውስጥ የራሱን ድርሻ የወጣል፡፡

3.11) ኦብክሽመ ፊንፊኔ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅቶች (በወል፣በጋራ፣በማህበር) ከሚዲያ ተቁዋማት ጋር በመሆን ድሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት፣መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ፈጣን ኢኮኖሚንና እድገትን እውን ለማድረግ ይሰራል፡፡

4. የሽግግር ወቅት ፕሮግራም

ኦብክሽመ የኦሮሚያን ህዝብ ሠላም፣ፖለቲካ፣ኢኮኖሚ፣ማህበራዊ ጉዳችን አስመልክቶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በልዩ ትኩረት ይፈፅማል፡፡

4.1. የህዝብ ሰላምና መረጋጋት፡ ኦብክሽመ የኦሮሚያ ህዝብ ለረዥም ጊዜ ያጣውን ሰላም ለመመለስ ይሰራል፡፡

ሀ) ከኦሮሚያ መንግስትና ህዝብ ጋር የሚጎራበቱ ሌሎች የክልል መንግስታትና ህዝብ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በቅርበት በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሰላምና መረጋጋትን ያረጋግጣል፡፡

ለ) የህዝብ ሰላምን ሊያውኩ የሚችሉትን ቀድሞ በመተንበይ ችግር ሳይፈጠር ከራሱ ከህዝብ ጋር በመሆን መፍትሄ እንድያገኝ ይሰራል፡፡ችግር በተፈጠረበት አካባቢም የሰላም አስከባሪ አካል በፍጥነት በምግኘት ከህዝብ ጎን በመቆም ሰላም እንድያሰፍን ይሰራል፡፡

ሐ) ከዚህ በፊት በሰላም እጦት ከቀየያቸው የተፈናቀሉትን ህዝቦች የመንግስት አቅም በቻለው መጠን ተመልሰው ቀየያቸው ላይ እንድኖሩ ሁኔታ ይመቻቻል፡፡

4.2. የፍትህና እርቅ ኮሚሽን

ኦብክሽመ በባላፉት ስርዓት ውስጥ ለተፋጠሩት ከባድ ወንጀሎች፣ግፍና ሰቆቃ ተጠያቂ አካላትን በመለየት ፍትህን የሚያሰፍን አጣሪ ኮሚሽን ያቁዋቁማል፡፡

4.3. የሰማዕታት ማሰታወሻ፡ ለኦሮሚያ ህዝብ ነፃነት የተሰውትን ሰማዕታትን በመላ ኦሮሚያ በማጥናት ሰማዕታቱን የሚመጥን ዝክርየሚያዘጋጅ ኮሚቴ ይቁዋቁዋማል፡፡

4.4. የህግ የበላይነትን ማረጋጋጥ፡ኦብክሽመ የህግ የበላይነት ለማረጋጋጥ ሲባል

a) የፍርድ ቤቶች ነፃነት በስራ ላይ እንድውልና እነሱ የሚሰጡት ፍርድም እንድከበር ይሰራለ፡፡

b) ማንም ሰው ያለፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዳይታሰርና መብቱም እንዳይነካ ይሰራል፡፡

c) ግለሰቦችም ሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት ለየትኛውም የህገወጥ ስራቸው በህግ እንድጠየቁ ያደረጋል፡፡

d) ቤትኛውም የስልጣን እርከን የተሾመ ባለስልጣን ለሚያጠፋው ጥፋት ይጠየቅበታል፡፡

4.5. ምርጫ ማዘጋጀት፡ኦብክሽመ ግልፅና ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲደረግሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ የህግና የስርዓት መንግስት እንዲቋቋም ያደርጋል፡፡የመንግስት ስልጣንንም ለተመረጠ ድርጅት በሰላም አሳልፎ ይሰጣል፡፡

4.6. የፖለቲካ እስረኞች፡ኦብክሽመ የኦሮሚን ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት ህገመንግስትን መሰረት በማድለግ ስልጣን ላይ በነበረው መንግስት የታሰሩትን ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች የፈታል፡፡

4.7. የኢኮኖሚ ጉዳይ፡ኦብክሽመ የሚከተሉትን ይፈፅማል

ሀ) የተፈጥሮን የኑሮ ውድነት በመለየት ህዝቡ የተሻለ ኑሮ እንድኖር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

ለ) ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ ብቻ ንብረት እንድያፈራ ይደረጋል፡፡

ሐ) እንደ እረሻ፤እንስሳት እርባታ፤ንግድና እንዱስትሪ የመሳሰሉት ሴክተሮች በሙሉ ሃይላቸው እንድያመርቱ በማድረግ ለአገር እድጋትና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል አሳተዋፅዖ እንድያደርጉ ይደረጋል፡፡

መ) የኢኮኖሚን እድገት ከሚያሳልጡ ነገሮች መካከል ትራንስፖርትና መገናነኛ ወሳኞች መሆናቸውን በመረዳት ምቹ ትራንስፖርትና መገናኛ ይዘረጋል፡፡

4.8. ማህበራዊ ጉዳች፡ኦብክሽመ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን ይሰራል

ሀ) የትምህርትና የጤና መሰረተ ልማቶች እንዲስፋፉና በቂ አገልግሎት ለህዝብ እንዲሰጡ የደረጋል፡፡

ለ) የትኛውም የማህበራዊ አደረጃጀቶች የሚጠበቅባቸውን ተሳትፎ በማድረግ ላፖለቲኮ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱና ተጠቃሚም እንድሆኑ መንግስት ሁኔታውን ምቹ ያደርጋል፡፡

ሐ) ኦብክሽመ የሴቶችና ወጣቶች በአገር ግንባታ ውስጥ የዛሬውን ሚናና የነገውን ተስፋ በሚገባ ስለሚረዳ ተሳትፎኣቸውን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል፡፡

መ) አካል ጉዳተኞች የተለየ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኙ በተለየ ትኩረት ይሰራል፡፡

እኛ የኦብክሽመ የሽግግር ጨፌ አባላት ሰኔ 30፣2021 የሽግግር መንግስቱ ምስረታ ጉባኤ አድርገን መጠነሰፊ ውይይት በማድረግ የሽግግር መንግስቱን አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቀናል፡፡

የኦብክሽመ የሽግግር ጨፌ

ሰኔ 30፣2021

ፊነፊኔ

 • የከረዩ አባ ገዳ በአሸባሪው ሸኔ ተገደሉ፤ ግድያው ከረዩ በስለፍ በመቃወሙ ነው
  በኦሮሚያ በርካታ ንጹሃንን እየገደለና እያፈናቀለ ያለው ኦነግ ሸኔ እጅግ የተከበሩና የሚወደዱ እንደሆነ የሚነገርላቸውን የከረዩ አባገዳ ከድር ሁዋስ ቦሩን መግደሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።ክልሉ ባይገልጽም በርካታ የከረዩ ሽማግሌዎች ተገድለዋል። ከአካባቢው እንደሚሰማው ከረዩዎችና አባገዳውን የሚያውቁ ኦሮሞዎች ተቆጥተዋል። “የየከረዩ ህዝብ በሸኔ ላይ ያደረገውን የተቃውሞና ለመንግስት የሰጠውን የድጋፍ ስልፍን ተከትሎ ተስፋ የቆረጠው አሸባሪው ሸኔ ህዝቡ በእኛ ላይ እንዲነሳና ሰልፉን እንዲያካሂ […]
 • Injifannoon Baahaa Fi Lixaatti Argamee Giddugala Biyyatti Akka Irra Deebi’uu Muummeen Ministiraa Abiy Ahimad Himan
   Injifannoon Baahaa fi Lixaatti argamee giddugala biyyatti akka irra deebi’uu Muummeen Ministiraa FDRI Abiy Ahimad himaniiru. Muummeen Ministiraa kana kan dubbatan adda waraanaa ijoo sadaffaatti argamuun raayyaa ittisa biyyaa waliin wayita mari’atanittidha. Oppireeshinii tibbana taasifameen dabalataan magaaloonni humna shororkeessaa ABUT qabaman bilisa akka ba’an kan ibsan yoo ta’u, gareen kun meeshaalee waraanaa kamiyyuu fudhatee akka […]
 • Preezdaant Shimallis Abdiisaan Qeerroo Fi Qarree Oromoof Waamicha Dabarsan
  Preezidaantiin Mootummaa Naannoo Oromiyaa obbo  Shimallis Abdiisaan qeerroo fi qarree Oromoof Waamicha dabarsaniiru. Ummanni Oromoo yeroo biyyi rakkoo keessa galtuu fi birmadummaan biyyaa sarbamutti dirqama gootummaa olaanaa fudhachuu fi bahachuun kan beekamu ta’uu ibsaniiru. Guutummaan Isaa Akka itti aanutti dhiyaateera:- Ummanni Oromoo saboota, sablammootaafi ummattoota Itoophiyaa biroo waliin ta’uun dhiigaafi lafeen biyya guddoo Itoophiyaa ijaare. […]
 • “ሰውየው በዶጎሎ ማማ …”
  ክፋት፣ምቀኝነትና ነቀፌታ እንዲሁም ቧልትና አሉባልታ የማይለየው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በዚህ ባህሪው የተነሳ አስሊዎች እንዳሻቸው ያላጉታል። ሃብታሙ አያሌው የሚባለው ” ተንታኝ” ኮምበልቻና ደሴ ነጻ መውጣታቸውን፣ ነጻ የወጡትም በአማራ ሃይል መሆኑን፣ ዜና ያልተነገረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀድመው መረጃ መስጠት ስላለባቸው … በሚል መቀመጫውን ለሸነቆሩለት ይሟገታል። አዋጥተው ሽንቁሩን የደፈኑለት ዜጎች ላይ መርዝ ይረጫል። ገና ብዙ ይላል … ሰውየው በዶጎሎ ማማ […]
 • መንግስት – በጦር ሜዳ የነተበውን ትህነግን በተሳሳተ መረጃ ለመደገፍ ሚዲያዎች ዘመቻ መጀመራቸውን ይፋ አደረገ
  የተለያዩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በመቀናጀት በሀሰት ዜናዎች ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ መሆኑን መንግስት ገለፀ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባሰራጨው መግለጫ መገናኛ ብዙሃኑ ከሽብር ቡድኑ ጋር በመቀናጀትና በመናበብ በማሳሳት ስራቸው ረጅም ርቀት ተጉዘዋል ነው ያለው፡፡ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በህወሓት አሸባሪ ቡድን ግጭት ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ አሸባሪ ቡድኑ ÷ መንግስት ላይ የሃሰት ውንጀላዎችን ሲያቀርብ ነበር ያለው […]

Leave a Reply

Previous post የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያልተሟላ ጥሪ አቀረበ
Next post Ethiopia to TPLF: No More Free Lunch
Close
%d bloggers like this: