የአለም ዋንጫ ቀሪ ጨዋታዎች የሚደረጉበት አዲስ ባለ 12 ካሜራ ኳስ ይፋ ሆነ

ታኅሣሥ 2/2015 (ዋልታ) በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ በአዲዳስ አማካኝነት የተሰራችዉ ‘ አል ሪሂላ’ ኳስ ከመክፈቻ እስከ ሩብ ፍፃሜ ያሉትን ጨዋታዎች አስተናግዳለች፡።

ፊፋ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መረጃ አሁን ደግሞ ‘አል ሂልም’ የተሰኘ አዲስ ኳስ ለቀጣይ ቀሪ ጨዋታዎች አዘጋጅቷል።

በአረብኛ አል ሂልም በእንግሊዘኛ ዘ ድሪም የሚል መጠሪያ ያገኘችው ይህች ኳስ እንደከዚህ ቀደሙ ኳስ በተገጠመለት ቴክኖሎጂ ትክክለኛ መረጃን ለVAR ባለሙያዎች የምታስተላልፍ ሲሆን የኦፍሳይድ (ከጨዋታ ዉጭ የሆነ ኳስ) መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ጋር በመናበብ የምትሰራ ኳስ ናት፡፡

ከጨዋታ በፊት ልክ እንደሞባይል ስልክ ቻርጅ የምትደረገዉ ይህች ኳስ 12 ካሜራዎች ከኳሷ እንቅስቃሴ ጋር በሜዳው ዙሪያ የተገጠሙ ሲሆን ከጨዋታ ውጭ የሆኑ ኳሶችን መረጃ ለዳኞች ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንዲሰጡ ይረዳቸዋል።

በሀብታሙ ገደቤ

See also  የኪሎገር የሳይበር ጥቃት ምንድነው ? እንዴትስ ይፈጸማል?

Leave a Reply