የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ኢትዮጵያውያንን በልማት ማገዝ እንሻለን፣ ያ የሚሆነው ግን የውሃ ድርሻችንን የማይነካ ከሆነ ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በሀያ ከሪማ ብሄራዊ ኮንፈረንስ ላይ ትላንት ባደረጉት ንግግር ሲሆን፣ ብሄራዊ ጥቅማችን ማስከበር የማይታለፍ ቀይ መስመር ነው ብለዋል፡፡
ግብጽ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጭ አላት ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ አማራጮቹን እንደ ሁኔታዎች አስፈላጊት መጠቀም ይገባል ሰሉ ነው የገለጹት፡፡ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸው ስጋት ተገቢ እንደሆነ የገሉት ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ፣ ስለግድቡ በዝርዝር እና በተረጋጋ መንፈስ መነጋገር ይሻል ብለዋል፡፡
“እኛ በጉዳዩ ላይ ያለንን ስጋት በምክንያት እና በተጠና እቅድ ነው የምናየው፡፡ እኛ የቅዠት ህይወት አልኖርንም፡፡ የናንተንም ስሜት ለመጠምዘዝ አንፈልግም” ሲሉ ስብሰባው ሲካፈሉ ለነበሩ ሰዎች መናገራቸውን ኢጅብት ቱደይ ዘግቧል፡፡
“ከኢትዮጵያውንና ከሱዳናውያን ጋር የዓባይ ወንዝ ለመልካም ትብብር በር እንደሚከፍት ተነጋግረናል፤ ለሁላችንም መልካም እንዲሆን እንሻለን፤ ኢትዮጵያውያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለልማታቸው እንዲያውሉት እንሻለን፤ የኢትዮጵውያንን የኑሮ ሁኔታ እንዲሁ እንዲሻሻል እሻለን፤ ግብጽ የኢትዮጵያውንና የሱዳናውያን ህይወት ብቻ ሳይሆን የመላ አፍሪካ ህይወት እንዲሻሻል ድጋፍ ማድረግ ትችላላች፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በአንድ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ያም የግብጽ የውሃ ድርሻ የማይነካ ከሆነ ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡
ጉዳዩ ቀላል ነው፤ እኛ ሙያተኛና የግብርና ምርቶችን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እንልካለን፤ እነሱ ደግሞ የውሃ ድርሻችን እንዳይነካ ያደርጋሉ ማለታቸውንም ዘገባው አስነብቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የወሰዱት በጉዳዩ ዙሪያ የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለማግኘት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በዓለም ዓቀፍ ህግ አግባብ ተስማምተን በሰላም እና ብልፅግና እንኑር ሲሉ ለኢትዮጵያና ለሱዳን ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አሳሪ ህግ መፈረም የመጪውን ትውልድ የመበልጸግ እጣ ፋንታ ስለሚገድብ እንዲህ አይነት ግደታ ውስጥ አልገባም ማለቷ ይታወቃል፡፡
የግብጹ ሀያ ከሪማ የሚባለው ብሄራዊ ፕሮጀክት የ50 ሚሊየን ዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል የተወጠነ ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ 700 ቢሊየን የግብጽ ፓውንድ ወጪ እንደሚደረግበትና በሶስት አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል።
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ