ለ”እጅ እንስጥ” የስልክ ጥያቄ መከላከያ ” ምርጫው የእናንተ ነው” አለ፤ ሽሬ ነዋሪዎችና መከላከያ እየተነታረኩ ነው

በትግራይ የ” ህግ ማስከበር” ዘመቻው እየተገባደደ መሄዱን ተከትሎ እጃቸውን ለመስጠት በግል ድርድር የፈለጉ አንድንድ የትህነግ ካድሬዎችና አክቲቪስቶች በመከላከያ ሃላፊዎች ምላሽ መገረማቸው ተሰማ። በሽሬ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ነዋሪዎች ንትርክ ውስጥ እንደሚገቡ ተገለጸ።

የኢትዮ 12 መረጃ አቀባይ እንዳለው በውል ከማይታወቅ የትግራይ ክልል እጅ ለመስጠት ስልክ የሚደውሉ አሉ። በትግራይ ላለው የአገር መከላከያ ፖስት ኮማንድ የስልክ ጥያቄ የሚያቀርቡት የትህነግ ካድሬዎች፣ እንዲሁም ራሳቸውን አክቲቪስት ብለው የመደቡ፣ አንዳንድ የባይቶናና ሳልሳይ ወያኔ አመራሮች ናቸው።

የመረጃ ምንጮቹ ለጊዜው ስም መጥቀስ አስፈላጊ እንዳልሆነ ጠቁመው እንዳስረዱት ደዋዮቹ የሚያቀርቡት ጥያቄ ራሳቸውን በመግለጽና አንዳንዴም ማንነታቸውን ለጊዜው በመሸሸግ ነው።

” በተደጋጋሚ ስልክ ይደወላል። ስልኩ የጥቆማ መልዕክትም ስለሚስተናገድበት ሁሌም ዝግጁ ነው” በማለት መረጃውን ያቀበለን እንዳለው ስልክ ከደወሉ በሁውላ የሚያቀርቡት ጥያቄ ” አሁን እጅ ብንሰጥ ታስሩናላችሁ ወይ?” የሚል ነው።

ለዚህ ስራ የተመደቡ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት ” ስማችሁ በይፈለጋል መዘገብ ተጽፎ መጥሪያ የወጣባችሁ መከላከያ ሳይሆን የሚፈልጋችሁ ህግ ነው። ከዚያ ውጭ ከሆናችሁ ምርጫው የናንተ ነው” የሚል መልስ እንደሚሰጡዋቸው ታውቋል።

” ዋሻ ውስጥ መኖርና ከዋሻ ወጥቶ በሰላም መኖር ልዩነቱን ስለምታውቁት መብታችሁ ነው ” የሚል አስደማሚ መልስ እንደተሰጣቸው ከገለጹት መካከል አንዱ በድብቅ ለሚገናኛቸው ሲናገር በተሰጣቸው መልስ ተገርሟል።

ይህ አክቲቪስት ሆኖ ሚዲያ ላይ ዘማቻ ሲያፋፍም ከነበሩት አንዱ የሆነው ደዋይ ” እንዳሻችሁ፣ ውሳኔው የናንተ ነው” የሚል መልስ ሲሰጣቸው ባሉበት ሆነው ሳያቋርጡ እንደሳቁ ተናግሯል። እጃቸውን ለመስጠት ወስነው ይግቡ አይግቡ የመረጃው ባለቤት አስካሁን አላረጋገጠም።

በተመሳሳይ የትግራይ የጥቆማ ዜና በሽሬ በመከላከያ ሰራዊት አባላትና ባጃጅ በሚያሽከረክሩ ሾፌሮች መካከል ንትርክ እንደሚሰማ ተጠቁሟል። እንደ ጥቆማው ከሆነ ንትርኩ የመከላከያ ሰአሪት አባላት ባጃጅ ላይ ሲሳፈሩ የሚፈጠር ነው። ባጃጅ ከያዙ በሁዋላ ሂሳብ ሊከፍሉ ሲሉ አሽከረካሪዎቹ ” አንቀበልም፣ አትከፍሉም” ማለታቸው ነው ንትርክ ያስነሳው። የመካላከያ ሰራዊትና የባጃጅ አሽከርካሪዎች በዚህ መልኩ ሲከራከሩ መመልከት እጅግ ስሜት እንደሚሰጥ ነው ምስክሩ የነገሩን።

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply