ኢሳያስ የትህነግ ወደ ሸዋ ማቅናት ከውትድርና አንጻር እብደት መሆኑን፣ ውሳኔው የአለቆች አምልኮ ውጤት መሆኑንን አስታወቁ

ትህነግ ወደ ሸዋ ለመግባት ያደረገው ሙከራና ጭንቀት የወለደው፣ ሰለውትድራና መጠነኛ እውቀት አለኝ ከሚል ሃይል የማይጠበቅ ድንቁርና የተሞላው፣ አለቆቻቸውን ለማስደሰት የተደረገ የብደት ውሳኔ መሆኑንን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቅ አስታወቁ። የኢዮጵጵያ የብሄር ፌደራሊዝም የውጭ ሃይሎች እጅ እንዳለበት አመለከቱ ። ጥቅምት 24 የትግራይ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ አምስትና ስድስት ሺህ የሚሆኑት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ኤርትራ ሸሽተው እንደነበር አመለከቱ። ሱዳንን አንድ አምራች ሃያ ደላላ በሚል ምሳሌ ገልጸዋል።

በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚነቅፉት ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ሀገር ከመገንባት ይልቅ የብሔረሰቦች አገራትንና ተቋማትን መፍጠር የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች እጅ አለበት አመልክተዋል።

“በኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት ሳይመጣና ለዚህ የሚያበቃ ሥርዓተ መንግሥት ሳይዘረጋ ከመጣው ሥርዓት ሁሉ እየተፋተግን መቀጠል አንችልም። ለዚህም የራሳችንን አስተዋፅኦ ማበርከት ስላለብን እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከተው አይሆንም” ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መምጣት ጋር ተያይዞ በሁለቱ አገራት መካከል የነበረው ውጥረት ይፈታል የሚል እምነት ቢኖራቸውም ህወሓትና በስም ያልጠቀሷቸው አጋሮቹ ብለው የጠራቸው አካላት ለውጡን ባለመቀበላቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የሰላሙ ሁኔታ ያሳስባቸው እንደነበር ተናግረዋል።

“አንዳንዱ ሰው ተስፈኛ ስለሆነ ሰላም፣ ሰላም ሲባል ሁኔታዎችን በጥልቀት ሳይገመግም በአዎንታዊ መልኩ አይቶታል” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በርካታ የኢትዮጵያ ታጣቂ ኃይሎች በኤርትራ መቀመጫቸውን አድርገው መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ስላለው የኢትዮጵያ ሁኔታ የገመገሙ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው መቃቃር መቼ እልባት እንደሚያገኝ ማን እንደሚፈታው ትልቅ ጥያቄ ነው ብለዋል።

“ሆኖም የራሳቸው ጉዳይ ነው ብለን ዝም አንልም። ሆኖም [የእኛ ተሳትፎ ] በዘፈቀደ ሳይሆን በእውቀትና በእቅድና በዲዛይን የሚደረግ ይሆናል” በማለት አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም በተደጋጋሚ ሲነቅፉ የሚሰሙት ፕሬዚዳንቱ በትናንትናውም ቃለ መጠይቅ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ሀገር ከመገንባት ይልቅ የብሔረሰቦች አገራትንና ተቋማትን መፍጠር የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች እጅ አለበት ብለዋል።

See also  በሕገወጥ የመሬት ወረራ በተሳተፉ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች አካላት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው

ቀጣናውንም አስመልክቶ ያነሱ ሲሆን ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በሶማሊያ ላይ የታየው መከፋፈልና በቅርብ ጊዜም በሱዳን ላይ እየታየ ያለው ቀውስ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በተመለከተ

በትናንትናው ቃለ መጠይቅ በያንዳንዱ የዓለም አካባቢ የሚፈጠር ቀውስ በራሳቸው መንገድ ለመፍታት በበላይነትና በብቸኝነት ለመፍታት ጥረት የሚያደርጉና የተለየ ጥቅም ጠባቂዎች ሲሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ከሰዋል።

“ኤርትራ የኛን ጥቅም የምታገለግል አይደለችም” በማለት በተከተሉት ፖሊሲ ምክንያት የኤርትራ ሁለት ትውልዶችን መስዋዕትነት አስከፍለዋል ሲሉም ወንጅለዋል።

እነዚህ የተለየ ጥቅም ጠባቂ ያሏቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከተለያዩ የጎረቤት አገሮች ጋር ግጭት በመቀስቀስ ኤርትራ ወደፊት እንዳትራመድ በክስና በስም ማጥፋት ለዘጠኝ ዓመታት ያህል በማዕቀብ መቅጣታቸውን አስታውሰው፣ አሁንም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ፍትሃዊ ያልሆነ ማዕቀብ ተጥሎብናል በማለት ወቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በአራት የኤርትራ ተቋማትና በሁለት ኤርትራውያን ላይ በያዝነው ዓመት ማዕቀብ ጥሏል።

ማዕቀቡ የኢትዮጵያን መረጋጋትና አንድነት እያናጋ ነው ባለው ቀውስና ግጭት ውስጥ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን የኤርትራ ተቋማትና ዜጎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን የአሜሪካ የፌደራል ግምጃ ቤት በወቅቱ አመልክቷል።

በዚህም መሠረት ዕቀባው የተጣለባቸው ተቋማት የኤርትራ መከላከያ ኃይል፣ የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ ህድሪ ትረስ እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ግለሰቦቹ ደግሞ አብረሃ ካሳ ነማሪያም እና ሐጎስ ገብረሕይወት ወልደኪዳን የተባሉት ናቸው።

በኤርትራ የሁለት ቀናት ጉብኝት ከሰሞኑ ያደረጉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አውግዘዋል።

ፕሬዚዳንቱም የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጉብኝት በማንሳት ከአገሪቱ ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ትግበራ የሚገባበት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የዛሬው የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ቃለ መጠይቅ!
(ጓል ፈዳይን ሻዕቢያ ቫይናክ)

ዛሬ ማምሻውን ፕረዚዳንት ኢሳይያስ ኣፍወርቂ፣ በቴሌቭዥን በቀጥታ የተላለፈ ሰፊ ቃለ-መጠይቅ ኣካሂደዋል።

በዚህ 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ በፈጀው ቃለ መጠይቃቸው ዓለም አቀፋዊ፣ ከባቢያዊና ሃገራዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊና የጸጥታ ጉዳዮችን በጥልቀት ዳስሰዋል።

See also  ስብሐት ነጋ የፌደራል ፖሊስን ከሰሱ፤ "ለስብሃትም የምትሆን ኢትዮጵያ እየተሰራች ነው"

የኢትዮጵያን ገዳይ በተመለከተ ከተናገሩት አንኳር ጉዳዮች መካከል:-

  • የኢትዮጵያ የፌዴራል ሰራዊት በሰኔ ወር ላይ ትግራይን ለቆ ለመውጣት ሲወስን ያልተጠበቀ ውሳኔ እንደነበር፣
  • የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ከፍተኛ የምዕራባዊያን መንግስታትን ጫና እንዳስተናገዱ፣
  • ወያኔ ገና ሲመሰረት ጀምሮ አንድን ህዝብ በጅምላ በጠላትነት ፈርጆ በማኒፌስቶ ፕሮግራም ቀርጾ ለ 50 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የነበረ ጠባብ ድርጅት መሆኑ፣
  • ወያኔ የአማራ ሾቪኒዝምን እታገላለሁ፣ የአማራ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይንቃል በሚል፣ የትግራይን ህዝብ ለእኩይ ኣላማው ያነሳሳ እንደነበር፣ ነገር ግን በጊዜ ሂደት በትረ መንግስቱን ከጨበጠ በኋላ የራሱን አናሳ የዘራፊዎች ቡድን በኢትዮጵያ ላይ ማንገሱ፣
  • አናሳው የወያኔ ቡድን ኢትዮጵያዊያንን በዘር ኣቧድኖ ለመግዛት ይሄንን መርዛም ዘረኛ ፕሮግራሙን ህገ-መንግስታዊ ሽፋን ሰጥቶ ኢትዮጵያን ለ 27 ዓመታት ሲገዛ እንደነበር፣
  • ወያኔ፣ ኢትዮጵያን በመንታ ልቡ ሲገዛት እንደነበር፣ ይህም ማለት፣ እስከተመቸው ድረስ ኢትዮጵያዊ መስሎ መግዛት፣ ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከሆኑበት ደግሞ የትግራይ ሪፐብሊክ የሚል ከኢትዮጵያዊያን የተሰወረ ድብቅ ፕላን ቢ እንደነበረው፣
  • ወያኔ የቀረጸው ህገ-መንግስት ተብዬውን ረቂቅ ሰነድ ለመጀመርያ ጊዜ ካዩት ሰዎች አንዱ እንደነበሩ፣ በህገ-መንግስቱ ሰነድ ላይ የተቀበሩት ጊዜ ጠብቀው የሚፈነዱ ፈንጂዎችና የመጪውን ጊዜ አደጋ በወቅቱ እንደታያቸውና ይሄንንም ለመለስ ዜናዊ እንደገለጹለት፣ ነገር ግን በመለስ ዜናዊ በኩል ኢትዮጵያን ለመግዛት የምንችለው በዚሁ ሰነድ ብቻ ነው ተብሎ እንደተገለጸላቸው፣
  • ወያኔ የምዕራባዊያንን ኣጀንዳ በኣፍሪካ ቀንድ ላይ እንዲያስፈጽም የተመረጠ ኣናሳ ተላላኪ ቡድን እንደነበር፣ ምንም ዓይነት ሃገራዊ ራእይና አጀንዳ እንዳልነበረው፣
  • ወያኔ ሁለት ጊዜ ትልልቅ በሚባሉ የእብደት ኩነተ- ኣእምሮ ውስጥ እንደገባ:- አንደኛው ሰሜን እዝን ማጥቃቱ ሁለተኛው ደግሞ የፌዴራል ሰራዊት መቀሌን ትቶ ከወጣ በኋላ ኣዲስ ኣበባ እገባለሁ ብሎ፣ በኣማራና ኣፋር ክልሎች ላይ የፈጸመው መጠነ ሰፊ የጥፋት ወረራ፣ ይሄንን እኩይ አላማውን ለማስፈጸም ህልቆ መሳፍርት የሌለው የትግራይ ወጣት እንዳስጨረሰ
  • ወያኔ አዲስ ኣበባ እንዲገባ፣ ምዕራባዊያን መንግስታት፣ በሚድያዎቻቸው በኩል የፕሮፓጋንዳ ጥሩንባ እንደነፉለት፣ ባንድ በኩል ገለልተኛ ኣደራዳሪ መስለው ይቀርቡ እንደነበር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለወያኔ ግልፅ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን ይሰጡ እንደነበር፣
  • የወያኔ መሪዎች እስከ ሰሜን ሽዋ የሄዱበት ርቀት ማንም መሰረታዊ እውቀት አለኝ፣ የወትድርናን መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ኣውቃለሁ ከሚል የሚጠበቅ እንዳልነበር፣ ይልቁንም በኣዕምሮ ጭንቀት ሳያሰላስሉ የገቡበት የእብደት ውሳኔ እንደነበር፣ በሳቢያውም የትግራይ ህዝብ ትልቅ ችግር ውስጥ እንደገባ፣
  • የትግራይ ህዝብ እራሱን ከሚጎዳው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አርቆ በዘሌቄታው የሚያዋጣውን ምርጫ መውሰድ እንዳለበት፣ የትግራይ ህዝብ፣ ዙርያውን ጠላት ከሚገዛለት ወያኔ ውጪ ጠላት እንደሌለው መገንዘብ እንዳለበት፣
  • ወያኔ እራሱ ለፕሮፓጋንዳ እንደሚለው ለሰላም ዕድል ለመስጠት ብሎ ሳይሆን በወታደራዊ መልሶ ማጥቃት ወደ ትግራይ እንዲያፈገፍግ መገደዱ፣
  • ምእራባዊያን መንግስታት፣ ወያኔ ኣዲስ ኣበባ ባለመግባቱና የለውጥ መንግስቱን ባለማፍረሱ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ እንደገቡ፣
  • የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታን ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት በተለየ መልኩ በትኩረት እንደሚከታተለውና ገንቢ የሚለውን ኣስተዋጽኦ ከማድረግ እንደማይቆጠብ፣
  • ኢትዮጵያ ወያኔ ካወረሳት ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮቿ እንድትፈወስ ከተፈለገ ለጊዜው የሚያሻግሩ የመፍትሄ ሃሳቦች ሳይሆን የሚያስፈልጓት ዘለቄታዊ መፍትሄዎችን የሚያመጡላትን የመፍትሄ ሃሳቦችን ነው መጠቀም ያለባት፣
  • በኤርትራ፣ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል፣ በራስ ተነሳሽነት የተፈጠረው ምእራባዊያን መንግስታት ያልባረኩት መቀራረብ፣ የአሜሪካንን መንግስት ስልጣን በተቆጣጠሩ ጥቂት የ special interest group ባለስልጣናት ዘንድ እንዳልተወደደ፣
  • የኤርትራ መንግስት የኤርትራን የብሄራዊ የደህንነት ጥቅሞችን ለማስከበር ምንም የኣቅም ዉስንነት እንደሌለው፣ የብሄራዉ የደህንነት ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ፣
  • የኤርትራ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር ያለው ግኑኝነት አንዳንዶች እንደሚሉት ከ1993 በኋላ የጀመረ ሳይሆን በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ከ 50 ዓመት በፊት የጀመረ እንደነበር፣ ቻይና ለኤርትራ የነጻነት ታጋዮች ዉሱን የጦር የመሳርያ እርዳታ ታደርግ እንደነበር፣
  • የሰሞኑን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኤርትራ ጉብኝት ተከትሎ በኤርትራና ቻይና መንግስታት መካከል ዘርፈ ብዙ የትብብር ስምምነቶች መደረጋቸውን፣
See also  ለንጮ ባቲ - አሜሪካ ቢሾፍቱ የተከሰከሰው ቦይንግ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ላኩ ስትል አብይ አሕመድ ከልክለዋል

Translated by our Paulos , by Eritrean press

Leave a Reply