የራይድ አሽከርካሪውን የገሉ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

የራይድ አሽከርካሪውን ገድለው መኪናውን እና ሌሎች ንብረቶችን የሰረቁ ወንጀል ፈፃሚዎች የእድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡


በላይነህ ንጉስ እና የአብስራ ሰለሞን ከአንድ ካልተያዘው ግብረአበራቸው ጋር በመሆን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚፈልጉ በማስመሰል ጥሪ ያደርጋሉ፡፡ ጥሪው የደረሰው ሟች ንጉሴ ከፍያለው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ A-88855 ቪትዝ መኪናውን ይዞ ከስፍራው ይደርስና ሦስቱን ግለሰቦች ይዞ መጓዝ ይጀምራል ፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅድው ጥሪውን ያደረጉት ነሃሴ 6 ቀን 2012 ዓ/ም በምሽት ክፍለ ጊዜ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ሆራ ትሬዲንግ አካባቢ ሲደርሱ አሽከርካሪውን በማነቅ እና በጩቤ በመውጋት ተሽከርካሪውን እና ሞባይል ስልኩን ይዘው ይሰወራሉ፡፡
የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ ወንጀሉን ከፈፀሙት ሦስት ግለሰቦች መካከል ሁለቱን በቁጥጥ ስር በማዋል ምርመራውን አጣርቶ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡
ያልተያዘውን ተጠርጣሪ ከተሰወረበት አድኖ ለመያዝ ክትትሉን አለማቋረጡን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተከሳሾች ለፍርድ ቤት ወንጀሉን አልፈፀምንም በማለት ክደው ቢከራከሩም ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰቡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ መሆናቸውን በማረጋገጡ እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡ ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደሌለ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ህብረተሰቡ የሚሰጠው መረጃ በህግ የበላይነት መከበር ለሚገኘው ውጤት መሠረት መሆኑን በመገንዘብ ቀና ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል ።

Source Addis Ababa police

See also  150 ሺህ የቀበሌ ቤቶችን ኦዲት ሊደረጉ ነው

Leave a Reply