ሚድሮክ ከመንግስት ሚዲያዎች ጋር የሚፈጽመው የ”አብረን አንስራ” ውል አነጋጋሪ ሆኗል

“ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡” የሚለው ዜና መሰማቱን ተከትሎ ( ቀደም ብሎ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ አሁን ደግሞ ከፋና )ሲሉ ውሉ ያስገረማቸው አስተያየት አየሰጡ ነው፤ ሚድሮክ የመንግስት ሚዲያዎችን በኮንትራት መጣባት የፈለገበት ምክንያት ግልጽ አንዳልሆነላቸው የሚናገሩ አንዳሉት ድርጅቱ ከመንግስት ሚዲያዎች ጋር ውል ገብቶ ከፍተኛ ብር ሲከፍል በሌላ መልኩ ሚዲያዎቹን አፍ ያዘጋል፤
ሚድሮክ በተከታታይ የሚያሰራጨው ከማስታወቂያ ያለፈ አቅድ ካለው የአር ሰአት ገዝቶ ሊሰራ አንደሚገባው ያመለከቱ ( አንዲህ ያለው መታከክ አድሮ ችግር መፍጠሩ ኣይቀርምÆ ብለዋል፤ አያይዘውም አጀንዳውን በፓርቲ ደረጃ አየተወያዩበት አንደሆነ ኣመልክተዋል፤ የፓርቲያቸውን ስም ግን ለጊዜው አልገለጹም፤ አክለው ግን ሚድሮክ ወርቅ በድጋሚ ማምረት ሲጀመር አነዚህ የመንግስት ሚዲያዎች የቀድሞው ችግር የተፈታበትን አግባብ ያድበሰበሱትም ከዚሁ አንጻር ሊሆን አንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፤ ይህን ሲሉ ፓርቲያቸው ድርጅቱ ወርቅ ማምረቱን ይቃወማል ለማለት ሳይሆን በዚህ ዙሪያ አየሰሩ ያሉት ስራ መኖሩን ለመዕተቆም ነው፤ የፋና ዘገባ ከስር ያለው ነው

የፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ

የፊርማ ስነ ስርዓቱን የፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ተፈራርመዋል፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ፋና የህዝብ ሚዲያ እንደመሆኑ እለታዊ እቅስቃሴዎችን ከመዘገብ ባለፈ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ ስራዎችን የሚሰሩ ተቋማትን ከህዝብ ጋር የማስተሳሰር ስራዎች እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ፋና ሰፊ የማህበረሰብ መሰረት ካላቸው ተቋማት ጋር ለመስራት ምርጫው ሲያደርግ ህብረተሰቡን በቀላሉ ለማገልገል ያለውን ፍላጎቱን ባለሃብቱንና ህብረተሰቡን እንዲሁም አገልግሎቱንና አገልግሎት ፈላጊውን ለማገናኘት ብሎም በውጤቱ የማቀራርብ የማደግ እንዲሁም የሃገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን የማሳደግ አላማን ይዞ ነው፡፡

በዚህም እንደ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያሉ ለህብረተሰቡ ለውጥና ለሃገር እድገት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን የሚሰሩ በመሆናቸው በጋራ ለመስራት መስማማታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት በሬዲዮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች በ11 ኤፍ ኤም ጣቢያዎች ፣ በ7 የሃገር ውስጥ እና በአንድ የውጭ ቋንቋ በመድረስ ብሎም የተወደዱ የዜና ትምህርታዊና መዝናኛ ፕሮግራሞቹን በተሻለ ጥራት በቴሌቪዝን አማራጭ ይዞ በመምጣቱ በህዝብ ዘንድ ተመራጭ አድርጎታል ብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በአቀራረቡ የተለየ በመሆኑ፣ የሃገርን ልማት ለማፋጠን እንዲሁም የህዝብ የሆኑ ስራዎችን በመስራት ተወዳጅ ጣቢያ በመሆኑ፤ ከሚድሮክ ጋር አብሮ መስራቱ  የሃገርን እድገት በማሳለጥ በኩል ብሎም ለተቋማቱ አስተዋጽዖ የጎላ መሆኑ ተነስቷል፡፡

በግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በንግድና ቢዝነስ እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፎች 35 ኩባንያዎችን የሚያንቀሳቅሰው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፤ ባሳለፍነው ዓመት መጨረሻ ባካሄደው የተቋም የለውጥ ስራዎች ውስጥ የሚዲያ አጠቃቀሙ አነስተኛ መሆኑን በመገምገም ከሁለት ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት መወሰኑን የኢንቨስትመንት ግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሃገርን ልማት ለማፋጠንና የሃሪቱን እድገትን ለማሳደግ እየሰራ ያለ ተቋም እንደመሆኑ የድርጅቱን አላማ የሚጋሩ አካላትን ተመራጭ በማድረግ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን መምረጡን ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሃገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች፣ በተለያዩ አማራጮች እንዲሁም በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ በመሆኑ ሌላው ተመራጭ የሆነበት ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ፋና የሚሰራቸው ዘገባዎች፣ ዜናዎችና ፕሮግራሞች የህዝብ የሆኑ እንዲሁም በስራዎቹም ሃላፊነት የሚሰማው ተቋም  በመሆኑ ተቋሙን ተመራጭ እንዳደረገው አቶ ጀማል አህመድ ጠቁሟል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply