በቀጣይ አምስት ዓመታት 500 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት አቅዶ እየሰራ ያለው የአዲስ አበባ አስተዳደር የአንድ መቶ ሺህ ቤቶች ግንባታ ለማከናወን ከስምምነት የደረሰ መሆኑንን ይፋ አደረግ።
በዚሁ መረሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ አመት ውስጥ 100 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ስምምነቱን የፈረሙት በየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ናቸው።
ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ ሙሉ ወጪው በኩባንያው እንደሚሸፈን ተመልክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ያቀርባል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ30 አመታት ክፍያ ለተጠቃሚዎች የሚተለለፉ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የተቀናጀ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ በመቶ አነስተኛ ወለድ ለህብረተሰቡ የሚተላለፉ ሲሆን፥ በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥም 500 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡም አስተዳደሩ እግረመነገዱን አስታውቋል።
ለመኖሪያ ቤቶቹ በመሃል ከተማ የመልሶ ማልማት በሚከናወንባቸው እና በአይሲቲ ፓርክ አካባቢ ቦታ መለየቱም በስምምነቱ ወቅት ተነስቷል፡፡
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?