ከነሐስ ቀልጦ የተሰራው ህፃን

Ethiopia | የኪነ ሀውልት ስራው ሠዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን ነው::

ከኪነህንፃው እስከ ኪነ ሐውልቱ ድረስ የከያኒያን የእውቀትና የጥበብ አሻራ ያረፈበት ቤተመጽሐፍት

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ትላንት የተመረቀው ቤተ መጻሕፍት ‹አብርሆት Enlightenment› ይሰኛል። ቤተመፅሐፍቱ ከውጭ ጀምሮ ከኪነህንፃው እስከ ኪነ ሐውልቱ ድረስ የከያኒያን የእውቀትና የጥበብ አሻራ ያረፈበት ቤተመፅሐፍት ነው:: በተለይ በአውሮፓ አገሮች ውስጥ የሚገነቡ ህንፃዎችና ሁል ጊዜ እንደቀናሁ ነበር የኖርኩት:: አብርሆት ቤተመፅሐፍ ህንፃው ከውጫዊ ገፅታው ጨምሮ የቤተመፅሐፋን ሃሳብና ርዕይ መሰረት አድርጎ እንደተሰራ ያመለክታል:: በሌላው ሐገር የምንቀናው የሐገርን ቁሳዊና መንፈሳዊ እሴትን የያዘ የህንፃ ግንባታን በአብርሆት ቤተመፅሐፍ ላይ መመልከታችን ነገ ለኪነ ህንፃ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን በመንግስትም ሆነ በግል ለሚሰሩ የህንፃ ግንባታዎች እንደ ማዕዘን ድንጋይ እንዲቆጠር ያደርገዋል ::

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ትላንት በምርቃቱ ላይ ስለ ቤተመፅሐፍቱ ዓላማና ኪነህንፃውን አስመልክተው ሲናገሩ “ከሥነ ሕንጻው ጀምሮ ዕውቀትንና ታሪክን እንዲያንጸባርቅ ተደርጎ የተገነባ ነው። ‹አብርሆት ቤተመፅሐፍ ዋና ዓላማውም እውነትና ዕውቀት ነጻ የሚያወጣውን ማኅበረሰብ ለመመሥረት ስለሆነ ነው።

ኢትዮጵያ ለልጆቿ የሥልጣኔን መንገድ መርጣለች። ለጠላቶቿ ደግሞ ክንደ ብርቱ ሆና ትጠብቃቸዋለች። የሥልጣኔው መንገድ ደግሞ መማር፣ መመራመር፣ መወያየት፣ መከራከር፣ በሐሳብ መሸናነፍ፣ ዕውቀትን ማነፍነፍ፣ በአመክንዮ፣ በማስረጃና በመረጃ ላይ መመሥረት ናቸው። ” ነበር ያሉት ::

ሌለው አብርሆት ቤተመፅሐፍ ደጅ ላይ የቆመውን ኪነ ሐውልት ሰራው ነው:: ይህ የኪነ ሐውልት ስራ ለህንፃውና ለቤተመፅሐፍቱ ግዙፍ ጌጥና ውበት እንዲላበስ አድርጎታል:: ይህንየኪነ ሐውልት ስራ የሰራው ሰዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን ነው:: በቀለ መኮንን ሐገራችን ካሏት የኪነሐውልት ስራ በለሙያዎች መካከል አንዱ ነው::

ስለዚህ የኪነ ሃውልት ትርጏሜና አጠቃላይ ስራውን በተመለከተ እንዲነግረኝ በስልክ ጠይቄው ነበር:: በቀለ መኮንንም አጠቃላይ ስለኪነ ሀውልቱ ያዘጋጀሁት ፁሑፍ ስላለ ለምን አልክልህም አልኝ :: እኔም የላከልኝ ፁሑፍ ይሄው ለእናንተ አድርሻለሁ::

“በአዲሱ የአብርሆት የህዝብ ቤተመፃሕፍት ደጃፍ የቆመው ኪነ ሀውልት በቅርፁ ፣ የስነውበትን ደስታ በሚፈጥር ቀረፃና የልጅነትን ደፋር ነፃነት ባጣመረ መልክ የተዋቀረ ነው። ከቅርብም ከሩቅም በሰዎች መተላለፊያ መንገድ ዳር በመሆኑ ለሁሉም አይኖች የተጋለጠ ነው።

See also  በወሎ ግንባር የትህነግ አዋጊ ጀነራል መገደላቸው ተሰማ ፣ 358 የአሸባሪው ታጣቂዎች ተያዙ

ወደ መፃሕፍት ቤቱ ዘልቀው ኮስታራ ንባብ ከመጀመራቸው በፊት ሁሉም ተመልካቾች ባለፉበት የልጅነት ወራት ተናፋቂና አስገራሚ ድርጊት ዘና የሚሉበትን ዕድል እንዲፈጥር ሆን ተብሎ የተመረጠ ነው ይዘቱ ።

ከነሀስ ቀልጦ የተሰራው ህፃን በልጅነት ነፃነቱ ከዚህ ዓለም ማናቸውም ተፅዕኖ ነፃ ስለሆነ ነባር የዕውቀትና የመረጃ ክምር ላይ ተኝቶ ባደግንባቸው ፊደልና ቁጥር የተሰራ ሉል/ ዓለም ጋር ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዟል። ይጠይቃል ይገረማል ይፈልጋል።እያደር ሲጎለምስ የሚፈራውን ገለባብጦና ተገለባብጦ ራሱንና አካባቢውን የማየት ድፍረት በዚች ዕድሜ ላይ ጀምራ እዛው ላይ የምታበቃ ድንቅ የቅፅበት ዘመን ናት።

ሁሉም ሰው ኋላ ተመሳሳይ ሰልፍ ውስጥ መግባቱ ባይቀርም ከርሞ በሚያጣው በነፃነቱ ዘመን የታደለውን ተሰጥዖ በዚህ ቅርፅ ውስጥ ማስቀረት ዋናው የዚህ ቅርፅ ዒላማ ነው ። የቅርፁ ትልቅ ተሸካሚ መሠረት ደግሞ እንደተፈጠረ የተተወ ትልቅ አለት ሲሆን ( subliminal )ውበትን ከሌላው የኤስቴቲክ ቀመር ጋር እንዲያዋህድና ግርምታን እንዲጨምር የተመረጠ ነው ።

ህፃኑና የፊደል ሉል ደግሞ በቀለም ፣በመጠን በቴክስቸር፣ በእይታ ክብደትና ቅለት ተናበው የተቀናበሩ የቅርፁ ይዘትና ቅርፅ ተጫዋችና አጫዋች ኤለመንቶች ናቸው።

በቀለ መኮንን 2021
በቄ እንኳን ደስ ያለህ!!

Leave a Reply