“እውነት ገሃድ ሲወጣ የተሃድሶ ትረካ ሕንፃዎች ሙሉ በሙሉ ይፈርሳሉ” የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው እንዳስታወቁት፣ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በቁጥር ያልገለጿቸውን ኤርትራዊያን በስደት ካምፕ ያሉትን ጨምሮ እየጨፈጨፈ መሆኑንን ዓለም እንዲሰማ ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው።
“በብዙ መንገዶች የትህነግ አስከፊ ተግባሩ አያስገርምም” ያሉት ሚኒስትሩ ፣ የጠፋውን ትህነግ መልሶ እንዲያንሰራራ የተሞከረው እጅግ ስፍ ወነጀሎቹን በመደበቅ እንደነበር አስታውሰዋል። እንዲህ ያለውን ድርጅት ተጎጂ አድርጎ በመሳል ሲሰራጭ የነበረው ትርክት ዛሬ ላይ መልኩ እንደቀየረና ትህነግ በትክክለኛ ማንነቱ የሚትይበት ወቅት መሆኑንን አመልክተዋል። ይህን ሲያጸኑ ” እወነቱ ገሃድ ሲወጣ የተሃድሶ ትረካ ህንጻዎች ሙሉ በሙሉ ይፈርሳሉ” ብለዋል። ይህንንም ያሉት ዛሬ እልቂቱን እየሰሙ፣ እዛው ሆነው እያዩ ዝምታ ለመረጡት ሚዲያዎችና መንግስታት ይመስላል።
ትህነግ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ ጨምሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የበቀል ጭፍጨፋ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ፤ ሆኖም እንዲህ ያሉትን አረመኔያዊ ድርጊቶችና ሁሉንም የሕወሃት ሕገ-ወጥ ተግባራት በማጋለጡ በኩል ኦቻ፣ የተመድ፣ የዓለም የስደተኞች ድርጅትና ተያያዥነት ያላቸው ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ የመብት ተከራካሪዎች ዝም ማለታቸው እጅግ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ቢቢሲ አፍሪካ “የማስጠንቀቂያ ዜና” ሲል ትናንት እንደዘገበው በሺሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ዜጎች በትህነግ መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ድርጅትን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደዘገባው Rights activists say they have received reports that many refugees were brutally killed by local militias. እየደረሰ ያለው መረጃ እጅግ አሰቃቂ ግድያ እንደሚፈጸም አመላክች ነው።
ከተለያዩ አቅጣጫዎች ” መንግስትን ደግፋችኋል” በሚል በርካታ እንደርታና የሌሎች ከተማ ነዋሪዎች መቀለን ጨምሮ ቢገደሉም በስፍራው ዘጋቢ ያላቸው ቪኦኤና የጀርመን ድምጽ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ሌሎችም ትግራይ ሆነው የሚዘግቡ ሚዲያዎች ድምጻቸው አልተሰማም። የኮረም ነዋሪዎች እየተጨፈጨፉና 30 ሺህ የሚሆኑት ሸሽተው ወደ መጠለያ መግባታቸውን በይፋ የህዝቡ ተወካይ ፓርቲ ቢያመለክተም ዓለም ምላሽ አልሰጠም።
የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግስታት ህዝባቸውን መታደግ ቢኖርባቸውም ጉዳዩን አስመልክቶ ሊወስዱ ስለሚችሉት እርምጃ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ይህ በንዲህ እንዳለ ትህነግ ለቀጣይ ጦርነት ዝግጅት ላይ መሆኑንን የውጭ ሚዲያዎች ትኩተር ሰጥተው እየሰሩ ነው።