ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ 30 የዓለም ሀገራት በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደረገውን የአንድ ወገን ማዕቀብ ተቃወሙ

የአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃዎችን (unilateral sanctions) መጠቀም ከተባበሩት መንግስታት ቻርተር እና ዓለም አቀፍ ሕግ ፣ ከብዙ ወገንተኝነት እና ከዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መሰረታዊ መርሆዎች ጋር ይቃረናልብለዋል

ቻይና እና ሩሲያን ጨምሮ 30 የዓለም ሀገራት በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደረገውን የአንድ ወገን ማዕቀብን በመቃወም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደብዳቤ ጽፈዋል።

ሀገራቱን በመወከል ደብዳቤውን ለተመድ ያስገቡት በተመድ የቻይና ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ዣን ጁን ናቸው። የኮቪድ-19 በዓለም ሀገራት፣ በተለይ ደግሞ በታዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑ በደብዳቤው የተገለጸ ሲሆን፣ ሁሉም የተመድ አባል ሀገራት ዓለም አቀፍ ወረርሽኙን በዓለም አቀፍ ትብብር እና አብሮነት ላይ ተመሥርቶ መከላከል እንደሚገባ ተመልክቷል።“የተመድ ቻርተር ውስጥ የተካተቱትን ዓላማዎች እና መርሆዎችን መከተል እና ቻርተሩ በሚያዝዘው መሠረት ሀገራት እርስ በርስ የመተባበር ግዴታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን” ብለዋል ደብዳቤውን የጻፉት አባል ሀገራቱ “የተመድ ቻርተርን ዓላማዎችና መርሆዎችን እንዲሁም ባለብዙ ግንኙነትንና መሠረታዊ ዓለም አቀፍ ግንኙነትን ያካተተውን ዓለም አቀፍ ሕግን በተቃረነ መልኩ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚወሰዱ አስገዳጅ የተናጠል እርምጃዎች በእጅጉ ያሳስቡናል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ዒላማ በተደረጉ ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚወሰዱ አስገዳጅ የተናጠል እርምጃዎች በሀገራቱ ላይ ከባድ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብአዊ ጫና የሚያስከትሉ በመሆኑ ሀገራቱ ሰብአዊ መብትን ለማሻሻልና ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት በእጅጉ እየገደቡ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የተቃውሞ ደብዳቤውን ለተመድ የላኩት አባላት፦ አንጎላ፣ አንቲጓ እና ባርቡዳ፣ ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ቬኒዙዌላ፣ ቡሩንዲ፣ ካምቦዲያ፣ ካሜሩን፣ ቻይና፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኩባ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዶሚኒካ፣ ግብፅ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ላኦስ፣ ናሚቢያ፣ ኒካራጓ፣ ፓኪስታን፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን፣ ሴይንት ቪንሰንት እና ግሬናዲንስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስሪላንካ፣ ፍልስጤም፣ ሱዳን፣ ሶሪያ እና ዚምባብዌ ናቸው።

China and 29 other countries deliver UN statement against sanctions

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply